Sooppe Soddo Baana

Sooppe Soddo Baana S**o betee

07/08/2026
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል የህዝቡ ባህል፣ ታሪክና ማንነት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውና በየዓመቱ በብሔሩ ዘመን አቆጣጠር መሠረት በመጀመሪያ ወር በታላቅ ድምቀት የሚከበር የማይዳሰ...
26/07/2026

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል የህዝቡ ባህል፣ ታሪክና ማንነት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውና በየዓመቱ በብሔሩ ዘመን አቆጣጠር መሠረት በመጀመሪያ ወር በታላቅ ድምቀት የሚከበር የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ነው።

ወላይታ የራሱ የሆነ መንግስታዊ መዋቅር የነበረው ፣ የዳኝነት ሥርዓት፣ ባህላዊ አልባሳት እና ሽመና ጥበብ ያለው በሁሉም ዘንድ የሚወደድ የዜማ ቅላጸና ውዝዋዜ ያለው ኩሩ ህዝብ ነው ።

የወላይታ ሕዝብ እና የግፋታ በዓል ያላቸው ቁርኝት ሺህ አመታቶችን ያስቆጠረ እጅግ የጠነከረና ደማቅ ማህበራዊ ህይወትን የሚያንጸባርቅ ነው።

ግፋታ የወላይታ ሕዝብ ማንነት፣ አንድነት፣ የጥበብና የሰላም እሴቶች በጉልህ የሚታዩበት ታላቅ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው ለወላይታ ብሎም ለኢትዮጵያ ልዩ ገጸበረከት ነው።

ግፋታ በዓል በወላይታ ብሔር ዘንድ ከአመት ወደ አመት መሸጋገሪያ፣ የሰላም፣ የዕርቅና የአዲስ ተስፋ በዓል ተደርጎ የሚወሰድ ልዩ በዓል ነው።

''Gifaataa''ማለት በኩር ወይም ታላቅ የሚለውን ትርጉም የሚይዝ ስሆን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከችግር ወደ ጥጋብ መሸጋገርን የሚያመላክት ስሆን በወላይታ ህዝብ ዘመን አቆጣጠር ጥበብን ተከትሎ በፀሐይና በጨረቃ ዑደት እና በተፈጥሮ ስሌት መሠረት ቀኖች ተቆጥረው ወቅቱ ታውቆ የዓመቱ መጀመሪያ ግፋታ ወር የሚከበር በዓል ነው።

በግፋታ ወቅት የተቀያየመ ሰው ሳይታረቅ በዓሉን ማክበር በባህሉ መሠረት አይፈቀድም። ስለዚህ በአካባቢው የተቀያየሙ ሰዎች ካሉ መረጃ የሰበሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች ግለሰቦቹን ተሰብስበው በዓሉ ከመድረሱ በፊት ያስታርቃሉ፤ በዚህም በቀልና ቅሬታ ይወገዳል።

ሌላው ግፋታ በዓል ሲቃረብ ርቀው የቆዩ የቤተሰብ አባላት ወደ ትውልድ ቀያቸው ተመልሰው ከወላጆቻቸውና ከዘመዶቻቸው ጋር የሚገናኙበት ታላቅና የፍቅር በዓል በመሆኑ በህዝቡ ዘንድ በእጅጉ ይወደዳል። ወጣቶችና አዋቂዎች በየደረጃው በባህላዊ አልባሳት አጊጠው "ሌኪያ"፣ "ባሊ ሄሌለ" ጨዋታ በመተቃቀፍ የሚጫወቱ ሲሆን ሌሎች ለአይን ማራኪ የሆኑ ባህላዊ ውዝዋዜዎችን በአደባባይ ያቀርባሉ።

ለግፋታ በዓል ተብሎ የተለያዩ ወላይታ ባህላዊ ምግቦችንና መጠጦችን ለማሰናዳት ከወራት በፊት ሁሉም ሰው በየአካባቢው ተዘጋጅቶ ስለምጠብቅ አከባበሩን ለየት ያደርገዋል።

ግፋታ በዓል በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የኢትዮጵያ ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንደኛው ነውና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ነው።

