ቅኔ ሚዲያ

ቅኔ ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቅኔ ሚዲያ, bole addis ababa, Addis Ababa.

እናቱ የዓምዕሮ ህመምተኛ አባት ጥበቃ ስለሆኑ ቀኑን ሙሉ ቤት ተቆልፎበት የሚዉለዉ ህፃን  ዉጪ ለማየት ያለዉን ጉጉትነገሩ የሆነዉ በነገሌ ቦረና የከብቶች ገበያ ሰፈር አከባቢ መሆኑን ግዮን ማ...
06/09/2026

እናቱ የዓምዕሮ ህመምተኛ አባት ጥበቃ ስለሆኑ ቀኑን ሙሉ ቤት ተቆልፎበት የሚዉለዉ ህፃን ዉጪ ለማየት ያለዉን ጉጉት

ነገሩ የሆነዉ በነገሌ ቦረና የከብቶች ገበያ ሰፈር አከባቢ መሆኑን ግዮን ማለዳ አረጋግጧል ። ይህን ምስል ያጋራዉ ሰዉ ድንገት በዚያ ሲያልፍ አይኑ ድንገት አንድ በተቆለፈ በር ስር አጮልቆ ወደ ዉጪ የሚመለከት ታዳጊ ላይ ያርፋል።

የሚያየዉን ማመን አቃተዉ በትልቅ ድንጋየይ ስር አጮልቆ ዉጪዉን ይመለከታል።እየተራመደ ወደ በሩ ሲጠጋ በሩ ተቆልፎአል።

ጎረቤት ያሉ ሰዎችን ሲያናግር እናቱ የአእምሮ ህመምተኛ ነች አባቱ ደግሞ የዘበኝነት ስራ ስለሚሰራ ለሊት ወጥቶ ማታ ነዉ የሚመጣዉ ህፃኑ ብቻዉን ተቆልፎበት ቤት ዉስጥ ነዉ የሚዉለዉ እዛዉ ነዉ የሚፀዳዳዉ፣በጣም የሚያሳዝነዉ ደሞ እራቁቱን ነዉ።

ሕፃናት የማንም የግል ጉዳይ ብቻ አይደሉም። ተጨማሪ ፎቶዎች የፈስቡክን ህግ ስለሚጥሱ በ Ghion Maleda ቴሌግራም ቻናል ላይ ይመልከቷቸው ። እጅግ ልብ ሰባሪ ነው። ማንኛውም ሕፃን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ከተገኘ ጎረቤት፣ ማህበረሰብና ተቋማት ተባብረው ደህንነቱን ማረጋገጥ ይገባል። ፍትህ ሊያገኝ ይገባል !

እናትና አባትን በመውቀስ ብቻ ሳይሆን መፍትሄ እንፈልግ። ከቤተሰቡ ችግር በስተጀርባ የአእምሮ ጤና፣ የኢኮኖሚ ችግር ወይም ሌሎች ሁኔታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ የቤተሰቡ ድጋፍም አስፈላጊ ነው።

አንድ ሕፃን ከበር ስር አጮልቆ የውጭውን ዓለም ሲመለከት ማየት ብቻ አያስፈልገንም፤ የሚፈልገውን እርዳታ እንዲያገኝ እንርዳው።
ሕፃናት መብታቸው ነው በደህና መኖር፣ መጫወት እና የውጭውን ዓለም በነፃነት ማየት። 🙏💔

እባካችሁ ለደጋጎች ይሄ መልዕክት እንዲደርስ #ሼር በማድረግና መረጃውን በማጋራት አድርሱልን የኛ አንድ የህፃኑን ህይወት ሊለውጥ ይችላል

ግዮን ማለዳ

ቅኔ ሚዲያ

🎹  (ደራሲው)አዲስ ቆንጆ ሙዚቃ ተለቀቀ #ዳህላክ(ናቅፋ)🎤🎤👇👇👇🎼🎹
05/09/2026

🎹 (ደራሲው)
አዲስ ቆንጆ ሙዚቃ ተለቀቀ
#ዳህላክ(ናቅፋ)🎤🎤👇👇👇🎼🎹

የዘፈን ርዕስ = ዳህላክ ( ናቅፋ )ግጥም ዜማ = ዘገዬ ታዴድምፂዊ = ዘገዬ ታዴቅንብር = ብርሃነ ገ...

