Midroc ethiopia

Midroc ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Midroc ethiopia, Addis Ababa.

17/06/2025

የቴሌግራም ቻናላችንን ፍሎው በማረግ አዳዲስ መሪ ጃዎችን ያገኙ
MIDROC Investment Group ይቀላቀሉ።

ለማላዉ አቭኦካዶ ጅምላ አቅፋፋዮች አቭኦካዶ ምርት ባሁኑ ስዓት እጃችን ላይ ስለሚገኝ ተቀብላችሁ ለማከፋፈል የምትፈልጉ ያናግሩን
09/06/2025

ለማላዉ አቭኦካዶ ጅምላ አቅፋፋዮች
አቭኦካዶ ምርት ባሁኑ ስዓት እጃችን ላይ ስለሚገኝ ተቀብላችሁ ለማከፋፈል የምትፈልጉ ያናግሩን

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአለም አቀፍ የቡና ገበያ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸውን የቡና ምርቶቹን ይዞ የቡና ፌስቲቫል ላይ ይቀርባል።ተወደው የሚጠጡ የቡና ምርቶቹ በበቃ፣ ሊሙ፣ አየሁ፣ ገማ...
29/11/2024

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአለም አቀፍ የቡና ገበያ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸውን የቡና ምርቶቹን ይዞ የቡና ፌስቲቫል ላይ ይቀርባል።

ተወደው የሚጠጡ የቡና ምርቶቹ በበቃ፣ ሊሙ፣ አየሁ፣ ገማድሮ፣ ዱየና፣ በሃ እና ሆራይዘን ናቸው።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አዲስ አበባ ሕዳር 20/2017
************************************************************

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ነገ ቅዳሜ ሕዳር 21 እና እሁድ ሕዳር 22/2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል በሚካሄደው የቡና ፌስቲቫል ላይ ሰባቱንም የቡና ምርቶቹን ይዞ ይሳተፋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የቡና ፌስቲቫል (ኮፊ ፌስት) ላይ ሚድሮክን ጨምሮ አሥር የሚደርሱ ታዋቂ የቡና አምራችና ላኪ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል፡፡

የቡና አምራች ኩባንያዎቹ የተለያዩ ዓይነት የቡና ምርቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ለኤክስፖርት የተዘጋጁ የቡና ምርቶችን ጨምሮ ለሸያጭ ይቀርባሉ፡፡ የቡና ቀመሳ ሥነ-ስርዓትም ይካሄዳል፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቡና ዘርፍ በስድስቱ ሰፋፊ እርሻዎቹ ማለትም በበቃ፣ ሊሙ፣ አየሁ፣ ገማድሮ፣ ዱየና እና በሃ የቡና እርሻዎች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችንና ተወዳጅነትን በማሟላት ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማዘጋጀት ወደ ዉጪ ሀገራት በመላክ ለሃገራችን የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ላይ ይገኛል።

ቡናን ከማምረት በተጨማሪ የማዘጋጀትና የማከማቸት አገልግሎት ይሰጣል። በምርትና አገልግሎቱም እንደ ሃገር በተደጋጋሚ ጊዜያት ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር ያለዉን የስፖንሰረሽፕ ስምምነት ማደሱን አስታወቀ።የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ...
09/11/2024

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር ያለዉን የስፖንሰረሽፕ ስምምነት ማደሱን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለመደገፍ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
************************************************************

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ለ28 አመታት በተከታታይ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ስፖንሰር በማደረግ ላይ የቆየ ነው ።

ስምምነቱን የሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ንጉስ ሰለሞን እና የአዲስ አበባ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ ተፈራርሟል።

ዛሬ የተፈራረምነው ስምምነት በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሀገራችን ታሪክ ለማስቀጠል ነው ያሉት የሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ንጉሱ ሰለሞን ናቸው ።

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ በበኩላቸው ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ፌደሬሽኑን ስፖንሰር በማድረግ በአለም ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች የሀገሪቷን ባንዲራ ከፍ እንዲያደርጉ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ እያደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ሀገራችን በአለም አትሌቲክስ ኦሎምፒክ መድረኮች አትሌቶቻችን አመርቂ ዉጤት እንዲያስመዘግቡ ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል ።

