Eden Eden

Eden Eden Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eden Eden, Grocers, Addis, Addis Ababa.

22/08/2026
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህገ ወጥ ተግባራትን ከመከላከል በተጨማሪ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን በልዩ ትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ። ሀምሌ 14/2...
21/07/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህገ ወጥ ተግባራትን ከመከላከል በተጨማሪ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን በልዩ ትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ሀምሌ 14/2018 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገበያ ማረጋጋት ፣ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ግብረ ሀይል የ1 ወር ከ15 ቀን እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የግብረ ሀይሉ አባላት በተገኙቡት ገምግሟል።

ውይይቱን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የተረጋጋ የገበያ ስርዓት በመፍጠር ህጋዊ የግብይት ሂደት እንዲሰፍን በልዩ ትኩረት በመስራት የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ መሆናቸውን በመግለጽ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም ህገወጥ ተግባራትን መከላከል፣ መደበኛ ያልሆኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ስርዓት ማስያዝ ፣ የንግድ ቁጥጥርን ስርዓትን ማጠናከር እንዲሁም ሌሎች ህገወጥ ተግባራትን በቅንጅት መከላከል በልዩ ትኩረት መፈጸም እንደሚገባው የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመድረኩም የምርት አቅርቦትን በማሳደግና ህገወጥ ንግድን ስርዓት በማስያዝ የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑንና በቀጣይም በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግ ተብራርቷል።

በመጨረሻም በክ/ከተማው ህገ_ወጥ ተግባራትን ከመከላከል አንጻር የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ በማካሔድ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የአዲስ አበባ ለውጥ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ያደሰችበት ጉዞ ነውኢትዮጵያ ታሪካዊ የአፍሪካ መዲናነቷንና ዲፕሎማሲያዊ ገጽታዋን በአዲስ መልክ በመገንባት፣ በዓለም አቀፍ ...
21/07/2026

የአዲስ አበባ ለውጥ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ያደሰችበት ጉዞ ነው

ኢትዮጵያ ታሪካዊ የአፍሪካ መዲናነቷንና ዲፕሎማሲያዊ ገጽታዋን በአዲስ መልክ በመገንባት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለመሆን በቃች። ​በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከናወኑት ግዙፍ ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ለአለም አቀፍ ጉባኤዎች ይበልጥ ማራኪና ዝግጁ አድርገዋታል።

አድዋ ድል መታሰቢያ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የአዳራሽና ኤግዚቢሽን ማዕከል፣ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አዳራሽና አቪዬሽን ከተማ፣ ግዙፍ አየር ማረፊያዎችንና መስተንግዶዎችን ጨምሮ የተከናወኑ የትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ ማሻሻያዎች ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል። በተጨማሪም ወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ፓርክና የዓመታት የሸገር ውበት ፕሮጀክቶች ለአለም አቀፍ እንግዶች ምቹ፣ ጽዱ እና አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር የመዲናዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረዋል።

24/06/2026
የሸገር ዳቦ ምርት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  የሸገር ዳቦ አቅራቢ ማህበራት ለማህበረሰቡ የሚያቀርቡትን ምርት በጥራትና በተደራሽ...
22/06/2026

የሸገር ዳቦ ምርት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሸገር ዳቦ አቅራቢ ማህበራት ለማህበረሰቡ የሚያቀርቡትን ምርት በጥራትና በተደራሽነት ማቅረብ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ ላይ ማህበራቱ የዳቦ ምርትን በአግባቡ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት የተመካከሩ ሲሆን ማህበራቱ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትም የጋራ ምክክር ተደርጓል።

በተጨማሪም ማህበራቱ በስራ ሂደት ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ ውይይት ተደርጓል።

ዉይይቱን የመሩት የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የአቅርቦት ሰንሰለቱን ውጤታማ ለማድረግና የዳቦ ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማህበራቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቀዋል።

