Ati Eenyu

Directions

Ati Eenyu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ati Eenyu, Grocers, Addis Ababa.

30/07/2026

አዲሷንና የበለጸገችዋን ኢትዮጵያ በጋራ የመገንባት ታሪካዊ አሻራ!

የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክቶች በአገራችን የተጀመረውን አጠቃላይ የብልፅግና ጉዞ በተግባር ያረጋገጡ፣ ኢትዮጵያን ወደላቀ የዘመናዊነትና የውበት ከፍታ ያሻገሩ ታላላቅ የታሪክና የልማት አሻራዎች ናቸው። በብልፅግና ፓርቲ መሪ እሳቤና ቁርጠኝነት የተቀናጀው ይህ ንቅናቄ፣ የከተሞቻችንን መሠረተ-ልማት ከመቀየርና የትራፊክ ፍሰቱን ከማቃለል ባለፈ፤ የፓርቲያችን እሳቤ የሆነውን ሰው ተኮር ልማት በግልጽ ያሳየ ነው። ለዜጎች ምቹ የሆኑ የእግረኛ መሄጃዎችን፣ አረንጓዴ ስፍራዎችንና የብስክሌት መንገዶችን በመፍጠር የከተሞች ሕይወት ጥራት ላይ መሠረታዊ የጥራት ለውጥ አምጥቷል።

በተለይም የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የኢኮ-ፓርክ ሥራዎች ከዚህ ቀደም የቆሻሻና የሥጋት ምንጭ የነበሩ ቦታዎችን ወደ ውብ፣ ዘመናዊና መስህብ ወደሆኑ መዝናኛዎች በመቀየር አዲስ አገራዊ ተስፋ ፈጥረዋል። ይህ ተግባር የአካባቢ ጥበቃን፣ የአረንጓዴ አሻራን እና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የመቋቋም የፖሊሲ ግቦቻችንን ከመተግበሩ ባሻገር፣ ለዜጎች ጤናማና የአእምሮ እረፍት የሚሰጡ የጋራ መኖሪያ ስፍራዎችን አበርክቷል።

በተጨማሪም በለውጡ አመራር የተመዘገቡት እነዚህ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች የከተማ ውበትን ከማድመቅ ባለፈ፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝምና ለሰፊው ወጣት የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአገራዊ የኢኮኖሚ እቅዳችን አዲስ የብልፅግና መነቃቃትን ሰጥተዋል። ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በገዛ አቅሟና በፈጣን አፈጻጸም ግዙፍና ጥራታቸውን የጠበቁ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እውን የማድረግ አቅምና ቁርጠኝነት እንዳላት ለዓለም ያሳየችበት የታሪክ ማረጋገጫ ነው።

የተገነቡትን ውብና ዘመናዊ ኮሪደሮችና መዝናኛ ፓርኮች በአግባቡ መጠበቅ፣ መንከባከብና ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ደግሞ የሁላችንም ባለቤትነትና የዕለት ተዕለት የዜግነት ኃላፊነት ሊሆን ይገባል። በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት አዲስ ምዕራፍ የከፈተችውና የገጽታ ግንባታዋ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰችው አዲሲቷ ኢትዮጵያ፣ በሕዝቦቿ የተቀናጀ አቅም የ አፍሪካ የብልፅግናና የከፍታ ተምሳሌት ሆና መጓዟን ትቀጥላለች!

30/07/2026

ለሀገራችን ልምላሜ! ለከተማችን ውበት! አረንጓዴ አሻራ የአብሮነታችን ድምቀት!

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም 4 ቀናት ብቻ ቀሩት!

ጎረቤት ሀገራትን እና ሌሎችንም የሚያረሰርሱ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች እያሏት የተጠማች፣ ለም አፈር እያላት ተመፅዋች፣ ሆና የኖረችውን የሀገራችንን ታሪካዊ ስብራቶች እየጠገኑ ከሚገኙ ውጤታማ እርምጃዎች አንዱ ነው፤ አረንጓዴ አሻራ፡፡

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሸቲቭ መተግበር ከጀመረበት 2011 ዓ.ም ጀምሮ የህዝባችን ችግኝ የመትከል ብቻም ሳይሆን ችግኞችን የመንከባከብ ባህል በእጅጉ ተሻሽሏል፡፡ በተጨባጭም የሀገራችን የደን ሀብት ከመራቆት ወደ ማንሰራራት ተሸጋግሯል፡፡

ለሀገራዊ ዓላማ በአብሮነት መሰባሰቢያ፣ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን ማጥበቂያ፣ የጋራ ብሩህ ነገን መገንቢያ የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የህዝባችንን አብሮነት አጠናክሯል፡፡

የሀገርን ጉዳይ ከግል እና ከቡድን ፍላጎቶች በማስቀደም ብዝሀ ማንነቶች፣ ብዝሀ ሀሳቦች በአንድነት የሚስተጋቡበት በመሆኑ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታም ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነው፡፡

