ማሜ Teravel agency

ማሜ Teravel agency MAME Travel
ዱባይ 🇦🇪
ባህሬን 🇧🇭
ጆርዳን 🇵🇸 ቤሩት በአጭር ቀን እንጨርሳለን 0947477487 ያናግሩን።

16/10/2025

ሁሉም ዜጋ ለብሔራዊ ጥቅም ዘብ መቆም አለበት
****************

ሁሉም ዜጋ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዘብ መቆም አለበት ሲሉ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህሩ አቶ ሙሉዓለም ኃ/ማሪያም ገለጹ።

አቶ ሙሉዓለም ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በተለያዩ ጊዜያት የምታከናውናቸው ተግባራት እንዳሉ አንስተዋል።

አክለውም፥ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ያነሳችው የባሕር በር ጥያቄ የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ሁሉም ዜጋ በአንድነት መቆም እንዳለበት አመላክተዋል።

በሜሮን ንብረት

15/09/2025

ውጤቴን ስሰማ በጣም ደንግጫለሁ፦ ተማሪ ካሊድ በሽር
*********************************************

የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።

ተማሪ ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከ600 ነጥቦች 9 ብቻ በማጣት ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው።

ተማሪ ካሊድ በሽር

እንግሊዘኛ 96🔥
ሒሳብ 100🔥
ፊዚክስ 100🔥
ኬሚስትሪ 98🔥
ባዮሎጂ 99🔥
አፕቲትዩድ 98🔥 ውጤት አስመዝግቧል።

"ውጤቴን ስሰማ በጣም ደንግጫለሁ" የሚለው ተማሪ ካሊድ፣ "ማንኛውም ተማሪ ዓላማ ሊኖረው ይገባል፤ ለዓላማ መድከም ካለ ከድካም በኋላ ጥሩ ውጤት ይመጣል" ሲል ገልጿል።

በሃይማኖት ከበደ

14/09/2025

ቡርኪና ፋሶ ለሁሉም የአፍሪካ ተጓዦች ከቪዛ ነፃ ጉዞን ፈቀደች

| ቡርኪና ፋሶ ለሁሉም የአፍሪካ ተጓዦች ከቪዛ ነፃ ወደ ሃገሪቷ መግባት የሚያስችል ፖሊሲን አስተዋውቃለች፡፡

ሰዎች እና ሸቀጦች ወደ ሀገሪቱ የሚገቡበትን ሁኔታ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ እና ቃጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር በማለም የተወሰነው ይህ ውሳኔ፤ ተጓዦች ጉዟቸውን ለማፀደቅ በበይነ መረብ በማመልከት ያለ ምንም የቪዛ ክፍያ ወደ ሃገሪቱ ለመግባት የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡

በዚህም ሃገሪቱ ለአፍሪካ ሃገራት የጉዞ መስፈርቶችን ካቀለሉ ከነ ጋና፣ ሩዋንዳ እና ኬንያ ጋር እንድትሰለፍ አስችሏታል፡፡

ውሳኔው ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ ስልጣን ላይ ያሉትን የሃገሪቱ ወታደራዊ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬን የፓን አፍሪካኒዝም ሃሳብ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህ ውሳኔ የሃገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ እና ባህሏንም በማስተዋወቅ ዓለም አቀፍ ትኩረትንም እንድትስብ ያደርጋል ተብሎ ታምኗል፡፡

ሆኖም የሃገሪቱ ውሳኔ ከጎረቤት ሃገሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ስለማጠናከሩ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻልም ዘገባው አመላክቷል፡፡

ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ሌላ ህብረት ለመፍጠር የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ለቀው መውጣታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

AMN

28/08/2025

Address

Ethiopai
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማሜ Teravel agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category