ጃዋር ዛሬ ያሳያቸው የምርጫ ካር ሁሉም ውሸት መሆናቸው ተጋልጧልሰውዬው ሁሌም ስራው እንደዚህ ህዝብን ማጭበርበር ነው። በውስጥ እንደተላከለት አድርጎ የለቀቃቸው ሁሉም ፎቶዎች የቆዩ እና ከአም...
25/05/2026

ጃዋር ዛሬ ያሳያቸው የምርጫ ካር ሁሉም ውሸት መሆናቸው ተጋልጧል

ሰውዬው ሁሌም ስራው እንደዚህ ህዝብን ማጭበርበር ነው። በውስጥ እንደተላከለት አድርጎ የለቀቃቸው ሁሉም ፎቶዎች የቆዩ እና ከአምስት አመት በፊት በሶሼል ሚዲያው ልክ እንደ እሱ ለፕሮፓጋንዳ ሲጠቀሙበት የነበረ ነው። ጀዋር መሃመድ በጣም የዘቀጠ እና በውሸት ላይ ብቻ ጊዜውን የሚያጠፋ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማሳያ የለም።

ዛሬ እና ትላንት ስለምርጫው የሚለቃቸው ነገሮች ውሸት መሆናቸውን ያጋለጡ መረጃዎች ይሄው ሁሉም ሰው እያየው ነው። የሚገርመው ነገር ይሄ ሰው ብዙ መረጃ በውስጥ ደረሰኝ የሚለው ሁሉም ውሸት መሆናቸው ነው።

ምርጫውን ለማንቋሸሽ ይሄን ሁሉ እርምጃ ሄዷል። ህዝብ በእሱ ውሸት ምክንያት አንቅሮ እንደተፋው ግልፅ ነው። ውሸት መቼም መቼም አያሻግርምተ በጀዋር ማወቅ ይቻላል።

የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል ይውደምበአንድ በኩል ለሺዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገነባ፣ ለሕፃናትና ለደካሞች የምገባ ፕሮግራም የሚዘ...
20/05/2026

የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል ይውደም

በአንድ በኩል ለሺዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገነባ፣ ለሕፃናትና ለደካሞች የምገባ ፕሮግራም የሚዘረጋ እና ዛሬ በጥቅሉ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ደግሞ ከ370 በላይ አባወራዎችንና እማወራዎችን የቤት ባለቤት አድርጎ የእንባ አባሽ የሆነ የከተማ አስተዳደር አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይሄ ሁሉ መልካም ስራ ሲሰራ እንቅልፍ የሚያጣ፣ የሰዎችን ደስታና የከተማዋን እድገት መሸከም ያቃተው አፍራሽ ኃይል አለ።

ዛሬ የተረጨው የኮዬ ፈጬ እና የአራብሳ ሳይት የሱቆች የውሸት ወሬ፣ ከተማዋ እያስመዘገበችው ያለውን ተከታታይ የልማት ድሎች ለመሸፈንና የህዝብን ልብ በጥርጣሬ ለመሙላት የተወረወረ የክፋት አረር ነው። አስተዳደሩ የዜጎችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በተግባር ሲመልስ፣ እነሱ ግን በወሬና በሃሰት ክስ ህዝብን ለማደናገር ይሮጣሉ።

ይህ የፈጠራ ዘገባ ተቃዋሚዎች ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ምንም ዓይነት አማራጭ ሃሳብ እንደሌላቸውና ስራቸው በሙሉ መልካም ስራዎችን ማጠልሸት ብቻ መሆኑን ያረጋገጠ ነው። የ370 ዜጎች የቤት ቁልፍ የመረከብ ደስታና የ20 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተስፋ በወሬ አይሸፈንም፤ የከተማው አስተዳደርም በእንደዚህ ዓይነት የፌስቡክ አሉባልታዎች ሳይገታ የጀመረውን የልማትና የፍትሃዊነት ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም የነዚህን አካላት አፍራሽ ዓላማ በመገንዘብ፣ ከወሬ ይልቅ ለመሬት ላይ እውነታዎችና ለከተማዋ ብልጽግና ትኩረት ሊሰጡ ይገባል።

15/05/2026

Address

Addis
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eden Eden posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category