ግፋታ በዓል በUNESCO በዓለም የሰው ልጅ ወካይ ቅርስ ሆኖ በይፋ መመዘገቡ ለወላይታ ሕዝብ፣ ብሎም ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በርካታ ፋይዳዎች የሚያስገኝ ነው።

ምን ፋይዳ አለው ? ከሆነስ የግፋታ ዋና እሴቱ ዕርቅ፣ ይቅርታና ሰላም በመሆኑ፣ ይህ በጎ ባህል በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ መልካም ተሞክሮ እንዲወሰድና በሀገር ውስጥም ቢሆን የማህበራዊ ትስስርንና አብሮነትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ስለምታስብ ፋይዳው የጎላ ነው።

ሌላው የወላይታ ሕዝብ ቱባ ባህል፣ ታሪክ፣ የዘመን አቆጣጠር ጥበብና የማህበራዊ እሴት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ እውቅና እና ክብር የሚያስገኝ ነው። ከዚህ ባሻገር ባህሉ ሳይበረዝ እንዲጠበቅ ያደርጋል።

የዩኔስኮ ምዝገባ ዋና ዓላማ በሌሎች አለም ሀገራት የተመዘገቡ ቅርሶችን ለመጠበቅ እንደሚያደርገው ሁሉ ይህንን በዓል እንዳይጠፋና ለወደፊቱ ሳይበላሹ ለትውልድ እንዲተላለፍ እንክብካቤና ጥበቃ ያደርጋሉ ማለት ነው። ስለዚህም የግፋታ እሴቶቹን ተጠብቆ እንዲቆዩ በእጅጉ ያግዛል።

የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡ የዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን ትኩረት በቀላሉ ለመሳብ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ ይህም የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ወላይታ አካባቢ እንዲጎርፉ ያደርጋል።

ይህ ታሪካዊ ምዝገባ ለአካባቢው የቱሪስቶች መምጣት ለሆቴሎች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለባህላዊ አልባሳትና እደ-ጥበብ ዕቃዎች አምራቾች እንዲሁም ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድልና ገቢ ይፈጥራል።

ቅርሱ ለዓለም አቀፍና ለሀገር ውስጥ ጥናትና ምርምር እንዲመች፣ በሰነድ ደረጃ በጥራዝ ተዘጋጅቶ እንዲያዝ እና ለዚህም የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ እንዲመቻች በማድረግ ታሪክን በትውልድ መካከል ለማስቀጠል ይረዳል።

ከቅርሱ ጋር የተያያዙ የሙዚየም እና የቅርሳ ቅርቅስ ማዕከላትን ለመገንባትና ለማጠናከር ዓለም አቀፍ የቴክኒክና የገንዘብ ትብብርን ያመቻቻል።

መጪው የሚከበረው የጊፋታ በዓል የቱሪዝም ፍሰትን በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያስገኝ እና የወላይታን ታሪክና ባህል ለዓለም ይበልጥ የሚያስተዋውቅ ታላቅ በዓል በመሆኑ፣ ዘንድሮ ከወትሮው በተለየ ደመቅ ባለ ሁኔታ ይከበራል።

ይህ ታላቅ ስኬት እንዲቀጥልም የባህሉ ባለቤቶችና ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሠሩ ይገባል።

በሰይፋ ስሙኤል

የወላይታ ባህል እና ታሪክን በመጎብኘቱ የተሰማውን ደስታ ዩቲዩበር  K_MONEY ገለፀ።ባህል ቅርስ እና ታሪክን ለአሁኑ ትውልድ ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ጥረት ያደነቀው ዩቲዩበር  K_MONE...
04/03/2026

የወላይታ ባህል እና ታሪክን በመጎብኘቱ የተሰማውን ደስታ ዩቲዩበር K_MONEY ገለፀ።

ባህል ቅርስ እና ታሪክን ለአሁኑ ትውልድ ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ጥረት ያደነቀው ዩቲዩበር K_MONEY ከአሜሪካን ወደ ወላይታ መጥቶ ባየው ነገር ሁሉ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

