19/08/2026
መደመር የደረመሠው የጠላት ካምፕና የባንዳዎች እሪታ
በምስራቅ አፍሪካና በታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የካይሮ እጅ ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረጉ እኩይ ስትራቴጂዎችን በመተለም ይታወቃል። የዓባይ ወንዝ ዋነኛ ምንጭና የተፈጥሮ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን ማዳከም፣ የውስጥ ግጭቶችን ማበረታት እና በቀይ ባሕር እንዲሁም በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ላይ ያላትን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ፍላጎት ማደናቀፍ የግብፅ የረጅም ጊዜ የውጭ ፖሊሲ መሠረት ሆኖ ቆይቷል።
ግብፅ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በወታደራዊ ኃይል ኢትዮጵያን በግልጽ ወርራ ለመቆጣጠር ባደረገችው ሙከራ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 1875 በጉንደት እንዲሁም 1876 በጉራዕ ጦርነቶች በኢትዮጵያ አሳፋሪ ሽንፈት አስተናግዳለች ። ከዚህ የቀጥታ ወታደራዊ ሽንፈት በኋላ ካይሮ ኢትዮጵያን በግልጽ ጦርነት ማንበርከክ እንደማትችል ተረድታ ወደ ተዘዋዋሪ የውስጥ ሴራና የእጅ-አዙር ጦርነት ተሸጋግራለች።
ካይሮ ኢትዮጵያ ጠንካራና የበለፀገች ሀገር ሆና ከተነሳች በዓባይ ውሃ ላይ ያላትን አጠቃላይ የበላይነት እንደምታጣ ስለሚሰማት፣ የሀገሪቱን እድገት የማደናቀፍና በጂኦፖለቲካው መስክ ወደብ አልባ አድርጎ የመዝጋት ስትራቴጂን ለዘመናት ስትከተል ኖራለች። ይህም የታሪክ እውነታ ከትላንት እስከ ዛሬ በስውርና በግልጽ የሴራ መረቦች ተሸርቦ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ሲፈታተን የኖረ መራራ እውነት ነው።
የቡትሮስ ብትሮስ ጋሊ የዲፕሎማሲ ሽፋን እና ኢትዮጵያን ወደብ የማሳጣት ሴራ
በታሪክ አጋጣሚዎች እንደምናየው፣ በግብፅ የፖለቲካ ልሂቃን የታቀዱ ሴራዎች በዓለም አቀፍ መድረኮች እንዴት ተግባራዊ እንደሆኑ አንደኛው ማሳያ የቀድሞው ግብፃዊ ዲፕሎማት ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ አካሄድ ነው።
ሙሉ ጽሑፉን 👉 https://www.ena.et/web/amh/w/amh_9422515