Addis Ketema Woreda 10 Prosperity ፓርቲ

Addis Ketema Woreda 10 Prosperity   ፓርቲ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ketema Woreda 10 Prosperity ፓርቲ, Grocers, Addis ababa, Addis Ababa.

በምክክር የምትፀና ሀገር! #መደመር
22/08/2026

በምክክር የምትፀና ሀገር!

#መደመር

"...በቀውስ መሐል ፈውስ፣ በመፈራረስ ውስጥ መታደስ፣ ተበታትኖ በመጥፋት መካከል ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት የመደመር መንገድ ነው።"(የመደመር_መንግሥት_ገጽ_113)
22/08/2026

"...በቀውስ መሐል ፈውስ፣ በመፈራረስ ውስጥ መታደስ፣ ተበታትኖ በመጥፋት መካከል ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት የመደመር መንገድ ነው።"

(የመደመር_መንግሥት_ገጽ_113)

 !​በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እና ወረዳ 4 በጋራ "በውይይት የተቃኘ ገዢ ትርክት ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ!" በሚል መሪ ቃል የገዢ ትርክት የኪነጥበብ ምሽት  በታላቅ ድ...
21/08/2026

!

​በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እና ወረዳ 4 በጋራ "በውይይት የተቃኘ ገዢ ትርክት ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ!" በሚል መሪ ቃል የገዢ ትርክት የኪነጥበብ ምሽት በታላቅ ድምቀት አካሂደዋል።

​ዘላቂና አዎንታዊ የጋራ ገዢ ትርክት እውን ሊሆን የሚችለው በህዝቦች መካከል በሚደረግ ግልጽና አካታች የምክክር ሂደት ብቻ ነዉ በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር የሀገርን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ፣ ታሪካዊ ቅሬታዎችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት እና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል::

ገዢ ትርክት በዜጎች ነፃ ውይይት፣ መደማመጥና በሀገራዊ ምክክር ሂደት በጋራ ስምምነት የሚገነባ ነዉ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር፣ የፖለቲካና የማህበራዊ አለመረጋጋቶችን በማስወገድ ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ብልፅግና ጽኑ መሰረት የሚጥል በመሆኑና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሃሳብ የበላይነት፣ ህብረ-ብሄራዊ አንድነት እና በውይይት የሚያምን የካበተ የፖለቲካ ባህል አስፈላጊነት ለማስገንዘብ የኪነጥበብ ስራዎች የህዝብን ስሜት በመግለጽ፣ የጋራ እሴቶችን በማጎልበትና ሀገራዊ ምክክሩን በማቀላጠፍ ረገድ ያላቸው ቀላል የማይባል ነዉ።

​በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ተሳፊዎች ሀገራዊ ምክክሩ የስኬት መንገድ እንዲይዝ እና ገዢ ትርክት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ያካተተ ይሆን ዘንድ ንቁ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ። ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ  አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ  ውሳኔዎችን  አስተላልፏል፡፡በዚህ መ...
21/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

ካቢኔው በዛሬው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሠረት፦

1- የማህበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ተጠቃሚዎች መዋጮን ለማሻሻል የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

2- ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች (ለሆቴል፣ ለሞልና አፓርትመንት፣ ኢንዱስትሪ፣ ለበጎ አድራጎት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና የህክምና ተቋማት) የማስፋፍያና አዳዲስ የመሬት ጥያቄዎች ለመመለስ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቋል።

3- በከፊል በኮሪደር ለምተው፣ በከፊል ሳይለሙ የቆዩ አከባቢዎችን በተሟላ ሁኔታ ለማልማት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

ኢትዮጵያ መርከብ ናት፤  ሰዎች የሚሰቃዩት ግን መርከቡን አፍርሰው ጀልባ በመስራት ነው፤ ጀልባ ባህር  አያቋርጥርም ፤ መርከብ ግን ባህር ያቋርጣል፤ ትልቁን ሩቅ የሚወስድህን አፍርሰህ ትንንሹ...
21/08/2026