ተፅእኖ ፈጣሪ ዩቲበሮች እና ቲክቶከሮች ወደ ወላይታ ሶዶ ሲገቡ የዞን እና የከተማ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

K_MONEY ወይም ኬና እና ሌሎችም ኢትዮጵያዊያን አጋሮቹ በወላይታ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የቅርሶችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

02/03/2026

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ 130ኛውን የአድዋ የድል መታሰቢያ በአል አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመልዕክቱ ሙሉ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

"በመላው ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ህብር ተጋድሎ የሀገራችንን ሉአላዊነትና ነፃነት ፣ የህዝቦቻችንንና የግዛት አንድነታችንን ከማረጋገጥ በተጓዳኝ የመላው ጥቁር አፍሪካዊያን ፣ የካሪቢያንና የላቲን አሜሪካ ህዝቦች የእኩልነትና የነፃነት ፋና ወጊ ተምሳሌት ለሆነው ለ130ኛው የአድዋ የድል መታሰቢያ በአል ዕለት በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን/ለማለት እወዳለሁ።

የዓድዋ ድል መላው ኢትዮጵያዊያን የመልክአ-ምድራዊ አሰፋፈር ፣ የቋንቋና የባህል ፣ የዘርና የሀይማኖት ልዩነቶቻቸውን በማቻቻል ኢትዮጵያችንን ከወራሪውና ተስፋፊው የኢጣሊያ ጦር ተከላክለው ነፃነታችን ቀጣይ እንዲሆን ውጤታማ ፣አኩሪና አንፀባራቂ ተጋድሎ ያደረጉበት በመሆኑ አውዱን ልዩ ያደርገዋል።

የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ነፃነት በመዳፈር ሀብቷን ለመቀራመት ያለመውና ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀው ዕብሪተኛው የኢጣሊያን ተስፊፊ ሰራዊት የለኮሰውን ጦርነት መላው የኢትዮጵያ ጀግኖች በአንድነት ታላቅ የሀገር ፍቅርና ወኔ በመታጠቅ በጦርና በጎራዴ መክተው ወረራውን መቀልበሳቸው ለዛሬው ሀገራዊ ግንባታና ለነገው የብሔራዊ ከፍታ የጎላ አርአያነት አለው።

ጀግኖች አባቶቻችን በዓድዋ ተራሮች ባደረጉት አኩሪ ተጋድሎ መነሻነት ሀገራችን በአፍሪካ ቀንድና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ክብር እንዲደምቅ እንዳደረጉልን ሁሉ የዛሬው ትውልድ የሆንን ሁላችንም ደግሞ ብሔራዊ ጥቅማችንን የማስከበር ኃላፊነት እንዳለብን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡

የአድዋን የድል ችቦ ከማብራት ጎን ለጎን ለተፅዕኖ ሸብረክ የማይል ፣ ዘላቂ ፣ የተሟላ ዕድገትና ልማት ዕውን ሊሆን የሚችለው የፖለቲካ ነፃነት በኢኮኖሚ ነፃነት ሲታጀብ በመሆኑ የሀገራችን ሉአላዊነት፣ የህዝቦቻችንና የግዛት አንድነት ቀጣይነት ከማረጋገጥ በተጓዳኝ በሰፋፊ ሀገራዊ የኢክኖሚ ሪፎርሞች የህዝቦቻችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን።

በታሪክ አጋጣሚ ከዛሬ 35 ዓመታት ወዲህ በሀገራችን በተሳሳተና ጠባብ የህወሀት አመራር ሰጪነት ያጣነውን የባሕር በር በመመለስ የህዝባችንን ኑሮ በአጭር ጊዜ ለማደላደል በምናደርገው ጥረት ወደ ቀደመው ልዕልናችን መመለስ ማለት በዓድዋ ድል ያገኘነውን ሀገራዊ ክብር በኢኮኖሚ ድል እንደማጀብ ነው።

