24/08/2026
የዘመን አቆጣጠር ተሻሻለ‼ ከዓ.ም👉ኢ.አ
የሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ዋና ዋና ውሳኔዎችና ያልተቋጩ አጀንዳዎች
ለ38 ቀናት ሲካሄድ የቆየውና 400 ምክረ-ሀሳቦች የቀረቡበት ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ መጠናቀቁ ተገለጸ። ከተስማሙባቸውና በልዩነት ከተያዙት መካከል ዋና ዋናዎቹ፦
✅ ስምምነት የተደረገባቸው፦
📌የዘመን አቆጣጠር፦ «ዓመተ ምህረት (ዓ.ም)» የሚለው ቀርቶ «የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ)» እንዲባል፤ «ሒጅራም» እንደ ካላንደር እንዲካተት።
📌አንቀጽ 39፦ «እስከ መገንጠል» የሚለው ድንጋጌ እንዲሰረዝ።
📌የስራ ቋንቋ፦ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ እና አፋርኛ የፌዴራል የስራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ (ብሔራዊ ቋንቋ ግን ለጊዜው አያስፈልግም ተብሏል)።
📌ውህድ ማንነት፦ ከሁለት በላይ ብሔሮች የተወለዱ ዜጎች «በውህድ ማንነት» እውቅና እንዲሰጣቸው።
የመንግስት አወቃቀር፦ «ፌዴራላዊ» ሆኖ እንዲቀጥል።
❓ በልዩነት የተያዙ (ያልተወሰኑ) 4 ነጥቦች፦
📌የአዲስ አበባ ጉዳይ፦ የፌዴራል ተጠሪነቷና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ ከተማነት/መብት ሁኔታ - አሁን ባለበት ነው።
📌የመንግስት ቅርጽ፦ «ፓርላሜንታዊ» ወይስ «ፕሬዚዳንታዊ» ይሁን የሚለው።
📌ሰንደቅ ዓላማ፦ አሁን ያለው አርማ ይ ቀጥል ወይስ በሌላ ይተካ።
📌የፌዴሬሽን ምክር ቤት፦ አባላቱ በህዝብ በቀጥታ ይመረጡ ወይስ በክልሎች።
📌 ኮሚሽኑ በልዩነት የተያዙትን አደራጅቶ ውሳኔ ለሚሰጠው አካል እንደሚያቀርብ አስታውቋል።(ቲክቫህኢትዮጵያ)
Wasu Mohammed - Mereja