ኢትዮጵያ መርከብ ናት፤ ሰዎች የሚሰቃዩት ግን መርከቡን አፍርሰው ጀልባ በመስራት ነው፤ ጀልባ ባህር አያቋርጥርም ፤ መርከብ ግን ባህር ያቋርጣል፤ ትልቁን ሩቅ የሚወስድህን አፍርሰህ ትንንሹን ብትሰራ ሰፈር ትቀራለህ እንጂ አትሻገርም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በህብረተሰቡ የነቃና የተደራጀ ተሳትፎ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም እናረጋግጣለን !ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም በመንግስት፣ በፀጥታ አካላት እና  በህብረተሰቡ ባለቤትነት፣ ተሳትፎና የጋራ ኃላፊነት የሚ...
20/08/2026

በህብረተሰቡ የነቃና የተደራጀ ተሳትፎ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም እናረጋግጣለን !

ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም በመንግስት፣ በፀጥታ አካላት እና በህብረተሰቡ ባለቤትነት፣ ተሳትፎና የጋራ ኃላፊነት የሚረጋገጥ የብልፅግና መሠረት ነዉ።

የመደመር መንግስት ሰላምን ከህዝብ ጋር በመሆን የሚገነባ፣ የሁሉንም ድምፅ የሚያዳምጥና የጋራ ጥቅምን የሚያስቀድም የፖለቲካ አቅጣጫን ይከተላል። ይህም ሰላምን ከልማት፣ ልማትን ከፍትሃዊ ተሳትፎና ከህዝብ ባለቤትነት ጋር በማስተሳሰር የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሠረት ይፈጥራል።

በዚህ ሂደት ውስጥም መዲናችን አዲስ አበባም የሰላምና የአብሮነት ከተማ እየሆነች መምጣቷ የዚህ ጥረት አንዱ ተጨባጭ ምልክት ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች በሰላም ጉዳይ ያላቸው ተሳትፎና ባለቤትነት እየጎለበተ ሲመጣ፣ የሰላም አደረጃጀቶችና የማህበረሰብ ትብብር እየጠናከረ በመምጣቱ በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት እየተጠናከረ ይገኛል።

ዘላቂ ሰላምን በከተማዋ ለማስፈንም የሰላም ሠራዊት ተሳትፎና ባለቤትነት እየጨመረ መምጣቱ የሰላም ግንባታው ከመንግስት ተቋማት ተግባርነት ብቻ መሆን ወጥቶ ወደ ህዝብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እየሰረጸ መሆኑን ያሳያል። ዜጎች ሰላምን የሚጠብቁት ተጠቃሚዎች ብቻ ሆነው ሳይሆን የሰላም አቅምና ባለቤት ሆነው ሲንቀሳቀሱ የሰላም ዘላቂነት ስለሚጠናከር መሆኑን ተረድተዋል።

ይህንንም ለማፅናት የከተማችን ነዋሪዎች ቀን እና ሌሊት የአካባቢያቸውን ሰላም ለማፅናት እየተጉ የሚገኝ ሲሆን በዛሬዉ እለትም በአዲስ ከተማ ላለፏት ተከታታይ ቀናት ስልጠና የወሰዱ የሰላም ሰራዊት አባላት በዛሬዉ እለት ተመርቀዉ ወደ ስምሪት ገብተዋል ።

ፈጣን ዕድገታችን አካታች በመሆኑ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አስችሏል !ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን ልዕልና ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ህይወት ለማሻሻልን፣ ሰብአዊ ክብርን ለማስጠበቅ...
20/08/2026

ፈጣን ዕድገታችን አካታች በመሆኑ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አስችሏል !

ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን ልዕልና ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ህይወት ለማሻሻልን፣ ሰብአዊ ክብርን ለማስጠበቅ የሚተጋ ሰው ተኮር ፓርቲ ነው።

ሰው ተኮር እሳቤዎቹን ተግባራዊ በማድረግ ፓርቲያችን የህዝባችንን የተከማቹ ውስብስብ ችግሮች እያስወገደ ሲሆን፣ በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ተፈጥሯዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ጭምር ኢትዮጵያን ከፍ ያደረጉ አንፀባራቂ ስኬቶችንም ማስመዝገብ ችሏል፡፡

በማህበራዊ ልማቶችም ህዝባችንን ከጥልቅ ጉስቁልና በማውጣት ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

የህዝባችን ትልቅ ፈተና የሆነውን የመኖሪያ ቤት አዳጊ ፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ችግር ለመቅረፍ የሚተገበሩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ታሳቢ እንዲያደርጉ መደረጉ የበርካቶችን ህይወት አሻሽሏል፡፡

አቅም የሌላቸውን ዜጎች፣ አረጋውያንን እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች ለመደገፍ የተዘረጉ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራሞችም የህዝባችንን የቆዩ የመረዳዳት እና የአብሮነት እሴቶች ማጠናከር ጀምረዋል፡፡

ህፃናት በትምህርት ገበታ ላይ እንዲውሉ ከማስቻል ባለፈ ለትምህርት ጥራት፣ ለተማሪዎች ጤና እንዲሁም የኑሮ ውድነቱን ጫና ለማቃለል ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የተማሪዎች ምገባ አገልግሎትም የሰው ተኮር እሳቤ ውጤት ነው፡፡

በየአካባቢው በተገነቡ የምገባ ማዕከላት አቅም የሌላቸው ዜጎች ቢያንስ በቀን አንዴ መመገብ እንዲችሉ መደረጉም ችግሮችን በራስ አቅም የመፍታትና የመሻገር ባህልን ለመገንባት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራሉ፡፡

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስጀመሩትና አዲስ አበባን ህፃናት በምቾት የሚያድጉባት የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ የሚተጋው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምም ማህበራዊ ልማቶቻችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የዘላቂ ዕድገታችን መሰረት መሆናቸውን አመላካች ናቸው፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

የሀገረ መንግስት ግንባታ ማፅኛ፣ የመደመር ፍልስፍና ማሳያ! ሀገራዊ ምክክር! ዘላቂ  ሰላምን ለማስፈንና የጋራ ግቦችን ለማሳካት ምክክር የማንኛውም ስልጡን ማህበረሰብ መሠረታዊ መሣሪያ ነው። ...
19/08/2026

የሀገረ መንግስት ግንባታ ማፅኛ፣ የመደመር ፍልስፍና ማሳያ! ሀገራዊ ምክክር!

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና የጋራ ግቦችን ለማሳካት ምክክር የማንኛውም ስልጡን ማህበረሰብ መሠረታዊ መሣሪያ ነው። ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰለጠነ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ፣ እርስ በእርስ እንዲደማመጡና ለጋራ ችግሮች የጋራ መፍትሔ እንዲያበጁ ዕድል የሚፈጥር ሀገራዊ ምክክር ነገን አሻግሮ የሚመለከት ተራማጅ ሀሳብ ነው፡፡

ምክክር ባለበት ቦታ ጥላቻና ግጭት ተወግደው መተማመንና ትብብር ይሰፍናሉ፤ ፅንፈኝነት እየተወገደ ሚዛናዊነት ይጎለብታል፣ መገፋፋት እየቀረ መደማመጥ ይጎለብታል፡፡ ሀገራዊ ምክክር ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

