Nuso Deriyaa

Nuso Deriyaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nuso Deriyaa, Grocers, Wolaita, Sodo.

19/04/2025

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ተ/ሀይማኖት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልክት እንደሚከተለው ይቀርባል ።

አቶ ፀጋዬ በእንኳን አደረሳችሁ መልክታቸው
የደህንነታችን ቤዛ የሆነው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ሃጢአት ማስተሰርያ ሲል፣ ሥጋዉን ቆርሶ፣ ክቡር ደሙን አፍሦ፣ ሞትን ድል አድረጎ የተነሳበትን የትንሳኤውን በዓል እንኳን በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን ያሉት ኃላፊው የትንሣኤ በዓል በክርስቶስ ፍቅር የሰው ልጅ ከሃጢያት ባርነት ነፃ የወጣበት ሰለሆነ እኛም ትንሳኤ ብርሃኑን ስናከብር ጥላቻን በመተው ፍቅርን በመስበክ በአንድነት ሁነን የተቸገሩትን በማሰብ እና በማገዝ መሆን እንዳለበት በመልዕክታቸው ተናግረዋል።

ትንሳኤ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰዉ ልጆች ፍቅር መከራውን ሁሉ በፅናት አልፎ፣ ዓመተ ኩነኔን ደምስሶ፣ የሰው ልጅን የዕዳ ደብዳቤ ቀዳዶ፣ ሲኦልን መዝብሮ፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት በዓል ነው በማለት የገለፁት አቶ ፀጋዬ ።

ይህ በዓል እንደሌሎች መንፈሳዊ በዓላት ለመታሰቢያነት እናከብረው ዘንድ የታዘዝነው ብቻ አይደለም፣ ይልቁንም ተምሳሌትነቱን ተከትለን እንድንፈፅመው ሲሉ ገልጸዋል!

በትንሳኤ ብርሃን ድል የተነሳው ጨልሞ የነበረው ተስፋ ነው ያየነው ትንሳኤ የመከባበር፣ የመታዘዝ፣ አንዱ ለሌላው የመስጠት፣ የማካፈል አብሮ መብላትን ለትውልድ ያስተማረ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችንን የሚያጎሉ እጅግ ብዙ ዕድሎች አሉን! ያሉት አቶ ፀጋዬ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት የተጋመደና የተሰናሰለ የጋራ ማንነት ያለን ኩሩ ህዝቦች ነን! ለዚህም እንደ ርግብ ንጹህ የሆነ ልብ ሊኖረን ይገባል ብለዋል ፡፡

የአገራችን ትንሳኤም እውን የሚሆነው በፍቅር፣ በይቅር ባይነት፣ አንዳችን ስለሌላችን ዋጋ በመክፈል፤ ከልብ በመነጨ መደጋገፍና አብሮነት ብቻ ነው ሲሉም አብራርተዋል።

በመጨረሻም አቶ ፀጋዬ በአስተላለፉት መልክት ሁላችንም በምንፈጽመው መልካም ተግባር አገራችን ትሻገራለችና ሁልጊዜም ቢሆን አገረን በማሻገርና የነገን ብርሃን እውን ለማድረግ የሚያስችል የመንፈስ ዝግጅት ሊኖረን ይገባል ስሉ የተናገሩት የመንግሥት ዋና ተጠሪው የዘንድሮው የትንሳኤ በዓል የቆዩ የተሳሳቱ ትርክቶችን በማረም፣ የገዥ ትርክት በማብዛት፣ የለማችና የበለጸገች ሀገርን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እኔነትን ሳይሆን እኛነትን መልመድ የግድ በማድረግ ፓርቲያችን ብልጽግና ላለፉት የለውጥ ዓመታት ህልም የመሰሉ በርካታ ድንቅ ስራዎች ማስመዝገብ የቻለ እና ነገን አስቦ ዛሬ ላይ ህዝብን አስተባብሮ እየሰራ የሚገኝ ጠንካራ ፓርቲ መሆኑን እጅ ለእጅ በመያያዝ እናስቀጥል ብዋል።

መልካም የትንሣኤ በዓል

አቶ ፀጋዬ ተ/ሀይማኖት
የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ
ሚያዝያ 11/2017
ወላይታ ሶዶ፣

17/04/2025

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ በከተማው በድምቀት የሚከበረውን የስቅለትና የትንሳኤ በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ የቅደመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አሰታወቀ።