‎ከአጋንንት ሁሉ የሚገርመኝ "ጵንሙኤል"ነው። አንባቢ ነው መፅሐፍ ከእጁ አይጠፋም እንደ ቀደምት ድርሳናት ‎በአካል ሲገለፅ ረጅም(የሰው 2× ቁመት)ቀጭንና ውብ አክናፋት ያሉት ነው።‎‎እንደ ...
31/08/2026

‎ከአጋንንት ሁሉ የሚገርመኝ "ጵንሙኤል"ነው። አንባቢ ነው መፅሐፍ ከእጁ አይጠፋም እንደ ቀደምት ድርሳናት ‎በአካል ሲገለፅ ረጅም(የሰው 2× ቁመት)ቀጭንና ውብ አክናፋት ያሉት ነው።

‎እንደ መፅሐፈ ሔኖክ ገለፃ ጵኑሙኤል ከግሪጎሪ 200 ‎አማፅያን መሃል አንዱ ሲሆን ልክ ሲወድቁ (በነገራችን ልይ ሳይንስ በምድር ዙርያ ያገኛቸው impact craters ‎ወይንም የሜትሮይት ጉድጓዶች ብዛት 200 ነው)‎ሄርሞን ተራራ ላይ ማንም በንስሐ እንዳይመለስና የሚመጣውን ቅጣቱ ለመቀበል ተረጋግመው መሪያቸውን
‎ሴሚሃዛን መርጠው በየአቅጣጫው ተበታትነዋል።

‎ጀለስ Fareast ነበር የደረሳት።የስልጣን የአካባቢ ተዋረድ እዛም አለ(4ኛ ነው ከመሪዎቹ በስልጣን ተዋረድ)እነ ሌግዎን በእስራኤል የፋርሱ ልዑል በመካከለኛው ምስራቅ እነ ጠቋር እዚህ እንዳሉት ሁሉ የየራሳቸው አለቃና ዲፓርትመንት አለ።ጵንሙኤል ከሰማያት እውቀቱ ለሰው ልጆች ደምበቅ አድርጎ ቀድቶ አስጎነጫቸው

‎የጽሕፈት መሣሪያዎች፡ ሰዎችን በቀለምና በወረቀት እንዴት መጻፍ እንደሚችሉ አሳየ።

‎ምስጢራትን መግለጥ፡የጥበብን ምስጢራት ሁሉ ለሰዎች ዘረገፈ።

‎ክፉና ደጉን ማሳወቅ፡ ለሰው ልጆች "መራራውንና ጣፋጩን" (ጥሩና መጥፎውን) ለይተው የሚያውቁበትን የሞራል መለኪያ አስተማረ።

‎ቻይኖቹ በእጅ ፅሑፍ ቀደምትነት የሚታወቁት ለዚህ ነው።‎የእያሱን ፀሐይን መገዘት በራሳቸው ቋንቋና ግዜ ፅፈው‎አስቀምጠውታል።ከሌላ ምንጭ መመርመር ለፈለገ ‎ይሄ ባይተዋር መገለጥ ነው።

‎ሌሎች አጋንንት የገለጧቸው ምስጥሮች

‎ዓዛዝኤል (Az**el): ሰይፍ፣ ቢላዋ፣ ጋሻ፣ የብረት ሥራ እና የአይን ኩል (መዋቢያዎችን) አስተማረ።

‎ሴሚሃዛ (Semjaza): መተትን (ጥንቆላን) እና የዕፅዋትን ምስጢራዊ ጥቅሞች አስተማረ።

‎ባራቅኤል (Baraqiel): የኮከብ ቆጠራን (Astrology) አስተማረ።

‎ኮካብኤል (Kokabel): የከዋክብትን ምልክቶችና አቀማመጥ ማንበብን አስተማረ።

‎ሕዝቅኤል (Ezeqeel): ስለ ደመናት እና ስለ አየር ሁኔታ መተንበይ አስተማረ።

‎አራቂኤል (Araqiel): የምድርን ምልክቶች (የመሬት መንቀጥቀጥንና የምድርን ምስጢር) ማወቅን አስተማረ።

‎ሻምሺኤል (Shamsiel): ስለ ፀሐይ ምልክቶችና ወቅቶች መለዋወጥ አስተማረ።

‎ሳሪኤል (Sariel): ስለ ጨረቃ ጉዞ እና የወራት አቆጣጠር አስተማረ።

‎ጵኔሙኤል (Penemue): በብዕርና በቀለም መጻፍን እንዲሁም የጽሕፈት ጥበብን አስተማረ።

‎ወደቀደመ ነገራችን ስንመለስ የጵንሙኤል የፅሕፈት ጥበብን ለሰው ልጆች ማስተዋወቅ አልነበረም የተኮነነው ‎እራሱ ሔኖክም በፅሑፍ አይደል የደረሰን ግን ከመጻፍ በፊት እውቀት በቃል ትውፊት ይተላለፍ ስለነበር በሰው ማስታወስ ችሎታና በማኅበረሰቡ ታማኝነት ላይም ይመረኮዝ ነበር። መጻፍ እውቀትን የተረጋጋና የማይለዋወጥ አደረገው፤ ነገር ግን ሐሰትንም እንዲሁ አስቀምጦ አስጠበቀ። በዚህም ምክንያት ሥልጣን መረጃን በሚቆጣጠሩ እጆች ውስጥ ወደቀ።ይህም ‎የእብሪትና የጥፋት መነሻ መሆኑ ነው ያልተፈለገው።

