Lafee Galata dhabde

Lafee Galata dhabde Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lafee Galata dhabde, Grocers, Liiban. Dhuungoo, Dila.

30/07/2026
25/07/2026
*ህወሓት፣ ፋኖ እና ሸኔ*ሶስቱም የሚያመሳስላቸው ዋና ዋና ተግባራት ንጹሃን ሰዎችን መግ*ደል፣ ሰዎችን ማገት፣ ገንዘብ መጠየቅ፣ የፍርሃት ድባብ መፍጠር እና በኃይል የፖለቲካ ወይም ሌላ ዓላማ...
24/07/2026

*ህወሓት፣ ፋኖ እና ሸኔ*
ሶስቱም የሚያመሳስላቸው ዋና ዋና ተግባራት ንጹሃን ሰዎችን መግ*ደል፣ ሰዎችን ማገት፣ ገንዘብ መጠየቅ፣ የፍርሃት ድባብ መፍጠር እና በኃይል የፖለቲካ ወይም ሌላ ዓላማ ለማስፈጸም መሞከር ናቸው እነዚህ ደግሞ የአሸባሪዎች መገለጫ እና ሶስቱንም ቡድኖች የሚያመሳስላቸው ዋና ተግባር ናቸው።

ዘላቂ ሰላም የሚገነባው በኃይል እና በፍርሃት ሳይሆን በሕግ የበላይነት፣ በፍትሕ፣ በተጠያቂነት እና በሰላማዊ መፍትሄዎች ነው። በማንኛውም ወገን የሚፈጸሙ በንጹሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በግልጽ እንደምናውቀው ከእነዚህ ሶስት አካላት ይመነጫል። የሀገር መረጋጋትና የዜጎች ደህንነት የሚረጋገጠው ሁሉም አካላት የሰብዓዊነትን እና የሕግን የበላይነትን ሲያከብሩ ነው።

🚨 የጥፋት ጥምረትና የግብዝነት ፖለቲካ፡ የኢህአፓ እና የህወሓት አደገኛ ሸፍጥ! 🚨በታሪክ አጋጣሚ ሀገርንና ትውልድን የፈጁ ኃይሎች ዛሬም እንደገና የሰላም ተቆርቋሪ መስለው ብቅ ብለዋል!ኢህአ...
23/07/2026

🚨 የጥፋት ጥምረትና የግብዝነት ፖለቲካ፡ የኢህአፓ እና የህወሓት አደገኛ ሸፍጥ! 🚨

በታሪክ አጋጣሚ ሀገርንና ትውልድን የፈጁ ኃይሎች ዛሬም እንደገና የሰላም ተቆርቋሪ መስለው ብቅ ብለዋል!

ኢህአፓ «መንግሥት በትግራይ ጦርነት ሊቀሰቅስ ነው» በማለት የሚያሰማው የሐሰት ጩኸት፣ ከህወሓት ጋር ያለውን አጥፊና የሴራ ፖለቲካ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ ነው። ሁለቱም ቡድኖች በታሪካቸው በጽንፈኝነት፣ በዜሮ ድምር እሳቤ እና የጥፋት መንገድ የተከተሉ የትርምስና የውድመት ምንጮች ናቸው።

ትናንት ትውልድ ያስፈጀው ኢህአፓ፣ ዛሬ ሀገር ካደማው ህወሓት ጋር ተሻርኮ የሚያሰማው የግብዝነት አቋም የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሽፋን በማድረግ ሀገርን ዳግም ወደ ጦርነት እና ግጭት ለመክተት የተሸረበ ትልቅ የፖለቲካ ሸፍጥ ነው!

⚠️ ከታሪክ ያልተማረ የጥፋት አካሄድ፦ የኢህአፓ ታሪካዊ ስህተት

ኢህአፓ በ1960ዎቹ በደርግ መንግሥት ላይ የ«ነጭ ሽብር» አዋጅ በመክፈት ሀገሪቱን የማያባራ ሰቆቃና ሽብር ውስጥ እንድትገባ አድርጓል። ድርጊቱ ለሀገራችን ያተረፈው ጥፋት በጥቂቱ፦
የምሁራንና የወጣቶች እልቂት፣ የማይሽር የታሪክ ቁስል፣የመከራ ጥሪ አስከትላል።

📢 የዛሬው ስጋትና ጥሪያችን!
አሁንም ባለው የፖለቲካ ሁኔታ፣ ከትላንቱ የጥፋት ታሪካቸው ያልተማሩና በህዝብ ሰላምና ደህንነት ላይ አዲስ ችግር ለመፍጠርና ሁከት ለማስነሳት የተሰለፉ አካላት አሉ!

❌ ከታሪክ መማር ያቃተው፣ ሀገርንና ህዝብን ለአደጋ የሚያጋልጥ ይህ ኋላቀር አስተሳሰብ ዳግም በሀገራችን ቦታ ሊኖረው አይገባም!

👉 የሀገራችንን ሰላም የሚረብሹና የሴራ ፖለቲካቸውን የሚያስፋፉ ማናቸውንም ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች ነቅተን ልንታገላቸውና በጋራ ልንቆምባቸው ይገባል!

27/06/2026

Address

Liiban. Dhuungoo
Dila

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafee Galata dhabde posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category