እናም ለስኬታማነቱ የሚጠበቅብንን መወጣት የአያቶቻችን አደራም ጭምር ነውና አብሮነታችንን በላቀ ደረጃ ማጠናከር ይጠበቅብናል።

ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታና ለህዝቦቻችን የጋራ የላቀ ተጠቃሚነት ጋሬጣ የሆኑ የውስጥ ባንዳዎችንና የውጪ ጠላቶችን ተቀናጅተን በመከላከልና በመቆጣጠር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በዘላቂነት የማስከበር ጉዳይ የዜግነት ግዴታም ጭምር መሆኑን መገንዘብ አስተዋይነት ነው ፡፡

የአድዋ ድል የብዝሀነትና የመቻቻል፣ የፅናትና የቆራጥነት ተምሳሌታዊ አንፀባራቂ ውጤት በመሆኑ ፈለጉን ተከትለን እያጋጠሙን ያሉትን ጊዜያዊ ፈተናዎች በፍትሀዊነት ፣ በላቀ የአብሮነትና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ተስፋ ሰጪውን የብልፅግና ጉዟችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ታሪክ መሥራት ማለት ከአባቶቻችን የተረከብነውን እናም በዓለምና በአፍሪካ አደባባዮች ቀና እንድንል ያደረገንን አኩሪ የድል አደራ ቀጣይ እንድናደርግ ብሎም ኢትዮጵያችንን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ ስንችል በመሆኑ ለጋራ ሀገር ውድቀት በኩርፊያ ከማሴር ይልቅ የቅድሚያ ቅድሚያ ድህነትንና መጠላለፍን ከብሔራዊ ክብራችን ላይ አሽቀንጥረን መጣል የወቅቱ ሀገራዊ ጥሪ መሆኑን እየገለፅኩ መድረኩ በይፋ የተከፈተ መሆኑን አበስራለሁ።

"የዓድዋ እሴት ለሁሌንተናዊ ብልፅግናችን!!"

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!"

ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
የካቲት /2018 ዓ.ም

21/02/2026

I accepted 2 fan badges from Jabessa Ahmed and ጫዓሎ ወዲ በርሀ.

24/01/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! ጫዓሎ ወዲ በርሀ, ሎምብሶ አየላ, Ahmed Adem

“የጊፋታ ብስራቶች፤ ለህዝባችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ  "ጊፋታ" በዓል በዩኔስኮ (UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርሶች በይፋ መመዝገቡን ተከትሎ በአደባባይ ከመላ...
14/01/2026

“የጊፋታ ብስራቶች፤ ለህዝባችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በዩኔስኮ (UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርሶች በይፋ መመዝገቡን ተከትሎ በአደባባይ ከመላዉ ኢትዮጵያዊያን ጋር የደስታ ማብሰሪያ በዓል በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።

ጊፋታ ከብዙ ትግል በኋላ በዓለም ቅርስነት
በዩኔስኮ (UNESCO) መመዝገቡ የመላው ወላይታ ህዝብ የአንድነትና የጋራ ትግል ውጤት ነው።

ይህም ለጋራ ጉዳይ በጋራ በአንድነት መቆም ምን ያህል ውጤታማ እንደሚያደርግ ማሳያ በመሆኑ በዞኑ በሚደረጉ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አንድነታችን እርሾ ሆኖ ያገለግላል።

በመሆኑም የጊፋታ ብስራት በፈጠረው መነቃቃትና አንድነት ሁሉም ለልማት በጋራ መቆም አስፈላጊ ነው።

በዞኑ የተጀመሩ በፌደራል፣ በክልልና በዞን መንግሥት የተጀመሩ ሥራዎች በታለመላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የሁሉንም ድጋፍና ትብብር ይጠይቃል። በመሆኑም በጊፋታ ላይ ያሳየነውን አንድነት እና ቁርጠኝነት በሌሎችም በመድገም ወደሌላ ብስራት፣ ወደሌላ ከፍታና ድል የምንሸጋገርበት እንዲሆን መሥራት ይጠይቃል።

07/01/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Teshome Tanga, Zehara Zehara, Asma Ajulo

