08/04/2026
"በሰሙነ ሕማማት ስለ ሰላምና ፍቅር መፀለይ ይገባል"-ብፁዕ አቡነ በርናባስ
ሰቆጣ፣ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (Waghimra Communication) የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርናባስ በሰሙነ ሕማማት ስለ ሀገር ሰላምና የሕዝቦች አንድነት አብዝቶ መፀለይ እንደሚገባ ለምእመናን አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕነታቸው በመልእክታቸውም ከሆሳዕና ማግሥት ሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ሰሙነ ሕማማት (የሕመም የመከራ ሳምንታት) እየተባለ ይጠራል ብለዋል።
በእነዚህ ዕለታት ማእመናን ከመፆም፣ ከመፀለይና መስገድ ባለፈ ስለሀገር ሰላም ስለ ሕዝብ አንድነትና ፍቅር አብዝቶ በመፀለይ ማሣለፍ ይገባል ነው ያሉት።
በዚህ ሳምንት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከሁልጊዜው በተለየ ይጾማል፣ ይፀለያል እንዲሁም ኪርያላይሶን እየተባለም ይሰገዳል ብለዋል።
ሰሙነ ሕማማት የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙና ሞቱ እንዲሁም ለሰው ልጅ ስለከፈለው ዋጋ የሚታሰብበት ሲሆን ምእመናኑንም በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ተግባረ ነፍሳቸውን የሚፈፅሙበት ሳምንት ነው።
በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ አድባራትና ገዳማት ግብረ ሕማማት የተሰኘ መጽሐፍ የየዕለቱና የሰዓቱ እየተለየ ይነበባል።ሊቃውንቱም ነገረ ሕማሙን፣ ስቅለቱንና ሞቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ እያጣቀሱ ያሥተምራሉ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ-ኽምራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
✔Facebook ፌስቡክ :-https://www.facebook.com/waghimracom/
✔Telegram ቴሌግራም ፡- https://t.me/waghimracomm
✔X ኤክስ :-https://X.com/waghimra_comm
✔You tube ዩቲዩብ ፡-https://www.youtube.com/channel/UCi9Rw14v6HxZy5zNv4xe