01/08/2026
"ወያኔ 'በምዕራብ ትግራይ ብልፅግና አጥቅቶኛል' ብሎ መግለጫ አውጥቷል ሲባል ሰምቼ በጣም ነው የገረመኝ።
እስኪ አስቡት፤ ትናንትና 'የምዕራብ ትግራይ ሉዓላዊ ግዛታችን ተይዞብናል፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት አልተከበረም' ሲል የነበረው ራሱ ህወሃት አልነበረም እንዴ? ታዲያ አሁን ደግሞ በየትኛው ሒሳብ ነው 'በምዕራብ ትግራይ ውጊያ ተከፈተብኝ' ሊል የቻለው? ምዕራብ ትግራይ የሚባለው እኮ በአሁኑ ሰዓት በፌደራል መንግስት እጅ ያለ ቦታ ነው። ወይስ ሱዳን ተሻግሮ ሌላ ምዕራብ ትግራይ አለ እንዴ?
እውነቱን ለመናገር ይህን እርስ በርሱ የሚጋጭ መግለጫ ስሰማ ህወሃቶች በእርግጥም አብደዋል ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስኩት። ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ሚዛናቸውና ስሌታቸው ፈጽሞ ጠፍቶባቸዋል። ቢያንስ ቢያንስ እንኳን 'ይህ እኮ ሎጂክ የለውም፣ ህዝብ ይታዘበናል' ብሎ የሚነግራቸው አንድ ጤናማ አማካሪ እንዴት ያጣሉ?"