Hashim tube

Hashim tube ኑ አዉሩ

17/02/2026
16/02/2026

ከሠላት የቀጠለ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 13
ጃቢር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "በኢማን እና በኩፍር መካከል የሚለየው ሶላት ነው"። عَنْ جَابِرٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ بَيْنَ الْكُفْرِ وَالإِيمَانِ تَرْكُ الصَّلاَةِ

ከነቢያችን”ﷺ” በፊት በነበሩት ነቢያት በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ላይቆሙ ይችላሉ፥ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል። ነገር ግን አሏህ ሶላትን መስገድ ወደ እነርሱ አውርዷል፦
21፥73 ”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

"ፈሕሻእ" فَحْشَاء ማለት "መጥፎ ቃላት" ማለት ሲሆን "ሙንከር" مُنكَر ደግሞ "መጥፎ ሥራ" ነው፥ ሁለቱም የሸይጧን እርምጃዎች ናቸው። ሶላት ግን በኢማን፣ በኢኽላስ እና በኢትባዕ ከተፈጸመች ከፈሕሻእ እና ከሙንከር ነገር ሁሉ ትከለክላለች፦
24፥21 እርሱ በመጥፎ እና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ
29፥45 ሶላት ከመጥፎ እና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው። إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ

ሶላት በዱንያህ የምታስረዳ እና አሏህ በሚፈሩት ላይ ቀላት ናት፥ በአኺራ ደግሞ የጀናህ ቁልፍ ናት፦
2፥45 በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ! እርሷም (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 4
ሙጃሂድ እና ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ." የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሶላት የጀናህ ቁልፍ ናት፥ ውዱእ ደግሞ የሶላት ቁልፍ ነው"። عَنْ مُجَاهِدٍ، عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، رضى الله عنهما قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مِفْتَاحُ الْجَنَّةِ الصَّلاَةُ وَمِفْتَاحُ الصَّلاَةِ الْوُضُوءُ ‏"‏ ‏

አሏህ ሙሶሊን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ወሠላሙ ዐለይኩም

16/02/2026

ሶላት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥103 ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

"ሩክን" رُكْن ማለት "ምሰሶ" "ዐምድ" "ማዕዘን" ማለት ሲሆን የሩክን ብዙ ቁጥር ደግሞ "አርካን" أَرْكَان ሲሆን "ምሰሶች" "አዕማድ" "ማዕዘናት" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "አርካኑል ኢሥላም" أَرْكَان الْإِسْلَٰم ማለት "የኢሥላም ምሰሶች" "የኢሥላም አዕማድ" "የኢሥላም ማዕዘናት" ማለት ነው። ከአርካኑል ኢሥላም አንዱ ሶላት ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአሏህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

"ሶላት" صَلَاة የሚለው ቃል "ሶላ" صَلَّىٰ ማለትም "ጸለየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጸሎት" ማለት ነው፥ "ሶላት" صَلَاة በውስጡ ሦስት ዐበይት ክፍሎች ያቅፋል። እነርሱም፦
1ኛ. "ቂያም" قِيَام ማለትም "መቆም"
2ኛ. "ሩኩዕ" رُكوع ማለትም "ማጎንበስ"
3ኛ. "ሡጁድ" سُّجُود ማለትም "ስግደት" ናቸው፦
22፥77 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

ሶላትን ደንቡን ጠብቀው የሚቆሙ፣ የሚያጎነብሱ እና የሚሰግዱ "ሙሶሊን" مُصَلِّين ይባላሉ፥ አመጸኞች በሰቀር ውስጥ ሆነው ለምን በሰቀር ውስጥ ገባችሁ? ሲባሉ፦ "ከሙሶሊን አልነበርንም" የሚል መልስ ይሰጣሉ፦
74፥43 እነርሱም፦ «ከሙሶሊን አልነበርንም» ይላሉ። قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ

ሙሰሊን በቂያም "ሙቂሚን" مُّقِيمِين ሲባሉ፣ በሩኩዕ "ራኪዒን" رَّاكِعِين ሲባሉ፣ በሱጁድ ደግሞ "ሣጂዲን" سَاجِدِين ይባላሉ። ሶላት በምእምናን ላይ በአምስት ወቅት ጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናት፥ ኢማን እና ኩፍርን ለይቶ በመካከል ያለው ግድግዳ ሶላት ነው፦
4፥103 ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا
ቀጣይ>>>

30/01/2026

ፈጣሪ አምልኮ ይፈልጋልን?