Eprem Jemal abdu ✍️

ማንበብ_ሙሉሰው_ያደርጋል 100%
ቅኔ ሚዲያ
በቴሌግራም በአይን ብቻ ሳይሆን በጀሮም የሚነበቡ መፅሐፎች አሉ ጎራ በሉ 👇👇
https://t.me/manebebmulusewyaderegal

የፊልም እውነታዎች - ፪🎬The Godfather-ከስክሪን ጀርባ የነበረው የስቱዲዮ ጦርነት እና እውነተኛው ማፊያ!ዛሬ በሲኒማ ታሪክ ውስጥ ቁጥር አንድ ተደርጎ የሚወሰደው The Godfather...
27/08/2026

የፊልም እውነታዎች - ፪
🎬The Godfather-ከስክሪን ጀርባ የነበረው የስቱዲዮ ጦርነት እና እውነተኛው ማፊያ!
ዛሬ በሲኒማ ታሪክ ውስጥ ቁጥር አንድ ተደርጎ የሚወሰደው The Godfather (1972) ፊልም ሲሰራ የስቱዲዮው የበላይ ሃላፊዎች ፊልሙ እንዲሰራ ቢፈልጉም፤ዳይሬክተር ፍራንሲስ ፎርድ ኮፖላ የሚያስበውን አይነት ግዙፍ፣ውድ እና ጥበባዊ ፊልም እንዳይሰራ ግን ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም።ቀለል ያለና ርካሽ የጋንግስተር ፊልም እንዲሆን ስለፈለጉ ዳይሬክተሩን ለማባረር እስከማሰብ ደርሰው ነበር።
የፊልሙ 'አዘጋጆች' ያጋጠሟቸው ዋና ዋና ፈተናዎች፦
🚫ተዋንያኑን በፍጹም አንቀበልም!
የስቱዲዮው (Paramount Pictures) ሃላፊዎች Marlon Brando አዛውንቱን ቪቶ ኮርሊዮኔን እንዲተው በፍጹም አልፈለጉም።ምክንያቱም ብራንዶ በወቅቱ "አብረውት ለመስራት አስቸጋሪና ስሙ የጠፋ" ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው።አል ፓቺኖ (Al Pacino) ደግሞ "አጭርና የማይታወቅ ተዋናይ ነው" በማለት ፈጽመው አልተቀበሉትም ነበር።
የወሰዱት አስደናቂ እርምጃ፦
ዳይሬክተር Francis Ford Coppola ግን አቋሙን አልቀየረም።ማርሎን ብራንዶ በጉንጩ ውስጥ ጥጥ ከቶና የፊት ገጽታውን ቀይሮ በቪዲዮ የቀረጸውን አስደናቂ የትወና ሙከራ (Audition Tape) ለስቱዲዮው ባለቤቶች በማሳየት አሳመናቸው።አል ፓቺኖንም ተከራክሯቸው አስቀረው።
🔫 ከእውነተኛው የኒውዮርክ ማፊያ ጋር የተደረገ ውል!
በወቅቱ በኒውዮርክ ይንቀሳቀስ የነበረው እውነተኛው የጣሊያን ማፊያ ቡድን (Italian-American Civil Rights League) ፊልሙ እንዲቀረጽ አልፈለገም ነበር።የቀረጻ ቁሳቁሶችን መስረቅ፣አዘጋጆቹን ማስፈራራት እና የቀረጻ ቦታዎችን መዝጋት ጀምረው ነበር።
የተወሰደው መፍትሄ፦
የፊልሙ ፕሮዲዩሰር Al Ruddy ከእውነተኛው የማፊያ መሪ (Joe Colombo) ጋር በአካል ተገናኝቶ ተወያየ።ማፊያው አንድ ሁኔታ ብቻ አስቀመጠ፦"በፊልሙ ስክሪፕት እና ንግግር ውስጥ «Mafia» ወይም «Cosa Nostra» የሚል ቃል ጨርሶ እንዳይነሳ!" ፕሮዲዩሰሩ ተስማማ፤ቃላቱ በሙሉ ከስክሪፕቱ ተሰረዙ። ከዚያ በኋላ ማፊያው የቀረጻውን ደህንነት እራሱ መጠበቅ ጀመረ።
በሲኒማ ታሪክ እጅግ ድንቅ የሚባለው ይህ የጥበብ ስራ የተፈጠረው በፍጹም ሰላም እና ምቾት ውስጥ ሳይሆን በስቱዲዮ ጫና፣በተዋንያን ፍልሚያ እና ከእውነተኛው የማፊያ አለም ጋር በተደረገ አደገኛ ድርድር ነው።
አዘጋጁ ኮፖላ ይሄን ፊልም አዘጋጅቶ ሲጨርስ የ33 አመት ወጣት ነበር።

