About Ethiopians

About Ethiopians Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from About Ethiopians, Grocers, Addis Ababa.

14/10/2026
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎች:-
04/10/2026

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎች:-

ዜና በራያ ዙሪያጦርነት ጠማቂው ህወሃት ሠራዊታችን እየወሰደ ባለው መልሶ ማጥቃት የእጁን እያገኘ ነው።ለሠላም ያልተዘረጋ እጅ ለተንኮል ወደር የለውም እንደማባለው የጥፋት ዓላማን ተሸክሞ የህዝ...
02/10/2026

ዜና በራያ ዙሪያ

ጦርነት ጠማቂው ህወሃት ሠራዊታችን እየወሰደ ባለው መልሶ ማጥቃት የእጁን እያገኘ ነው።

ለሠላም ያልተዘረጋ እጅ ለተንኮል ወደር የለውም እንደማባለው የጥፋት ዓላማን ተሸክሞ የህዝብን ሠላም ለማናጋት ጦርነት የገጠመው ህወሃት ከሰሞኑ ኮሩ በወሰደበት ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ እየተሽመደመደና ንብረቱን ጥሎ እየሸሸ ነው።

ህወሃት ለውድመት ሲጠቀምባቸው የነበሩ መድፎችን ጨምሮ የተለያዩ ተተኳሾችን እና ተቀጣጣዮችን እያዝርከረከ ጥሎ ሸሽቷል።

ወቅታዊ መረጃዋጃ እና ጥሙጋን የኢትዮጵያ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸዋል። ወደ አላማጣ የሚደረገው ጉዞ/ግስጋሴ ቀጥሏል።የህወሓት ታጣቂዎች በሁሉም አቅጣጫ እየተበተኑ ነው። የደቡብ ግንባር አዛዥ ጆን መ...
26/09/2026

ወቅታዊ መረጃ

ዋጃ እና ጥሙጋን የኢትዮጵያ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸዋል። ወደ አላማጣ የሚደረገው ጉዞ/ግስጋሴ ቀጥሏል።

የህወሓት ታጣቂዎች በሁሉም አቅጣጫ እየተበተኑ ነው። የደቡብ ግንባር አዛዥ ጆን መዲድን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አዛዦች፣ “አልቻልንም፤ ሠራዊታችን እየተበተነብን ነው” ብለዋል።

በራያ አላማጣ የሚገኙ ሁሉም የገጠር ወረዳዎችና ቦታዎች ነፃ የወጡ ሲሆን የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዝናቡ ገብረመድህን ከነሙሉ ተባባሪዎቹ/አጃቢዎቹ ጋር ወደ መቐለ አቅጣጫ ሸሽቷል።

ህወሓት በደቡብ ግንባር እና በዋግኽምራ ዞን የድሮን ጥቃት የተቀበለች ሲሆን በዚህ ግንባር ከሌሎች የሚለየው የህወሓት ታጣቂ ኃይል በቁጥር 5 የሚደርሱ መድፎችን ይዞ እንደነበር ተገልጿል። በድብርሳኤ 1 መድፍ፣ በ02 ቲያ 2 መድፎች እና በራያ አላማጣ ወረዳ፣ ፋጫ በተባለ ቦታ 2 መድፎች፣ በድምሩ 5 መድፎች በድሮን ጥቃት ተመትተዋል የሚል መረጃ ተሰጥቷል። በስፍራው የነበረው የሜካናይዝድ ኃይልም ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።

በላሊበላ ግንባር ደግሞ ታጣቂዎች“ሁሉም ተበታትነዋል የተረፉትን አሰባስበው ጦርነቱን ለማስቀጠል እንዲሁም ለማጥቃትና ለመከላከል ቢሞኩሩም ፤ አልቻሉም።
እየሞቱ፣ እየቆሰሉ እና እየሸሹ ነው ያሉት ።

ኮሩ የሀገር እና የህዝብ ጠላቶችን በላቀ ጀግንነት እየተፋለመ እንደሚገኝ ተገለፀጦርነት ናፋቂው የህወሀት ቡድን በተኩለሽ፣ ድልድይ፣ ቀይ አፈርና አካባቢው የጀመረውን ትንኮሳ በቀጠናው የሚገኘው...
26/09/2026

ኮሩ የሀገር እና የህዝብ ጠላቶችን በላቀ ጀግንነት እየተፋለመ እንደሚገኝ ተገለፀ

ጦርነት ናፋቂው የህወሀት ቡድን በተኩለሽ፣ ድልድይ፣ ቀይ አፈርና አካባቢው የጀመረውን ትንኮሳ በቀጠናው የሚገኘው ኮር በፍፁም ሀገራዊ ጀግንነት በመመከት የጠላትን ምኞት እያከሰመ እንደሚገኝ የኮሩ አዛዥ ገልፀዋል።

እንደ አዛዡ ገለፃ ቡድኑ የጥፋት ተልዕኮውን ለመፈፀም ሲነሳሳ ያሰበውና በተግባር የገጠመው እውነታ በእጅጉ የተለያየበት ሲሆን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመቀየር ያደረጋቸው መፍጨርጨሮች ሁሉ ከንቱ በመቅረታቸው ታጣቂው ተስፋ የቆረጠበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

