Omega Mekurya

Omega Mekurya Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Omega Mekurya, Grocers, Adis Abeba, Addis Ababa.

04/02/2026
29/10/2025

በክልሉ አጠቃላይ የትምህርት ስልጠና ፈቃድ አግኝተው የሚቀሳቀሱ ተቋማት የትምህርትና ስልጠና ተግባርንን በአገር አቀፍ ደረጃ የወጡ እስታንዳርዶችን መሰረት አድርጎ ቁጥጥር የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ባለስልጣኑ አስታወቀ፤

ሆሳዕና ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በክልሉ አጠቃላይ የትምህርት ስልጠና ፈቃድ አግኝተው የሚቀሳቀሱ ተቋማት የትምህርትና ስልጠና ተግባርንን በአገር አቀፍ ደረጃ የወጡ እስታንዳርዶችን መሰረት አድርጎ ቁጥጥር የማድረግ ስራ እንደሚሰራ የክልሉ የትምህርት እና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ገለፀ፡፡

በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ራመቶ ቦካ እንደገለፁት ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያየ ስያሜ እየተንቀሳቀሰ መቆየቱን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ተግባሩን ለመጀመሪያ አሰፈላጊው ቅድመዝጅት ስራዎች እያጠናቀቀ እንደሆነ አስረድተዋል።

በክልሉ መንግስት በሚተዳደር መንግስታዊ ተቋም እንዲሁም በክልሉ ፈቃድ አግኝቶ በሚንቀሳቀስ ማንኛውም የግል ወይም መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት በሚተዳደር የትምህርት ተቋም የመቆጣጠር ስራ ባለስልጣኑ የተቋቋመለት ዓላማ ነው፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ሥራ ነፃና ገለልተኛ በሆነ አስፈፃሚ አካል በተደራጀ አኳኋን እንዲመራ በማድረግ የጥራት፣ የግምገማ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራን በመስራት ሀገራዊና ክልላዊ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቴፊኬት በመስጠትየትምህርትና ሥልጠና ጥራት ማረጋገጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ባለስልጣኑ በክልሉ በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ያለውን የትምህርትና ስልጠና የጥራት ቁጥጥር ተግባራትን እንደሚያናከውን የጠቀሱ ሲሆን የብቃትና ጥራት መከታተያና መገምገሚያ ስርዓት በመዘርጋት ስራው የሚመራበትን ስትራቴጂ በመንደፍ ተግባራዊ ያደርጋል፣ አፈፃጸሙንም ይቆጣጠራል፣ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድም አብራርተዋል።

በክልሉ መንግሥት፣ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት፣ ወይም በግል የትምህርትና ስልጠና ተቋም በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አግባብነቱና ጥራቱ የተጠበቀ አገልግሎት ስለመሰጠቱ ይቆጣጠራል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣኑ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስታውቀዋል።

በክልሉ ፈቃድ ሰጪ አካል ፈቃድ አግኝተው በሚንቀሳቀሱ የመንግስት፣ የግል ወይም መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ተቋቁመው የትምህርትና ስልጠና አገልግሎት በመስጠት ላይ በሚገኙ ተቋማት የተቋምና የፕሮግራም ግምገማ በማድረግ ከግብዓት፣ ከሂደት እና ከውጤት አኳያ የተቀመጡትን አገር አቀፍ የአግባብነትና የጥራት ስታንዳርዶች ማሟላታቸውን በጥብቅ እንደሚቆጣጠርም አክለዋል፡፡

ዋና ባለስልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ከግብዓት፣ ከሂደት እና ከውጤት አኳያ የተቀመጡትን ስታንዳርዶች ማሟላታቸውን የኢንስፔክሽን ሥራ በመስራት በተገኘው ውጤት መሠረትም የደረጃ ምደባ የመስጠት ፣ የማደስና የመሰረዝ መብት እንዳለዉም ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ፈቃድ በተሰጣቸው ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የተገኘን የትምህርት ማስረጃንና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቴፊኬት አስመልክቶ ለሚቀርብለት የማጣራት ወይም ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ህጋዊነትና ትክክለኛነት በማጣራት ባለስልጣኑ ማረጋገጫ እንደሚሰጥም አስታውቀዋል።

አቶ ራመቶ በክልሉ ፈቃድ ሰጪ አካል የተሰጣቸውን ፈቃድ፣ ስለእድሳት፣ ስለክፊያ ሁኔታ፣ ለተማሪዎች እና ለህብረተሰቡ በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም መረጃ መድረሱን ባለስልጣኑ አረጋግጦ ክትትል እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች አጣርቶ ባለስልጣኑ ወሳኔ እንደሚሰጥም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ለአብነትም የመዝጋት፣እዳ የመክፈል፣ የመዋሃድ፣ የመስፋፋት፣ትምህርት የሚሰጥበት ቦታን የመቀየር ወይም የባለቤትነት መብት የማስተላልፍ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ወዲያውኑ ለባለስልጣኑ የማሳወቅ መተግበራቸውን መቆጣጠርን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት የውስጥ ጥራትና ብቃት ማረጋገጥ ስርዓት መዘርጋታቸውንና መተግበራቸውን መቆጣጠር፣ ተጨማሪ ስልጠና ለመስጠት የሚፈልጉ ከሆነ ስልጠና የሚሰጥበትን ፕሮግራምና ጊዜ መቆጣጠር የባለስልጣኑ ተግባር መሆኑን አቶ ራመቶ አስታውቀዋል።

Address

Adis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Omega Mekurya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category