Garaa Nama Nyaata

Garaa Nama Nyaata Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Garaa Nama Nyaata, Grocers, Delhi.

09/07/2026

ኢትዮጵያ በምክክር ችግሮቿን ትፈታለት ! አዲስ አበባም እንደ መዲናነቷ ታዳሚያንን ተቀብላ በብቃት ለማስተናገድ ዝግጅት አድርጋለች!

ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሊካሄድ 6 ቀናት ብቻ ቀሩት!

የሀሳብ የበላይነት ሲከበር ፣ መደማመጥ ሲዳብር ሀሳብ አልባነት ቦታ ያጣል። ኢትዮጵያ በብሔራዊ ምክክር በኩል የውይይት ባህልን ለመገንባት ብርቱ ጥረት ጀምራለች።

ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍ ፣ ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ ህዝባችን አሉኝ የሚላቸውን ጥያቄዎች በሰለጠነ መንገድ አቅርቧል።

በህዝብ የተነሱ ሁሉንም ጥያቄዎች ሲያሰባስብ የቆየው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ስምንት ጥቅል አጀንዳዎችን በመጠመር ሀምሌ 8 / 2018 ዓ.ም ሁሉም የህበረተሰብ ክፍል በተወካዮቹ በኩል የሚሳተፍበትን የምክክር መድረክ ደግሷል።

የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት፣ የአፍሪካ ኩራት፣ የዲፕሎማቲክ ስዕበት የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባም ከሁሉም የኢትዮጵያ ወረዳዎች የሚመጡ እንግዶችን መቀበል ጀምራለች፡፡

ይህ የምክክር እና የውይይት አካሄድ አሻጋሪ ነው ። ይህ አካሄድ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞን በፅኑ አለት ላይ የሚገነባ ብቸኛው መንገድ ነው።

የሀገራችን ውስብስብ ችግሮች የሚቀረፉት በዳበረ የውይይት ባህል ነው ፤ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሁሉንም እያሳተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ምክክር ደግሞ አንደኛው ቁልፍ ነው።

ለሀገራችን ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀውን ይህ እድል የሰመረ እንዲሆን ሁሉም ዜጋ የድርሻው ጠጠር ሊያሳርፍ ይገባል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

09/07/2026

ሀገራዊ ምክክር፤ ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ

ኢትዮጵያችን በረጅም ታሪኳ ልብን በኩራት የሚሞሉ በርካታ አንጸባራቂ ድሎችን አስመዝግባለች፤ በተመሳሳይ ደግሞ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ውጣ ውረዶችንም አሳልፋለች። የፖለቲካ ልዩነቶች፣ የታሪክ አተረጓጎም ሽኩቻዎች፣ የማንነት ጥያቄዎችና የፍትሕ መጓደሎች ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡና ማህበራዊ ትስስራችንን የፈተኑ ከባድ ጉዳዮች ናቸው። ዛሬ ላይ ሆነን ስናስበው፣ እነዚህን ውስብስብና ስር የሰደዱ ችግሮች በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም እርስ በርስ በመወነጃጀል ልንፈታቸው እንደማንችል በግልፅ ተረድተናል። ይልቁንም፣ በመደማመጥ፣ በውይይትና በመግባባት አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት የጀመርነው ሀገራዊ የምክክር ጉዞ ለሀገራችን አዲስ የብርሃን ወጋገን ነው።

ሐምሌ 8 በይፋ የሚጀመረው ሀገራዊ ምክክርም ከዚህ እውነታ የሚመነጭ ነው። ይህ መድረክ ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍል የመጡ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው የልባቸውን የሚነጋገሩበት፣ ስጋትና ተስፋቸውን የሚያካፍሉበት ትልቅ የጋራ አላማ ያነገበ ውይይት ነው። ከመላው ሀገሪቱ፣ ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ጀምሮ በከፍተኛ ተሳትፎ የተሰባሰቡት አጀንዳዎች የጥቂቶችን ድምፅ ብቻ ሳይሆን፣ የብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ የልብ ትርታና እውነተኛ ጥያቄ የሚያንፀባርቁ ናቸው። ይህ ሂደት እያንዳንዱ ዜጋ "ድምፄ ተሰምቷል" ብሎ እንዲያምንና ለመፍትሄውም የራሱን ጡብ እንዲያኖር የሚያስችል ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።

ይህን ጉዞ ስንጀምር፣ የብልፅግና ፓርቲ ከመነሻው ያነገበውን "መደመር" የተሰኘ መሪ ዕሳቤ ማስታወስ ተገቢ ነው። ልዩነቶችን በግጭትና በመጠላለፍ ሳይሆን፣ በውይይትና በወንድማማችነት መንፈስ ለመፍታት የተያዘው ይህ ፖለቲካዊ አቅጣጫ፣ ዛሬ በሀገራዊ ምክክሩ መልክ መሬት እየነካ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ደጋግመው እንደሚያነሱት፣ "ሰላም እንደ ውርስ በራሱ የሚተላለፍ ስጦታ ሳይሆን፣ በጋራ ጥረት፣ በውይይትና በመተማመን የምንገነባው እሴት ነው።" አክለውም "ኢትዮጵያን የምንገነባት አንዱ ሌላውን በማሸነፍና በመርገጥ ሳይሆን፣ በመደመር ነው" በማለት የገለጹት ጥልቅ ሀሳብ፣ የዚህ ሀገራዊ ምክክር ዋነኛ ሞተር ነው።

በዚህ ምክክር ማንም የሚያሸንፈው ወይም ማንም የሚሸነፈው አካል የለም፤ ብቸኛዋ አሸናፊ ኢትዮጵያ ነች። ይህ መድረክ የታሪክ ቁርሾዎቻችንን በይቅርታ የምናክምበት፣ የትውልዱን ጥያቄዎች በጋራ የምንመልስበት፣ እንዲሁም መጪው ትውልድ ቂም ሳይሆን ፍቅርን፣ ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን አውርሰነው እንዲያልፍ የምንሰራበት ወርቃማ እድል ነው።

በመሆኑም፣ ይህ የጋራ ቤታችን ጉዳይ ነውና እያንዳንዱ ዜጋ፣ የፖለቲካ ተዋናዮች፣ የሲቪል ማህበራት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ሁላችንም በቅንነት፣ በከፍተኛ ኃላፊነትና በተስፋ መንፈስ ልንደግፈው ይገባል። ዛሬ የምናደርገው በሳል ውይይት፣ ነገ የልጆቻችን መፈንጠቂያ የሆናች፣ ሰላሟ የተረጋገጠ፣ ፍትሕ የሰፈነባትና የበለፀገች ኢትዮጵያን ይገነባል።

ሀገራዊ ምክክር እውነተኛ የሀገር ግንባታ የመሠረት ድንጋይ፣ የጋራ ዕጣ ፈንታችን መሪ አቅጣጫ ጠቋሚ እና የአንድነታችን ዘላቂ ዋስትና ነው።

01/03/2026
03/01/2026

Address

Delhi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Garaa Nama Nyaata posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category