የቡድኑ ታጣቂዎች ከመዋጋት ይልቅ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ራሳቸውን ለማትረፍ ለሠራዊታችን እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን የጠቀሱት የኮሩ አዛዥ ለምርኮኞች አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኮሩ የተከፈተበትን ማጥቃት በታላቅ ሀገራዊ ጀግንነት በመመከት በመልሶ ማጥቃት በርካታ የጠላት ኃይል መማረኩን፣ መግደሉንና ማቁሰሉን እንዲሁም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በምርኮ መያዙን አዛዡ አሥታውቀዋል።

14/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ፑቲን አንድ ላይ ተጉዘው ወደ ስብሰባ ሲገቡ

Prime Minister Abiy Ahmed and President Vladimir Putin travel together to a meeting in New Delhi

08/09/2026

አዲስ አበባ ከአሜሪካዋ ቺካጎ ቀጥላ በዓለም 2ኛ ደረጃን ያዘች

አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የመቋቋም አቅሟ በ2ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች! የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አልፋ ጂኦ የተባለውን የጂኦስፓሻል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ጥናት ዋቢ አድርጎ እንዳስነበበው፣ በዓለም ዙሪያ ካሉ 72 ግዙፍ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ በዓየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ከተሞች ዝርዝር ውስጥ ከቺካጎ ቀጥላ የሁለተኛነት ደረጃን ይዛለች። ጥናቱ የከተሞችን የተጋላጭነት መጠን እና የመቋቋም ዝግጁነት ከግምት ውስጥ ያስገባ ሲሆን፣ እንደ ሜልበርን፣ ባርሴሎና እና ፓሪስ ያሉ ታዋቂ የዓለማችን ከተሞች ከአዲስ አበባ በታች ተቀምጠዋል።

ከተማዋ ለዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ እውቅና እንድትበቃ ያደረጓት በቅርብ ጊዜያት ትኩረት ተሰጥቷቸው የተከናወኑት መጠነ ሰፊ የልማት ስራዎች መሆናቸው ተመላክቷል። በተለይም በከተማዋ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻዎች ማሻሻያ እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች የዓየር ንብረት ተጽዕኖን ለመቋቋም ከፍተኛ አቅም የፈጠሩ በመሆናቸው ለዚህ ስኬት ዋነኛ ምክንያቶች ሆነዋል።

የትውልድ ስራ ይቀጥላል፤ የውሾቹ ከንቱ ጩኸት የሚያቆመው አንዳች ስራ አይኖርም!!​ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ያገኙት ዓለም አቀፍ ሽልማት አዲስ አበባ ለህፃናት ሁ...
06/09/2026

የትውልድ ስራ ይቀጥላል፤ የውሾቹ ከንቱ ጩኸት የሚያቆመው አንዳች ስራ አይኖርም!!
​ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ያገኙት ዓለም አቀፍ ሽልማት አዲስ አበባ ለህፃናት ሁለንተናዊ እድገት እያደረገች ያለውን ታሪካዊ ስራ የሚያረጋግጥ ነው።

ከዚህ ቀደም የመጫወቻ ስፍራ ኖሯቸው ለማያውቁ፣ በበቂ ሁኔታ እንክብካቤና ትምህርት ላላገኙ፣ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ ህፃናት ዛሬ ላይ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ የነገዋን አገር ብሩህ ተስፋ የሚገነባ ነው። እኛ በልጅነታችን ያላገኘነውን፣ አይተነውም የማናውቀውን እና ተመኝተነው የቀረነውን የህፃናት መዋያ፣ መዝናኛ እና ዘመናዊ የእንክብካቤ ስፍራዎች ዛሬ ልጆቻችን በየአካባቢያቸው በስፋት ሲያገኙ ማየት እጅግ አስደሳችና የልብን የሚያረካ ነው። ይህ የትውልድ ግንባታ ስራ ማንም ሊያሳንሰው የማይችል ትልቅ እውነት ነው።

​ይሁን እንጂ የፖለቲካ ባህላችን ያወረሰን የማጣመም፣ የማሳነስ እና የማጥላላት አባዜ የተጠናወታቸው እንደ ፎርቹን እና ዘሃበሻ የመሳሰሉ የሚዲያ አካላት ይህንን ብሩህ ስኬት ለማጠልሸት ሲሞክሩ ተስተውሏል። ነገር ግን ይህ ምኞታቸው ይህንን ታላቅ ውጤት ፈፅሞ ሊያሳንሰው ሆነ ሊደብቀው አይችልም። ይህ አይነቱ እኩይ ተግባር የራሳቸውን ደካማ ማንነት እና የዕይታ መዛባት አጋልጦ ከማውጣት ባለፈ በተግባር የሚያመጣው ምንም አይነት ተጨባጭ ለውጥ የለም።

​ የከተማዋ አስተዳደር እና ከንቲባዋ የጀመሩት ትውልድን የመቅረፅ ታላቅ ስራ ወደኋላ ሳይል በሙሉ ሀይል ተጠናክሮ ይቀጥላል። ፈረንጆች "ውሾች ይጮሃሉ፤ ገመሉ ግን ጉዞውን ይቀጥላል" እንደሚሉት፣ ምንም ያህል የስም ማጥፋት ዘመቻ ቢከፈትም የብልፅግና እና የትውልድ ግንባታ ጉዞው ቆም ብሎ ወደኋላ አያይም። ለህፃናት የተዘረጋው ይህ የፍቅርና የእንክብካቤ መሰረት የነገዋን ጠንካራ ኢትዮጵያ የሚገነባ ፅኑ መሰረት በመሆኑ በየትኛውም ሁኔታ የጠላቶች ጩኸት ሊያደናቅፈው አይችልም።

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when About Ethiopians posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category