25/10/2026
የሀገርና የህዝብ ጠላቶች የሽብር ሴራቸውን በተግባር እያሳዩ ነው!
ኢትዮጵያን ለማፍረስ በግልጽ የተጣመሩት እንደ ሸኔ፣ ፋኖ እና ህወሀት ያሉ የጥፋት ኃይሎች ከዚህ ቀደም በተናጠልና በመናበብ ንጹሐንን ሲጨፈጭፉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይባስ ብለው ግልጽ ወደሆነ የሽብር ተግባር ተሰማርተዋል።
እነዚህ ቡድኖች የፈጸሙትን የንጹሐን ግድያ በመንግሥት ላይ በማላከክ፣ በህዝቦች መካከል መጠራጠርን በመፍጠር፣ እንዲሁም ለጥፋት ድርጊታቸው የሃይማኖትና የብሔር ግጭት መልክ ለመስጠት ሲያሴሩ ቆይተዋል።
በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ፣ ሽርካ ወረዳ፣ ቢርቢሩ ጮሌ ቀበሌ በንጹሐን ዜጎች ላይ የፈጸሙት ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊት የዚሁ ጸረ-ህዝብ ሴራቸው ማረጋገጫ ነው። የህዝባችንን ሰላምና የዘመናት አብሮነት ለማፍረስ የሚያደርጉትን ይህንን የሽብር ዘመቻ ሁላችንም በጋራ ልንቆመውና ልናወግዘው ይገባል!