ሁለቱም ተቋማት ለወደፊትም በታማኝነት አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቀድሞ አትሌቶች ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ለረጅም አመታት በተለያየ መልኩ ላደረገላቸው ድጋፎች አመስግነዋል።

በመድረኩ ላይ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያም ተሰጥቷል።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ 8 ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን ምርቶቹም ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ አፕል፣ ሚሪንዳ ኦሬንጅ፣ ሚሪንዳ ቶኒክ እና 7ኣፕ ናቸው።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከነውማን ካፌ ግሩፕ (Neumann Kaffee Gruppe) ጋር የቡና ግብይት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተመረጡ የኢ...
07/11/2024

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከነውማን ካፌ ግሩፕ (Neumann Kaffee Gruppe) ጋር የቡና ግብይት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተመረጡ የኢትዮጵያ ቡናን ወደ ዉጪ ሀገራት በመላክ ለሃገር ኢኮኖሚ እያደረገ ያለዉን አስተዋጽኦ ለማሳደግ የሚረዳ ነው ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አዲስ አበባ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
**********************************************************************

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መቀመጫውን በጀርመን ካደረገው ድርጅት ነውማን ካፌ ግሩፕ ጋር የቡና ግብይት የሁለትዮሽ ስምምነት አድርጓል።

ነውማን ካፌ ግሩፕ 60 ድርጅቶችን በስሩ ያቀፈና ከ30 በላይ በሚሆኑ ሀገራት በቡና ሽያጭ ቀዳሚ ድርጅት ነው፡፡

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ እና የነውማን ካፌ ግሩፕ ባለቤትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ዴቪድ ነውማን ፈርመዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ከድርጅቱ ጋር መፈራረማቸው የሚድሮክ የቡና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት የሚጨምር መሆኑን ተናግረዋል።

የስምምነቱ አላማ በዋነኝነት የቡና ምርታማነትን መጨመር እና በሀገሪቱ የቡና እርሻ ልማትን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነም ገለፀዋል።

በተጨማሪም አቶ ጀማል ሚስተር ዴቪድ ነውማንን ኢትዮጵያን ከልባቸው የሚወዱና የኢትዮጵያን ቡና ለዓለም ገበያ በማስተዋወቅ ታላቅ ሚና ያላቸው እንደሆኑ በመግለፅ አመስግነዋቸዋል።

ሚስተር ዴቪድ ነውማን በበኩላቸው ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር የተፈራረሙት የሁለትዮሽ ስምምነት ዘላቂነት ያለዉ እንደሆነና በቡና ሳይንስ ላይ አብሮ በመስራት የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማስቻል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

አክለውም በኢትዮጵያ የቡና ገበያ ዉስጥ ትልቅ ሚና እየተወጣ ከሚገኘው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር አብሮ ለመስራት በመስማማታቸው የተሰማቸውን ደሰታ ገለፀዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነት ካለው ነውማን ካፌ ግሩፕ ጋር መፈራረሙ የሀገሪቱን የቡና ምርታማነት የሚያሳድግና ለኢትዮጵያ ታላቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በስምምነቱ እጅግ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቡና ዘርፍ በስድስቱ ሰፋፊ እርሻዎቹ ማለትም በበቃ፣ ሊሙ፣ አየሁ፣ ገማድሮ፣ ዱየና እና በሃ የቡና እርሻዎች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችንና ተወዳጅነትን በማሟላት ከፍተኛ ጥራት ያለቸውን ምርቶች በማዘጋጀት ወደ ዉጪ ሀገራት በመላክ ይታወቃል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቡናን ከማምረት በተጨማሪ የማዘጋጀትና የማከማቸት አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም ተቆልቶ የተፈጨ ቡናን ለሀገር ዉስጥና ለዉጪ ሀገራት በማቅረብም እንደሃገር በተደጋጋሚ ጊዜያት ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የሻይ ምርት ማሸጊያና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የአፍሪካ ካይዘን 2024 ዓመታዊ ኮንፈረንስ በላቀ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
03/11/2024

