15/06/2026
እረ በመኪና አደጋ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን አለቁ! መፍትሄው ምንድን ነው? አረ ይሄ ነገር ስር እየሰደደ ነው!
ከትራፊክ አደጋ መበራከት ጋር ተያይዞ አሳሳቢነቱ በጨመረበት በዚህ ወቅት፣ በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ በዛሬው ዕለት እጅግ ዘግናኝ የትራፊክ አደጋ መከሰቱን ፖሊስ አስታውቋል።
ከደሴ ከተማ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ፣ ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ ላይ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው አስቸጋሪ ስፍራ ላይ ቁልቁል ተከስክሷል።
ተሽከርካሪው በግምት 100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል መግባቱን የገለጹት የጸጥታ አካላት፣ በአደጋው ሳቢያ እስካሁን የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በርካታ መንገደኞች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በሕይወት የተረፉትን ተጎጂዎች ወደ ሕክምና ተቋማት ለማድረስና አስቸኳይ ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በዝርዝር በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን፣ መሰል አደጋዎችን ለመግታት አሽከርካሪዎችም ሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ጥብቅ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ወገኖቻችን
በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
📷አሚኮ፦ ሳሙኤል ኪሮስ
ጉርሻ Page
🌴🌴🌴