የብልፅግና ፓርቲ ፍኖተ ካርታ የሆነው "መደመር" ለምክክርና ለውይይት ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ መደመር ማለት ካለፉት ስኬቶች መማር፣ ስህተቶችን ማረም እና ለአገር የሚበጁ አዳዲስ እሳቤዎችን በማቀናጀት ወደፊት መራመድ ነው። ይህ እሳቤ ልዩነቶችን እንደ ውበትና እንደ ፀጋ በመቁጠር፣ የሁሉንም ዜጎች ተሳትፎና እውቀት በማቀናጀት፣ ለጋራ ብልፅግና በጋራ መታተር በመሆኑ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት የማይተካ ሚና ያበረክታል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያካሄደች የምትገኘው ታሪካዊው የምክክር ጉባኤ የመደመር እሳቤ የሚንፀባረቅበት ተግባራዊ እርምጃ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በታሪካዊ ቅራኔዎች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መፍትሄ ለመፈለግና በዋና ዋና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ ስምምነት ለመፍጠር ያለመው ይህ ምክክር የፖለቲካ ልሂቃኑ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድምፅ የሚስተጋባበትና የሚሰማበት ወሳኝ መድረክ ነው፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

ማህበራዊ ስብራቶቻችንን በመጠገን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!አካታቹ የብልፅግና የልማት ፖሊሲ በተግባር እየተተረጎመ በመሆኑ የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጎልብቷል፡፡  ሁለንተናዊ ብልፅግ...
19/08/2026

ማህበራዊ ስብራቶቻችንን በመጠገን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!

አካታቹ የብልፅግና የልማት ፖሊሲ በተግባር እየተተረጎመ በመሆኑ የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጎልብቷል፡፡ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞአችን የሁሉንም ዜጋ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

የፓርቲያችን ሰው ተኮር እሳቤዎች ሁሉም ዜጋ እኩል ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችለዋል።

ባዶ የምሳ እቃ በመያዝ ምሳቸውን ሳይመገቡ የሚውሉ በርካታ ተማሪዎች የነበሩባት አዲስ አበባ በጀመረችው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ፍትሀዊ የትምህርት ተደራሽነትን አሳድጋለች፡፡

በተለይም የአቅመ ደካማ ወላጆችን ሸክም በእጅጉ ማቃለል ያስቻለው ይህ ፕሮግራም ከትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ባሻገር የኑሮ ውድነቱን ጫናም እያቃለለ ነው፡፡

በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች የከተማችንን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ችግሮች ከመቅረፍ አንፃር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ጧሪ የሌላቸውን፣ የሀገር ባለውለታዎችንና አቅመ ደካሞችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግም ባለሀብቶችን እና የከተማችንን ነዋሪዎች በማስተባበር የከተማ አስተዳደሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በመገንባት የብዙዎችን እምባ አብሷል፡፡ በከተማችን እየተበራከቱ የሚገኙት የበጎነት መንደሮች የከተማችንን የለውጥ ግስጋሴም አፋጥነዋል፡፡

የምግብ ሉዓላዊነትን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብርቱ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን፤ ቢያንስ በቀን አንዴ መመገብ የማይችሉ ዜጎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በአቅራቢያቸው የምገባ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚያሻሽሉ ሰው ተኮር ልማቶችን በማጠናከር ፣ ማህበራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጣችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

ሰው ተኮርነት ለአዲስ ከተማ ከፍታ!​ሰው ተኮር እሳቤ የዜጎችን ኑሮ ና አኗኗር በመቀየር  የከተማችን አዲስ አበባ ዋነኛ የመልካም ለውጥና የዕድገት መሰረት እየሆነ ይገኛል ።በአካታችነትና ፍት...
19/08/2026

ሰው ተኮርነት ለአዲስ ከተማ ከፍታ!

​ሰው ተኮር እሳቤ የዜጎችን ኑሮ ና አኗኗር በመቀየር የከተማችን አዲስ አበባ ዋነኛ የመልካም ለውጥና የዕድገት መሰረት እየሆነ ይገኛል ።

በአካታችነትና ፍትሀዊነት መርህ የማህበረሰቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት፣ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን በመፍጠር አቅመ-ደካሞችን፣ ህጻናትንና አረጋውያን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ይገኛል።

​ሰውን ማዕከል ያደረገ ልማት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ ኘሮግራም በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Woreda 10 Prosperity ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category