28/01/2026

ተወኩል

22/01/2026

[የ ሀይማኖት እና ህብረት አንድነት እና ልዩነት]
ሃይማኖት" እና "ህብረት" ምንም እንኳን ተደጋጋፊ >ቢሆኑም፣ የራሳቸው የሆነ የተለየ ትርጉም እና ትኩረት አላቸው። ልዩነታቸውን በሚከተለው መልኩ ማየት እንችላለን፡
​1. ሃይማኖት (Religion)
​ሃይማኖት በአንድ የበላይ አካል (ፈጣሪ) ማመንን፣ ያንን እምነት የሚገልጹ ስርአቶችን እና ህጎችን የያዘ መዋቅር ነው።
​ትኩረቱ፡ በሰው እና በፈጣሪ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ያተኩራል።
​ይዘቱ፡ ዶግማ (የማይቀየሩ መርሆዎች)፣ የአምልኮ ስርአቶች፣ ህጎች እና መመሪያዎችን ይይዛል።
​መገለጫው፡ አንድ ሰው የሚከተለውን የእምነት መስመር ወይም ተቋም (ለምሳሌ፦ እስልምና፣ ክርስትና...) ለይቶ ያሳያል።
​ግቡ፡ የነፍስ መዳንን፣ ከፈጣሪ ጋር መታረቅን እና የሞራል መመሪያን ማግኘት ነው።
​2. ህብረት (Fellowship/Unity)
​ህብረት ማለት በተመሳሳይ እምነት፣ አላማ ወይም ፍላጎት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚኖር ጥልቅ ቅርበት እና ግንኙነት ነው።
​ትኩረቱ፡ በሰው እና በሰው መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ያተኩራል።
​ይዘቱ፡ ፍቅር፣ መረዳዳት፣ መጽናናት፣ ልምድን መጋራት እና አብሮነትን ይይዛል።
​መገለጫው፡ ከሃይማኖታዊ ተቋሙ ባለፈ ሰዎች በልባቸው የሚገናኙበትና የሚደጋገፉበት መንፈሳዊ ቤተሰብነት ነው።
​ግቡ፡ እርስ በእርስ መተናነጽ፣ ብቸኝነትን ማስወገድ እና የጋራ ጥንካሬን መፍጠር ነው።
ለምን ሁለቱም ያስፈልጋሉ?
​ህብረት የሌለው ሃይማኖት፡ ደረቅና ህግን ብቻ የሚከተል (Legalistic) ሊሆን ይችላል። ሰዎች በስርአቱ ይገኛሉ እንጂ እርስ በእርስ አይተዋወቁም ወይም አይረዳዱም።
​ሃይማኖት (መሰረት) የሌለው ህብረት፡ ዝም ብሎ ማህበራዊ ክበብ (Social Club) ብቻ ሊሆን ይችላል። መንፈሳዊ መመሪያና የጋራ እምነት ስለማይኖረው በቀላሉ ሊበተን ይችላል።

22/01/2026

ሃይማኖት _
ሃይማኖት" የሚለው ቃል ጥልቅ የሆነ የግዕዝ ስርወ-ቃል ያለው ሲሆን፣ ትርጉሙንም እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል፡
​1. ስርወ-ቃላዊ ፍቺ (Etymology)
​"ሃይማኖት" የሚለው ቃል የመጣው "አመነ" (አምነ) ከሚለው የግዕዝ ግስ ነው። ይህም በቀጥታ ሲተረጎም የሚከተሉትን ትርጉሞች ይይዛል፡
​ማመን፡ በአንድ ነገር እውነተኝነት ላይ ሙሉ እምነት ማሳደር።
​መታመን፡ ለአንድ ዓላማ ወይም ለፈጣሪ ታማኝ መሆን።
​መረጋገጥ/መጽናት፡ በአንድ በኩል የማይናወጥ አቋም መያዝ።
​ስለዚህ በቃላዊ ትርጉሙ "ሃይማኖት" ማለት "የማመን ተግባር" ወይም "የእምነት ስርዓት" ማለት ነው።
​2. በሌሎች ቋንቋዎች ያለው ፍቺ
​ለተጨማሪ ግንዛቤ፣ "Religion" የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል አመጣጥ ማየቱ ጠቃሚ ነው፦
​"Religion" የሚለው ቃል "Religare" ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን፣ ትርጉሙም "ማሰር" ወይም "መልሶ ማገናኘት" (to bind back) ማለት ነው።
​ይህም የሚያመለክተው ሰውን ከፈጣሪው ጋር መልሶ የሚያገናኝ "ገመድ" ወይም "መንገድ" መሆኑን ነው።
​3. የ"ሃይማኖት" ዋና ዋና ባህሪያት
​አንድ ነገር "ሃይማኖት" ተብሎ ለመጠራት ብዙውን ጊዜ እነዚህን ሦስት ነገሮች ይይዛል፡
​ዶግማ (አስተምህሮ)፦ አማኙ እውነት ነው ብሎ የሚቀበለው መሰረታዊ እውቀት (ለምሳሌ፦ የፈጣሪ መኖር፣ የሞት በኋላ ህይወት)።
​ስርዓተ አምልኮ (Ritual)፦ እምነቱን ለመግለጽ የሚደረጉ ተግባራት (ለምሳሌ፦ ጸሎት፣ ስግደት፣ መስዋዕት)።
​ግብረ ገብ (Morality)፦ አማኙ በህይወቱ ሊከተላቸው የሚገቡ የባህሪ መመሪያዎች (ለምሳሌ፦ አለመዋሸት፣ መርዳት)።
​ማጠቃለያ
​በአጭር አገላለጽ፣ ሃይማኖት ማለት አንድ ሰው ስለ ፈጣሪ፣ ስለ ዓለም አፈጣጠር እና ስለ ሰው ልጅ ህልውና ያለውን እምነት የሚገልጽበትና ከፈጣሪው ጋር የሚገናኝበት መንፈሳዊ መንገድ ነው።

Address

Adiss Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hashim tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category