06/03/2026
የመደመር ፍልስፍና መሰረታዊ መነሻ የሰው ልጆችን ፍላጎትና አቅም መዳሰስ ነው።
የመደመር ፍልስፍና የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ንድፈ-ሀሳብ ብቻ አይደለም፤ መሰረቱ ጥልቅ የሆነ የሰዉ ልጅ አቅምና ፍላጎት ላይ ያተኮረ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ እይታ ነው። ማንኛውም ለውጥ ወይም እድገት ስኬታማ የሚሆነው የሰውን ልጅ ውስጣዊ ፍላጎት ሲረዳና ያለውን አቅም ማውጣት ሲችል ብቻ ነው፡፡
የሰው ልጅ ፍላጎቶች ዘርፈ ብዙ ናቸው። ከመሰረታዊ የቁሳቁስ ፍላጎቶች ምግብና መጠለያ ጀምሮ እስከ ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች ማለትም ክብር፣ እውቅና እና ነፃነት ድረስ ይዘልቃሉ። መደመር እነዚህን ፍላጎቶች በሁለንተናዊ መልኩ በመዳሰስ ያልተመለሱ የትውልድ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይተጋል። ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልን ዓላማ ያደርጋል።
እያንዳንዱ ሰው፣ ማህበረሰብም ሆነ ሃገር የራሱ የሆነ ፀጋና አቅም አለው። መደመር ይህንን አቅም አቀናጅቶ መጠቀምን ያስተምራል፡፡ ያሉንን መልካም እሴቶች በመጠበቅ፣ ጉድለቶቻችንን ደግሞ በሌላው አቅም በመሙላት ወደ ላቀ ውጤት እንድንሸጋገር ያግዘናል። የሰው ሀብትን ወደ ምርታማነት በመቀየር የብልፅግና ጉዞን ያፋጥናል።
የሰው ልጅ ፍላጎቱና አቅሙ ሲጣጣም ውጤቱ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ይሆናል፡፡ መደመር የቆዩ ስብራቶችን በመጠገን እና አዳዲስ አቅሞችን በመገንባት፣ የሁላችንንም ፍላጎት የምታስተናግድ ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት ዋና ግብ አድርጎ ይሰራል።
ሁላችንም ልክ እንደ ስንዴ ነዶ በአንድነት ቆመን፣ በያለንበት ዘርፍ የሌላውን ፍላጎት እያከበርን፣ የራሳችንን አቅም ደግሞ ለጋራ እድገት ስናበረክት "መደመር" ትርጉም ይኖረዋል።