የምንተክላት እያንዳንዷ ችግኝ የነገ ልምላሜያችን፣ የነገ ጥላችን እንዲሁም የነገ ውበታችን ናት፡፡ ተፍጥሮ በብዙ መልኩ አሟልታ ሰጥታናለች፡፡ በአግባቡ መያዝ ስላልቻልን ድርቅን ለመሳሰሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች በእጅጉ ተጋልጠን ቆይተናል፡፡ አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን ከነበረችበት ከፍተኛ የመራቆት ደረጃ በማውጣት ለዓለም የአየር ንብረት መጠበቅ ተምሳሌት ያደረገ ተግባራዊ እርምጃ ነው፡፡

በጥቂት ዓመታት ውስጥ 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል እራሱን የቻለ የገዘፈ ታሪክ ነው፤ ከ4 ቀናት በኋላ የምናካሂደው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ደግሞ አይበገሬነታችንን ጭምር ለዓለም የምናሳይበት ታሪካዊ ሁነት ነው፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

29/06/2026

በተቀናጀ የሕዝብ ተሳትፎና በብልፅግና ፓርቲ መሪነት ሰላማችንን እናጸናለን!

የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የምናደርገው ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን መገንባት ስንችል ነው። ፓርቲያችን ብልፅግና፣ ሰላምን የሁሉም መስተጋብሮች መነሻና በማድረግ ፣ በከተማችን የተጀመረውን የለውጥና የሰላም ጉዞ ይበልጥ ለማጠናከር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሰላም ሠራዊት ስምሪትና የብሎክ ስታንዳርዳይዜሽን የመስክ ምልከታ ተካሄደ::

የፓርቲያችንን የሰላም እሴቶች በየአካባቢው ለማስረጽ፣ የሰላም ሠራዊት ስምሪት መስጠት ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ከሰላም ሠራዊቱና ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት፣ የብልፅግና ጉዟችንን የሚያስተጓጉሉ ወንጀሎችን ቀድሞ የመከላከል፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበርና የተረጋጋ የኑሮ ሁኔታ የመፍጠር የፓርቲያዊና የዜግነት ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።

ከሰምሪቱ መድረክ በመቀጠል በየደረጃው የሚገኙ የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ የፓርቲና የመንግሥት አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት እንዲሁም የሰላም ሠራዊት አባላት በተገኙበት ጠንካራ የሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የተቀናጁ የሞዴል ብሎኮች ስታንዳርዳይዜሽን (Model Blocks Standardization) ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት የመስክ ምልከታ ተደርጓል። ይህም የፓርቲያችንን የአደረጃጀት ጥራትና የለውጥ አቅም በተግባር ያሳየ ነው።

29/06/2026

የዜጎች ኑሮ የማሻሻል ማህበራዊ ፍትህን የማንገስ ጉዞ፦ በቅጠል ተራ

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እሳቤ መነሻውም መድረሻውም “ሰው” ነው። ለዘመናት በከተማችን እምብርት ላይ ሆነው፣ ለሰው ልጅ ክብር በማይመጥን የኑሮ ሰቆቃና በከፋ ድህነት ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ዜጎች እውነተኛ የሰብአዊ ክብርና የፍትሃዊነት ትርጉምን በተግባር ማሳየት የፓርቲያችን ቀዳሚ የትግል መስመር ነው።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የቀድሞው “ቅጠል ተራ” ሰፈር ለሰው ልጅ ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ ለከፋ አደጋ የተጋለጠ፣ ዜጎች በጨለማና በኩራዝ የሚማቅቁበት የነበረና ያለፉት ሥርዓቶች የፈጠሩት የኢ-ፍትሃዊነትና የከተማ ነዋሪዎችን ያገለለ አድሏዊ አሰራር ትልቅ ማሳያ ነበረ። ብልፅግና ፓርቲ ግን ይህንን የታሪክ ጠባሳ ለመቀየር ቆርጦ ተነስቷል! ችግሩን በየመድረኩ በማውራትና ሳይሆን፣ መፍትሄ ላይ በማተኮር የዜጎችን ህይወት ከግርጌው ለመቀየር በወሰድነው የፓርቲያችን የሕዝብ ወገንተኝነት ቁርጠኝነት “ቅጠል ተራን” ወደ ውብ፣ ምቹና ጽዱ የመኖሪያ መንደርነት የመቀየር ታላቅ የልማት ምዕራፍ ከፍቷል።

ግንባታው ከተጀመረ በወራት ውስጥ ባለ 9 ወለል ህንጻዎች ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መድረሳቸው፣ ፓርቲያችን የሕዝብን አመኔታ በተግባር የመመለስና የገባውን ቃል በፈጣን አፈጻጸም የማረጋገጥ ቁመናን ያሳያል። ግንባታው መኖሪያ ቤቶችን ብቻ ሳይሆን የንግድ ማዕከላትን፣ እንዲሁም የሕፃናት መጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ያካተተ የተቀናጀ ልማት መሆኑ የፓርቲያችንን “ሁለንተናዊ ብልጽግና” ራዕይ ፍንትው አድርጎ ያሳያል::

ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን የልማቱ ቀዳሚ ተጠቃሚ በማድረግ፣ ክብራቸው ተጠብቆ የከተማዋ እውነተኛ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ የፓርቲያችን የማህበራዊ ፍትህ መርህ ማሳያ ነው።

ይህ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በ“ቅጠል ተራ” የታየው ተጨባጭ ለውጥ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ አገልጋይነት መለያ፣ የትውልድ መገንባት ስራ እና ማህበራዊ ፍትህን የማንገስ ጉዟችን የማይቀለበስ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ኩሩ ስራችን ነው!

