09/06/2026
ሰበር ዜና‼️
➖➖
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን በማፍረስ ሥልጣን በኃይል የያዘው በደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የክልሉ አስተዳደር፤ አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን የሚፈቅድና ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስት የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ።
ረቂቅ አዋጅ፤ ዕድሜው የደረሠ ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ በወታደራዊ ግዳጅ እንዲሳተፍ ግዴታ የሚጥል ሲሆን፤ ጥሪውን የማይቀበል ከ10 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚጣልበት ደንግጓል።
የክተት ጥሪውን መሸሽ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ሀሰተኛ የሕክምና ማስረጃ የሚሠጡ የጤና ባለሙያዎችም እስከ 50 ሺሕ ብር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በረቂቁ ላይ ሠፍሯል። ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት የሚመራው የክልሉ ፕሬዝዳንት፣ የተዋጊ ኃይሎች የበላይ አዛዥ እንደሚኾን ተጠቅሷል።
በጦር ግንባር የተከፈለውን መስዋዕትነትና የሕዝቡን ትግል የሚያሳንስ ወይም የሚያጠለሽ ጽሑፍ፣ ንግግር ወይም ምስል ማሰራጨት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣም ተደንግጓል።