Addis Ababb

Addis Ababb Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababb, Grocers, Addis ababa, Addis Ababa.

29/08/2026
20/08/2026
17/08/2026

"ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!

የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው።

‎የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል።

የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

‎ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባን እንደ ደሴት ማሰብ ከንቱ ቁዠት ነው፤ የሀሰት ፕሮፖጋንዳው ይቁም!​በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አዲስ አበባን እና ኦሮሚያን እርስ በርስ ለማጋጨት ሆን ተብለው የሚነዙ የተሳሳቱ ትርክቶ...
15/08/2026

አዲስ አበባን እንደ ደሴት ማሰብ ከንቱ ቁዠት ነው፤ የሀሰት ፕሮፖጋንዳው ይቁም!
​በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አዲስ አበባን እና ኦሮሚያን እርስ በርስ ለማጋጨት ሆን ተብለው የሚነዙ የተሳሳቱ ትርክቶችን በስፋት እየተመለከትን ነው። ነገር ግን ሁላችንም በግልጽ ልንገነዘበው የሚገባው ትልቁ እውነታ፣ አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያላት ግንኙነት እጅግ ጥብቅ፣ የማይነጣጠል እና ተፈጥሯዊ መሆኑን ነው። አዲስ አበባን ከዙሪያዋ ካለው የተፈጥሮ ማህጸን ሙሉ በሙሉ ነጥሎ እንደ ደሴት ብቻዋን እንድትኖር ማድረግ ፈጽሞ የማይቻል እና ከተፈጥሮ ህግ ጋር የሚጋጭ ነው። ይህን ለማድረግ መሞከርም ሆነ እንደዚያ አድርጎ ማሰብ ከንቱ ቁዠት ነው።
​ከተማዋ የእለት ተዕለት የምግብ ፍጆታዋን፣ የውሃ አቅርቦቷን፣ የግንባታ ጥሬ እቃዋን እንዲሁም የኢንቨስትመንት ፍላጎቷን የምታሟላው ከዚሁ ተፈጥሯዊ ጎረቤቷ ጋር በጥብቅ በመቀናጀት ነው። ላለፉት 35 አመታት የኦሮሚያ ክልል መንግስት መቀመጫ በመሆን፣ ህዝቡም በሰላም፣ በፍቅር እና በመከባበር አብሮ ኖሯል። ይህ የ35 ዓመታት ጤናማ አብሮነት ዛሬም ወደፊትም የሚቀጥል እንጂ፣ ማንም ፖለቲከኛ በፈጠረው የሀሰት ትርክት የሚፈርስ አይደለም።
​ስለዚህ፣ ከተማዋን "ልትወረር ነው" ወይም "በሌላ ክልል ልትዋጥ ነው" በሚል የሚሰራጨው አፍራሽ እና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በአስቸኳይ መቆም አለበት። ህዝባችንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ወንድማማች ህዝቦችን ለማጋጨት ለሚሰሩ የጥፋት ሃይሎች የፈጠራ ወሬ በፍጹም ጆሮ መስጠት የለበትም። በእነዚህ ወገኖች የሚነዛው አሉባልታ ለሀገራችን ሰላም ምንም አይነት ፋይዳ የለውም። አዲስ አበባ የሁላችንም ማዕከል እና ፌደራላዊ ከተማ ሆና የሰላም ጉዞዋን አጠናክራ ትቀጥላለች። ከሀሰተኛ መረጃ ራሳችንን በማራቅ ለጋራ እድገታችን እና ለሰላማችን ዘብ እንቁም! ኢትዮጵያ በህዝቦቿ አንድነት ፀንታ ትኖራለች!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababb posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category