WAHEL Secondary school

WAHEL Secondary school Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from WAHEL Secondary school, Grocers, Wahel, Dire Dawa.

ኢመማ 13ኛውን  የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ አካሄደ  የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከሚያከናውናቸው ትምህርት ነክ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱ የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ...
29/06/2026

ኢመማ 13ኛውን የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ አካሄደ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከሚያከናውናቸው ትምህርት ነክ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱ የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ ማካሔድ ነው፡፡ በመሆኑም ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የማህበሩ የጋራ ህንፃ ላይ የተለያዩ ተባባሪ አካላት በተገኙበት ሰኔ 18/2018 ዓ/ም 13ኛውን የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡
በኢፌደሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ደኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ፣ የሲዳማ ክልል ምክትል ር/መስተዳድር እና የትምህረት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ በየነ በራሳ፣ የክልሎች፤ ከተማ አስተዳደሮችና የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር አመራሮች፣ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፤ትምህርት ኮሌጅ፤ከከተማው በ1ኛ ደረጃ፣ በ2ኛ ደረጃ እንዲሁም ከቴ/ሙያ ኮሌጅ የተውጣጡ መምህራን በኮንፈረንሱ ታድመዋል።

የኢመማ ፕሬዚዳንትና በትምህርት ዓለም አቀፍ አፍሪካን በመወከል የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ማህበሩ ከመምህራን መብትና ጥቅም ጎን ለጎን በትምህርት ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቅሰው ይህን ኮንፈረንስ ልዩ የሚያደርገው በማህበሩ ህንጻ የተካሔደ የመጀመሪያው ኮንፈረንስ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ምክትል ር/መስተዳድር እና የትምህረት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ በየነ በራሳም በዚሁ ኮንፍረንስ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ኢመማ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ አንጋፋ ማህበር መሆኑ ብቻም ሳይሆን ሀገራዊ ፋይዳና ትርጉም ያላቸውን ተግባራት በብቃት እየተወጣ ያለ ማህበር በመሆኑ በዚህ ኮንፈረንስ የሚቀርቡ የጥናት ውጤቶች ምክረ ሀሳብን እንደ ክልላችን ወስደን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ኮንፈረንሱን በንግግር ከከፈቱት መካከል አንዷ ሲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢመማ ጋር በትብብር በርካታ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ተቋርጦ የነበረው የመምህራን የክረምት የሥራ ላይ ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ሥልጠና በያዝነው ክረምት እንደሚጀምር ተናግረው የተለያዩ የመምህራን የጥቅማ ጥቅም ሰነዶችን ከማሀበሩ ጋር እየሰራን ነው በማለት በኮንፍረንሱ የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ተናግረዋል፡፡

ከወለዲያ ዩኒቨርሲቲ፤ከኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲተ፤ ከሚዘን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በግጭት ዙሪያ፣ ቴክኖሎጂን አካቶ ማስተማር ላይ፣ በ12ኛ ክፍል የተማሪ ውጤት ፣በርዕሰ-መምህራን የአመራር ዘይቤ እና በከፍተኛ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት ላይ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለውይይት ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደረጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የጋራ ውይይት ተደርጎ ኮንፈረንሱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ ይህ ኮንፈረንስ የተሳካ እንዲሆን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ላደረጉት ድጋፍ ኢመማ በመምህራን ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

20/03/2026
በድሬዳዋ በትምህርት ቤቶች የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችሉ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገድሬዳዋ | የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም - የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከ UN-H...
20/02/2026

በድሬዳዋ በትምህርት ቤቶች የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችሉ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ድሬዳዋ | የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም - የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከ UN-Habitat Ethiopia እና ከድሬዳዋ ከተማ ጽዳት፣ ውበትና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አወጋገድ እና መልሶ መጠቀምን (Recycling) የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በጃፓን መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነው ይህ መርሃ ግብር "የእኔ ቆሻሻ የሁላችንም ሀብት ነው" በሚል መሪ ቃል በትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ተከናውኗል።

የድጋፉና የሥልጠናው ዋና ዓላማ ተማሪዎች እና የትምህርት ማህበረሰቡ ስለ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ሳይንሳዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ፣ ትምህርት ቤቶችን ለትምህርት ምቹ፣ ጽዱ እና አረንጓዴ ማድረግ ነው።

በተጨማሪም ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ቆሻሻን የመቀነስ፣ የመለየት እና መልሶ የመጠቀም (Recycling) ባህልን እንዲያዳብሩ በማገዝ፣ በቀጣይ ለከተማዋ የፅዳት እና ውበት ስራ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል።

በዕለቱ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ ድጋፉን ከ UN-Habitat Ethiopia የድሬዳዋ ፕሮጀክት ማናጀር ከአቶ ፍጹም ፀጋዬ የቁሳቁስ ድጋፉን ተረክበዋል።

አቶ አቡበከር በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ትምህርት ቤቶች የተደረገላቸውን ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ እንደሚያውሉት አረጋግጠው፣ ለተደረገው ድጋፍም በቢሮው እና በትምህርት ቤቶቹ ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቀጣይነት ደግሞ የአካባቢ ጥበቃ ማህበር ክለብ አባላቶች፣ የትምህርታዊ ጉብኝት በድሬዳዋ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች እና እንደዚሁም ደግሞ ፕላስቲክ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውሉ ፋብሪካዎችን የጉብኝት መርሃ ግብር እደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በድሬዳዋ የተማሪዎች ምገባ መርሐ ግብር ትምህርት እንዳይቋረጥና ጥራት እንዲረጋገጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸየካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም — የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በኢኮኖሚ...
19/02/2026

በድሬዳዋ የተማሪዎች ምገባ መርሐ ግብር ትምህርት እንዳይቋረጥና ጥራት እንዲረጋገጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ

የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም — የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በገንደ ገራዳ ትምህርት ቤት 41ኛው ዙር የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። ይህ የምገባ ፕሮግራም 25 ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ጨምሮ በአጠቃላይ 150 ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል።

በምገባ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ እንደገለጹት፤ መሰል የምገባ መርሐ ግብሮች ተማሪዎች በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይርቁ እና በትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ በማስቻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።

መርሃ ግብሩ እውን እንዲሆን ከ‘ዎች ኤንድ ፕሬይ ሚኒስትሪንግ ኢንተርናሽናል’ (Watch and Pray Ministry International) እና ከ‘ኤስ ኤን ቪ’ (SNV) በተገኘ ድጋፍ እንዲሁም ከ‘ድሬ ፍሬዎች በጎ አድራጎት ማህበር’ ጋር በመተባበር የተከናወነ መሆኑ ገልጸዋል።

በአስተዳደሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምቹ የመማር ማስተማር አካባቢን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት፣ የምገባ መርሐ ግብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ አቡበከር አዶሽ አረጋግጠዋል።

09/02/2026

Sand Erosion feature

03/02/2026

Address

Wahel
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WAHEL Secondary school posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category