07/01/2026

የገናን በዓል አስመልከቶ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ‼️

ከሁሉ አስቀድሜ ለክልላችንና ለሀገራችን የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንዲሁም ለመላው የግብርና ቤተሰብ ‹‹እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ‼️›› እላለሁ፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ቆይታው አበክሮ ካስተማራቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው እርስበርሳችን እንድንዋደድና እንድንፋቀር በመሆኑ መላው ህዝበ-ክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናክብር በፍቅር፣ በመተጋገዝ፣ በመረዳዳትና በአንድነት ሊሆን ይገባል፡፡

ሰው ተኮርነት ከሁሉም በላይ የላቀ ዕሴት በመሆኑ መላው ኅብረተሰብ ለሰው ልጅ ክብርና ፍቅር በመስጠት ያለንን በማካፈልና ጧሪ-አልባ እና አቅመ-ደካማ ወገኖቻችንን በማገዝ በዓሉን ልናከብር ይገባል፡፡

ምድር በረከቷን እንድትሰጠን ባለፉት ሰባት ዓመታት በሀገራችን ሰው ተኮር የአኗኗር ዘይቤን ለማስረፅና ሰብዓዊነትን ለማጎልበት መንግሥት በቀየሰው ስትራቴጂ እጅግ በርካታ ተምሳሌታዊ ተግባራት በመፈጸማቸው የበርካታ ዜጎችን ህይወት ማለምለም ተችሏል፡፡

የዜጎችን ህይወት በማሻሻልና የአኗኗር ዘይቤን በማዘመን የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሠራ በመሆኑ እና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመሸፈን ለዜጎች የተሟላ ብሔራዊ ክብርና ኩራትን እንዲሁም ሉዓላዊነትን ለማጎናጸፍ የተጀመረው የ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሽግግር በስኬት ታጅቦ እየተጓዘ ይገኛል፡፡

ግብርናችንም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እየዘመነ፣ ምርታማነትን እያጎለበተ፣ በገበያ-ተኮርና ኤክስፖርት-መር አመራረት የክልላችንን አርሶና አርብቶ አደሮችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና የብልፅግና ጉዟችንን ለማፋጠን በሚደረገው ሁሉ-አቀፍ ጥረት ውስጥ ቀዳሚውን ሚና እንዲጫወት እየተረባረብን እንገኛለን፡፡

በዚህ ረገድ ቢሯችን ይህንኑ ውጥን ለማሳካት በእርሻ ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት፣ በግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት፣ በአደጋ ስጋት ሥራ አመራርና ምግብ ዋስትና፣ በግብዓትና ምርት ጥራት ቁጥጥር፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት ልማት፣ በቡናና ቅመማ ቅመም ልማት፣ በቴክኖሎጂ ማፍለቅ ማላድና ብዜት እንዲሁም በሌሎች መሰል የትኩረት መስኮች ባለፉት ዓመታት አመርቂ ስኬቶችን አስዝግቧል፡፡

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሀሳብ አፍላቂነት ተጀምረው እየተተገበሩ በሚገኙት የግብርና ኢኒሼቲቮች የተመዘገቡ ለውጦች ብልፅግናን ለማረጋገጥ እንደምንችል የሚያረጋግጡ አብነቶች መሆን ችለዋል፡፡

ጊዜው ዕዳን ወደ ምንዳ ፤ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የምንቀይርበትና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የምናሳድግበት እንዲሁም በመፍጠርና በመፍጠን ብልፅግናችንን የምናረጋግጥበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የግብርና ልማታችን የፊት መስመር ተሰላፊ የሆኑት አርሶና አርብቶ አደሮቻችን፣ ተግባሮቻችንን በውል ተገንዝበው የተቀረፁ ስትራቴጂክ ግቦቻችንን ለማሳከት የአመራር ሚና የሚጫወቱ አስፈፃሚዎቻችን፣ ፈፃሚዎቻችንና መላው ኅብረተሰብ ከምንጊዜውም በላቀ ትጋት እንዲንረባረብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን እያስተላለፍኩ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በድጋሚ መልካም በዓል እመኛለሁ‼️፡፡

በድጋሚ መልካም የልደት በዓል‼️

ክቡር መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር)
በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ

Address

Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sooppe Soddo Baana posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category