******
ወላይታ ሶዶ ሚያዝያ 9/2017ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ በከተማው በድምቀት የሚከበረውን የስቅለትና የትንሳኤ በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ የቅደመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቋል ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ በከተማው የሚከበረውን የስቅለትና የትንሳኤ በዓል በማስመልከት መላው የከተማችንን የክርስትና እምነት ተከታዩች እንኳን አደረሳችሁ ያለው የከተማው ፖሊስ በዓሉን ያለምንም ስጋት በሠላም እንዲጠናቀቅ ሙሉ የቅደመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ መልክት አስተላልፏል ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ በከተማችን በድምቀት የሚከበረውን የስቅለትና የትንሳኤ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ወደ የቤተሰቦቻቸው የሚጡ ሰዎች ወላይታ ሶዶ እንደሚገቡ ያስታወሱት አዛዡ የንግድ፣የትራፊክ ፈሰቶች፣ በዛው ልክ የሚጠናከሩበት፣በመሆኑ እነዚህ የበዓል ሁኔታዎች ምክንያት በማድረግ ለስርቆት እና ለሌብነት እራሳቸውን የሚያዘጋጁ ግለሰቦች መኖራቸውን ያስታወሱት አዛዡ ወቅቱን በመረዳት እና በመገንዘብ ህብረተሰቡ በጥንቃቄ ግብይትና እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅረበዋል ።

ይሄ በመሆኑም የከተማ የፖሊስ በዓሉ በሠላም እንዲጠናቀቅ 24 ሰዓት የፖትሮል ቅኝት እና በሞንተርበ የታገዘ የጥንቃቄ ምልክቶችን በመሰጠት እንዲሁም በሰባቱም ቀበሊያት የፖሊስ የማህበረሰብ ቅደመ ጥንቃቄ ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን በማስረዳት የስቅለትና የትንሳኤ በሰላም እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

ማንኛውም ጥቆማ ሲኖር የከተማ ፖሊስ የኢንተለጀንስ እና የመረጃ ስልኮች 0465510146 ይደውሉ

17/04/2025
08/04/2025
ጊፋታ በዩኒስኮ በታህሳስ ወር 2025 በሚካሄደው 20ኛ ጉባኤ በኮሚቴው ከሚገመገሙ ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኗል። የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጀት(ዩኒስኮ)ጊፋታን በ...
08/04/2025

ጊፋታ በዩኒስኮ በታህሳስ ወር 2025 በሚካሄደው 20ኛ ጉባኤ በኮሚቴው ከሚገመገሙ ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኗል።

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጀት(ዩኒስኮ)ጊፋታን በታህሳስ ወር 2025 በሚያካሄደው 20ኛ ጉባኤ በኮሚቴው ከሚገመገሙ ቅርሶች መካከል አንዱ ማድረጉን በድረ-ገጹ ይፋ አድርጓል።

''ጊፋታ'' በዎላይታ ብሔር ዘንድ ከአሮጌ ወደ አዲስ ዘመን መሻገርን፣ ከአሮጌው ወደ አዲስ መንፈስ መሻገርን የሚያመለክት በኩር ወር ነው።

የዎላይታ ባህል አዋቂዎችና ጥበበኞች የጨረቃንና የፀሐይ ዑደት ስሌት መሠረት በማድረግ ማኅበረሰቡ ከክረምት ወደ በጋ፣ ከጭጋጋማ ድባብ ወደ ብርሃናማ ዓውድ፣ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲስ ዓመት የሚደረገውን ሽግግር የሚያበስሩበት በዓል ነው ጊፋታ።

ይህንን በዓል ዩኒስኮ በማይደሰስ የሰው ልጀ ወካይ ቅርስነት ለመመዝገብ በታህሳስ 2025 በኮሚቴው ከሚታዩት መካከል ማስቀመጡን በድረ-ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።

ለዚህ ፌስቡክ ገጽ አዲስ ከሆኑ በዚህ ዎንታ ሚዲያ ውስጥ በመግባት follow የሚለውን አንድ ጊዜ በመንካት አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ።

  ኢትዮጵያ የባህል ዕሴቿን እና ኪናዊ ፀጋዎቿን ለብሪክስ አባል ሀገራት ልታስተዋውቅ ነው   | “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ህዝብ ለህዝብ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ኢትዩጵያ ላይ ያሉ ቱባ ባ...
08/04/2025



ኢትዮጵያ የባህል ዕሴቿን እና ኪናዊ ፀጋዎቿን ለብሪክስ አባል ሀገራት ልታስተዋውቅ ነው

| “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ህዝብ ለህዝብ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ኢትዩጵያ ላይ ያሉ ቱባ ባህላዊ ዕሴቶችን፣ ኪናዊ ፀጋዎችን እንዲሁም የፈጠራ ምርቶችን በመጠቀም ከኢትዩጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች በተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ለማቅረብ ዝግጅት ጀምራለች፡፡

ኢትዩጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በዲፕሎማሲው መስክ ከምትሰራቸው ስራዎች አንዱ የባህልና የኪነ ጥበብ ዲፕሎማሲ እንደመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ልክ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህንን ዝግጂት ለማቅረብም የሚያስችል የውል ስምምነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር ተፈራርሟል፡፡

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ
Ministry of Culture & Sport-Ethiopia

Address

Wolaita
Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nuso Deriyaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category