ቅኔ ሚዲያ

"ለሌሎች ነፃነት የሚነፍጉ ሰዎች ለራሳቸውም ነፃነት አይገባቸውም!"- አብርሀም ሊንከን በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸውና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን ...
22/08/2026

"ለሌሎች ነፃነት የሚነፍጉ ሰዎች ለራሳቸውም ነፃነት አይገባቸውም!"- አብርሀም ሊንከን
በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸውና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን ለነጻነትና ለሰብአዊ መብት መከበር የነበራቸው ቁርጠኝነት ዛሬም ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።

ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን ሀገራቸውን በአስቸጋሪው የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በብቃት በመምራት እና የባርነት ስርዓትን በመደምሰስ ረገድ የመሪነቱን ሚና ተጫውተዋል።

"ለሌሎች ነጻነትን የሚከለክሉ ሰዎች ለራሳቸውም ነጻነት አይገባቸውም" በማለት የተናገሩት ንግግር የነጻነት የእኩልነትና የፍትህ መሰረታዊ መርህ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ይገኛል።

የአብርሃም ሊንከን ንግግሮችና ጠንካራ አመራር ለአሜሪካውያን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ የፍትህና የነጻነት ታጋዮች ትልቅ ብርታት ሲሰጡ ኖረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
GetuTemesgen

ቅኔ ሚዲያ
በቴሌግራም ጎራ በሉ
👇👇👇
https://t.me/manebebmulusewyaderegal

https://t.me/djbarkmusic

19/08/2026

" ምሁርነት እና ዘረኝነት አብሮ አይሄድም "

ፕ/ር ሀይሌ ገሪማ
----------------------------------

«እግዚአብሔር ነኝ ካላልክ በስተቀር ይኽን እርስበርስ የሚጠፋፋ ዛራም (ዘረኛ) ትውልድ አስተምሬ አድናለሁ አትልም። ለዚህ ትውልድ ብዬ እነሱ የሚፈልጉትን አይነት ፊልም አልሰራም። ምሁርነትና ዘረኝነት አብሮ አይሄድም። እሳት የላሰ፣ ምርጥ ትውልድ ይወለዳል፤ ይመጣል። እነሱ ሲመጡ እንዳይሳሳቱ መንገዱን (map) ማሳየት አለብህ፤ እምነትህን በጽሑፍ ይኹን በፊልም ቀርጸህ ለእነሱ ማስተላለፍ አለብህ። ለእነሱ ነው ፊልም የምሠራው።»

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ

ማንበብ_ሙሉሰው_ያደርጋል 100%
በቴሌግራም ጎራ በሉ 👇👇
https://t.me/manebebmulusewyaderegal

19/08/2026


#ፍቅርእስከመቃብር ...

17/08/2026

አብዝተህ ....

= ስለ መሞትህ ሳይሆን ስለ መኖርህ አስብ !
= ስለ መራብህ ሳይሆን ስለ መጥገብህ አስብ !
= ስለ ማጣትህ ሳይሆን ስለ ማግኘትህ አስብ !

የሁሉንም አመጣጡን ካወቅኸው አካሄዱም አይጠፋህምና ! ትልቁ ነገር ግን ...." አጥፊ ቀን አልሚ ይመስላል ! " እንዳይሆን ነገሩ ።

ከሰው የተጣላ በሰው ይታረቃል ። ከራሱ የተጣላ በማን ይታረቃል ። ጨርሶም ከአምላኩ ጋር ይጣላል እንጅ !!!!

ደገኛው ነኝ

“ እኛ ኢትዮጵያውያን ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው፡“ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናው...
17/08/2026

“ እኛ ኢትዮጵያውያን ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው፡
“ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም፡፡ በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም፡፡ የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው፡፡ በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው፡፡ በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም፡፡ መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው፡፡ የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው፡፡ ያለ ጭንብል እናስቀይማለን ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም፡፡ ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!''
በዓሉ ግርማ ፥
የቀይ ኮከብ ጥሪ ፥ ገፅ 234

ቅኔ ሚዲያ
በቴሌግራም ብዙ ነገር ታተርፋላችሁ
👇👇👇👇👇
https://t.me/good_mind_Barklign_mulugeta

Address

Bole Addis Ababa
Addis Ababa
MOJITO

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቅኔ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share