04/07/2026
📢 ደረሰ! ደረሰ!! ደረሰ!!!
እንኳን ለ2019 በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት በሰላም አደረሳችሁ፤
የተከበራችሁ በዌራ ዲጆ ወረደ የምትገኙ ታማኝ ግብር ከፋይ ነጋዴዎቻችን በሙሉ፦
የ2019 በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት ከፊታችን ረቡዕ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በወረዳችን በአንድ ማእከል በበሸኖ ከተማ የኦን-ላይን አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ላይ ይሰጣል።
ስለሆነም የተከበራችሁ ግብር ከፋይ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ አገልግሎቱን ለማግኘት
በበሸኖ ከተማ በሚገኘው የንግድና ገበያ ልማት ጽሕፈትቤት በመቅረብ የንግድ ስራ ፈቃዳችሁን በወቅቱ በማሳደስ ንግድዎን በሕጋዊነት ያስቀጥሉ።
የተከበራችሁ ታማኝ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ለፈቃድ እድሳት ሲመጡ የሚያሟሏቸው ቅድመ ሁኔታዎች ወይም መስፈርቶች፦
✔ በእጃችሁ ያለዉን ኦሪጅናል የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
✔ የታደሰ ወይም ዲጂታል መታወቂያ፤
✔ ከገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ የገቢ ክሊራንስ፤ በክሊራንሱም የ2018 በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ትርፍ ግብር መከፈሉን እና ለ2019 በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ፈቃዱ እንዲታደስ ተቃውሞ እንደሌለ የሚያረጋግጥ መሆን አለበት፤
✔ ለፈቃድ እድሳት የተወሰነውን 102 (አንድ መቶ ሁለት) ብር የአገልግሎት ክፍያ፤
የዌራ ዲጆ ወረደ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከይሩ እ/ሁሴን "የንግድ ፈቃድዎን በወቅቱ ማደስ ሕጋዊ ግዴታ ብቻም ሳይሆን ለንግድ ቀጣይነት፣ ለተሻለ አገልግሎት እና ለወረደችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ነጋዴዎች ለእድሳት የሚያስፈልጉትን ሰነዶች በቅድሚያ በማሟላት በተጠቀሰዉ ጊዜ ውስጥ ቀርባችሁ ፈቃዳችሁን በወቅቱ እንዲታሳድሱ በማለት ጥሪ አቅርቧል።
ለዚህም ተቋማችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ አገልግሎት ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ማሳሰቢያ
=======
↘️ ሁሉም ነጋዴዎች ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች አሟልታችሁ በወቅቱ በመቅረብ አገልግሎቱን እንዲያገኙ በአክብሮት እናሳስባለን!!
"ፈቃድዎን በወቅቱ ያድሱ፤ ንግድዎን በሕጋዊነት ያስቀጥሉ!"
የዌራ ዲጆ ወረደ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ።