31/12/2025
ልዩ መረጃ ፡
ከሰሞኑ በጃልመሮ የሚመራዉ የሸኔ ቡድን ከዘመነ ካሴ ጋር ከሚመራዉ የፋኖ ቡድን ጋር የነበራዉን ግንኙነት እና ለ 3 ቀን የተደረገዉን ንግግር እንዲሁም ከስምምነት በደረሱባቸዉ ጉዳዩች ጋር በተገናኘ በሸኔ ካምፕ ዉስጥ ከፍተኛ ዉጥረት መፈጠሩ ምጮች መረጃ አጋርተዋል። በተለይ የማዕከላዊ(በጃል አብበዲ የሚመራ) ዞን እና የደቡብ ዞን (በጃል አቦዬ) የሚመራዉ ጎራ ከጃል መሮ ጋር ያለዉን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማቋረጣቸዉን እና ከፋኖ ጋር ስምምነት ከፈጠረዉ ቡድን ጋር መስራት እንደማይችሉ በመስማማት ፥ ሌሎች አማራጮችን ማመቻቸት በሚችሉበት ሁኔታ ለመመካከር ቀጠሮ መያዛቸዉ ታዉቋል ። በተለይ በጃል አቦዬ የሚመራዉ የደቡብ ዞን ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ያልሆኑ ንግግሮችን እያደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ይህንን አጋጣሚ በመደበኛ መልኩ ለማስኬድ አደራዳሪዎች ተመርጠዉ እና የማዕከላዊ ዞን በሚቀላቀልበት ሁኔታ ላይ ከጃል አብዲ ጋር በቃል ደረጃ ስምምነቶች መኖራቸዉ ተጠቁሟል።
አዝማሚያ ፦ ምናልባት ይህ እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ እና ከ85% በላይ የሸኔ ታጣቂ ቡድን በሰላማዊ መንገድ ከጫካ ሊመለስ እንደሚችል ይገመታል። በደቡብ ሱዳን ድንበር የሚገኛዉ የጃል መሮ ማዘዣ ጣቢያ በቅርቡ በደህንነት ክትትል እንደተገኘ እና የድሮን ጥቃት እንደተፈፀመበት አይዘነጋም።