Bekar yusuf

Bekar yusuf Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bekar yusuf, Grocers, Dire, Addis Ababa.

17/06/2026
17/06/2026

በሀረሪ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ

በሀረሪ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን በአግባቡ ለመስጠት ውጤታማ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተከናውነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መካከል በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ሞዴል ፈተና መሰጠቱን እንዲሁም ፈተናው ታትሞ ዝግጁ መደረጉን ጠቅሰዋል።

የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ክልል አቀፍ ፈተና ከነገ ሰኔ 11 ጀምሮ እስከ ሰኔ 12 2018 እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

በተለይም ተማሪዎችን ካለፈው ተሞክሮ በመነሳት በስነልቦና ከማዘጋጀት ጀምሮ የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ ለፈተናው የሚረዱ ቅድመ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሚሰጠው ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተናም 4614 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡

የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም ቢሮው ከመምህራን ማህበር፣ ከጤና ቢሮ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጭ ሌላ መገልገያ ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንም ነው ቢሮ ኃላፊው የገለጹት፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት ማንኛውም አይነት የጤና ችግር ቢያጋጥማቸው የህክምና እርዳታ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች መመደባቸውን ጠቁመው ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናውን እንዲሰሩ አሳስበዋል።

17/06/2026
17/06/2026

Address

Dire
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bekar yusuf posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category