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
የሻይ ምርት ማሸጊያና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የአፍሪካ ካይዘን 2024 ዓመታዊ ኮንፈረንስ በላቀ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የሻይ ም/ማ/ማ/ ፋብሪካ በአፍሪካ ካይዘን 2024 ዓመታዊ ኮንፈረንስ በካይዘን ትግበራ በላቀ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ!*****...
30/10/2024

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
የሻይ ም/ማ/ማ/ ፋብሪካ በአፍሪካ ካይዘን 2024 ዓመታዊ ኮንፈረንስ በካይዘን ትግበራ በላቀ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ!
***********************************************
ኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የሻይ ም/ማ/ማ ፋብሪካ ጥቅምት 18 እና 19 2017 ዓ.ም. በቱኒዝ ቱኒዝያ በተካሄደው የአፍሪካ ካይዘን ዓመታዊ ኮንፈረንስ 2024 ላይ በካይዘን ትግበራ ላስመዘገበው የላቀ ውጤት( OUTSTANDING) ደረጃ እውቅና አገኘ ።

ሽልማቱን አቶ ጌታእንዳለው መንበሩ የኩባንያው ከፍተኛ የካይዘን ኤክስፐርት ከቱኒዚያ የኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ምኒስቴር እና በቱኒዚያ የጃፓን አንባሳደር እጅ ተቀብለዋል ።

ኮንፈረንሱ በፓን አፍሪካ ምርታማነት ማህበር (PAPA) እና በቱኒዚያ የኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስተናጋጅነት እንዲሁም በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) እና በአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ (AUDA-NEPAD) በጋራ አዘጋጅነት የተከናወነ ሲሆን ከአፍሪካ፣ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከላቲን አሜሪካ ለተውጣጡ ተሳታፊዎች በምርታማነት ማሻሻያ ረገድ መልካም ተሞክሮዎችን አካፍሏል።

ኢትዮ አግሪ-ሴፍት ራሱን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ የካይዘን አሰራር ስርአትን የሻይ አመራረት እሴት ሰንሰለት ውስጥ በመተግበር በብክነት ቅነሳ፣ በጥራት ቁጥጥር ማሻሻያ እና በሰራተኞች ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ፖሊሲ መከተል እንዴት የኢንዱስትሪዎች ዘላቂ እድገት እና የላቀ ተወዳዳሪነት ላይ በጎ ተፅኖ መፍጠር እንደሚችል ያገኘውን ልምድ በዘርፉ ባለሙያ በአቶ ጌታእንዳለው መንበሩ ባቀረቡት ማብራሪያ አማካኝነት አካፍሏል።

ኩባንያው እነዚህን መርሆች ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነት እና በሻይ ም/ማ/ማ/ ፋብሪካ ላይ ያስመዘገበውን ውጤት በቀሪ ልማቶቹ ላይ ለማስመዝገብ በየደረጃው ዕቅድ ይዞ ከፍተኛ በሆነ ተነሳሽነት እና ክትትል እየሰራ ሲሆን ዘንድሮም አዳዲስ ልማቶችን በትግበራ ከማካተት በተጨማሪ እየተከናወነ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድር ላይ TPPFን ጨምሮ ሁለቱ የሻይ እርሻ ልማቶች (ጉማሮ እና ውሽውሽ) የመጨረሻ የውድድር መራፍ ላይ አድርሷል፤ በቀጣይ ዓመትም (2025) በሚደረገው የአፍሪካ ካይዘን ሽልማት ላይ ከሻይ ፋብሪካ የተገኙ መልካም ተሞክሮችን በመቀመር ይህንን ውጤት በሁለቱ የሻይ እርሻ ልማቶች (ጉማሮ እና ውሽውሽ) ለመድገም እና ሁለቱን የቡና ልማቶች (ገማድሮ እና ዱይናን) ደግሞ ለአገር አቀፍ ካይዘን ውድድር ብቁ ለማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

ይህ ትግበራ በፖሊሲ ደረጃ ተይዞ ውጤት እንዲያሳይ የላቀ አመራር እየሰጡ የሚገኙት አቶ ጀማል አህመድ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ አቶ ፈለቀ ታደሰ (በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በግብርና ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ)፣ የማያቋርጥ ሙያዊ ማማከር ለሚሰጠው በክላስተሩ አቅም ግንባታ እና የሲስተም ልማት ዳይረክቶሬት ፣ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ተፈጻሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ለሚገኘው የኩባንያው አመራር፣ በየደረጃው ድጋፉን የሚሰጠው የኩባንያው ሰራተኛ እንዲሁም የአሰራር ስራቶች ግባቸውን እንዲመቱ በብቃት እየተገበረ የሚገኘው የሻይ ም/ማ/ማ ፋብሪካ አመራር እና ሰራተኞች ለተገኘው ውጤት ያላቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው:
ኢአሴ ጥቅምት 2017

ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪ (ኤሊኮ)ን ጎበኙ።ከፍተኛ የመንግስት አመራሮቹ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል ።ሚ...
28/10/2024

ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪ (ኤሊኮ)ን ጎበኙ።

ከፍተኛ የመንግስት አመራሮቹ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ
****************************************************************
በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፣የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አካልወለድ አድማሱ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ተከሉ ለጎብኚዎች ስለ ድርጅቱ ገለፃ አድርገዋል።

በገለፃቸውም ኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪ የተለያዩ የቆዳ ዉጤቶችን በማምረት ለሀገር ዉስጥ አምራቾችና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ኤሊኮ አሁን ላይ ትርፋማ በመሆን ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር እና የዉጪ ምንዛሬን ማስገኘት በመቻሉ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም የድርጅቱን አቅም የበለጠ ለማሳደግና በስራ ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሰሩ አምባሳደር ግርማ ብሩ ገልፀዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አካልወለድ አድማሱ በበኩላቸው ድርጅቱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ጫማዎች በማምረት ለውጪ ገቢያ በብዛት ለማቅረብ ጥናት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ኢትዮ-ሌዘር ኢንዱስትሪ የተለያዩ የበሬ፣ የፍየልና የበግ ቆዳዎችን በማምረት ለቆዳ አምራቾችና ለውጭ ገበያ ያቀርባል፤ እንዲሁም የሴፍቲ፣ የህጻናት፣ የአዘቦትና የሚሊተሪ ጫማዎችንም ያመርታል።

በተጨማሪም ኤሊኮ የቆዳ ቀበቶዎችን፣ የእግር ኳሶችን፣ ቦርሳዎችንና የሌዘር ጃኬቶችን በማምረት ለገበያ ያቀርባል፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለቂልጦ 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል የX-RAY Machine' ድጋፍ አደረገ።ሚድሮክ እንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ****************...
24/10/2024

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለቂልጦ 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል የX-RAY Machine' ድጋፍ አደረገ።

ሚድሮክ እንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ
******************************************************************

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የቂልጦ 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል የX-RAY Machine' ድጋፍ አድርጓል።

ስጦታውን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ለአካባቢው ተወካዮች አስረክበዋል።

ሆስፒታሉ ከዚህ በፊት የX-RAY Machine' ባለመኖሩ ታካሚዎች ለተለያዩ እንግልት ሲዳርጋቸው እንደነበር የአካባቢው ተወካዮች ተናግረዋል።

ለማሕበራዊ ችገሮች ቀደሞ በመድረስ የሚታወቀው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የወረዳው ነዋሪዎች በአካባቢያቸው አገልገሎቱን እንዲያገኙ ድጋፉን አድርጓል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀገር ደረጃ በተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች በማከናወን ላይ ሲሆን ለቂልጦ 1ኛ ደረጃ ሆስፒታል ባደረገው ድጋፍም የተሰማውን ደሰታ ይገልፃል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ከኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር ለኩላሊት ህሙማን የሚያገለግሉ የዲያልስስ ማሽኖችን ከሪኤጀንቶች ጋር በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Midroc ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share