፦

29/06/2026

ቀበና! በትጉህ እጆች ትንሳኤው ተበስሯል! ወደ ቀደመ ከፍታው ተመልሷል!

ጠቢባን የተቃኙለት ፣ ታዳጊዎች የዋኙበት ፣ የብዙዎች የልጅነት ትውስታ ፣ አዲስ አበባ ሲባል ቀድመው ከሚመጡ ወንዞች አንዱ ! ቀበና !

ባለግርማ ሞገሱ የቀበና ወንዝ በአያያዝ ጉድለት የክረምት ጎርፍ ብቻ ወደ መሆን የተሸጋገረበት የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል።

ለብዙ አገልግሎት ሲጠጥ የነበረው የቀበና ወንዝ በጊዜ ሂደት አይደለም ለመዋኛ ለእይታም ከማይመችበት ሁኔታ ደርሶ እንደነበር የትናንት ትውስታችን ነው፡፡

በተለወጠ አስተሳሰብ፣ በተሻጋሪ እይታ ፣ በዳበረ የስራ ባህል ውብ አበባ መሆን እንደጀመሩት አሮጌ የከተማችን መንደሮች ፣ ቀበናን የመሳሰሉ ወንዞቻችንም የጉስቁልና ታሪካቸው ተሽሮ የማንሰራሪያ ጊዜአቸው ተበስሯል።

የአዲስ አበባ ከፍታ ከሆነው ከታሪካዊው የእንጦጦ ተራራ የሚመነጨው ታሪካዊው ወንዝ ወደ ቀድሞ ከፍታው ተመልሷል።

ታዳጊዎች የሚዋኙባቸው የነበሩ የቀበና ወንዝ የተለያዩ ቦታዎችአሁን ላይ የቆሻሻ ክምራቸው ተወግዶ መለስተኛ ግድቦች ሆነዋል።

በተለይም ቀበና አደባባይ ወይም ኮከበ ፅባህ ት/ቤት አካባቢ የተፈጠረውን መለስተኛ ግድብ የተመለከተ የከተማችን ነዋሪ እንዲህም ይቻላል እንዴ ? ብሎ እንደሚጠይቅ ጥርጥር የለውም።

በቦታው ከተፈጠረው ግዙፍ ግድብ ባሻገር ለብዙዎች የስራ ዕድል የፈጠሩት የንግድ ማዕከላት አይንን ገለጥ አድርጎ መስራት ከተቻለ ታምር መስራት እንደሚቻል አመላካች ናቸው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ሲያስጀምሩ በወንዝ ዳር ፕሮጀክት እንዲለማ ባስቀመጡት አቅጣጫ የለማው የእንጦጦ - ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት የወንዙን ህልውና ከማስጠበቅ ባሻገር የከተማችንን ተምሳሌታዊ ጉዞ አንድ ደረጃ ወደ ፊት አራምዷል።

የነዋሪዎችን ህይወት በሚያሻሽል መልኩ አዲስ አበባን ውብ አበባ ለማድረግ የተጀመረው ቅንጅታዊ ርብርብ በከተማችን ውስጥ የሚፈስሱ ወንዞች ተፈጥሯዊ ንፅህና እንዲመለስ በማድረግ ለነዋሪዎቻችን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡበትን ዕድል ፈጥሯል፤ ቀበና ወንዝ አንዱ ማሳያ ነው።

የወንዝ ዳርን ተከትለው በተሰሩ ቤቶች የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ብቻም ሳይሆኑ ሌላውም የከተማችን ነዋሪ በአንድም በሌላም በወንዞች መበከል ለተለያዩ የጤና እክሎች ተጋላጭ ሆነው ቆይቷል።

ከምንም በላይ ግን በወንዙ ዳርና ዳር የሚኖሩ ነዋሪዎች ከጤና እክል በተጨማሪ በተለይም በክረምቱ ወራት ለሚፈጠር የጎርፍ እና የአፈር መሸርሸር አደጋ ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነበር።

መነሻውን የከተማችን ከፍታ ከሆነው ከእንጦጦ ተራራ ያደረገው ፣ 87 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት የሚሸፍነው ፣ 10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ግዙፉ የእንጦጦ - ቀበና ወንዝና የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ወንዙን ብቻም ሳይሆን የስጋት ህይወት ይኖሩ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎቻችንን ታድጓል።

የእንጦጦ - ቀበና ወንዝ እና የወንዝ ዳር ፕሮጀክት የወንዙን ህልውና በመታደግ ለከተማችን ገፅታ ግንባታ ጉልህ ሚና የሚያበረክት የቱሪስት መዳረሻ ማዕከል አድርጎታል።

በአካባቢው ለነበሩ ነዋሪዎችም ከአስቸጋሪና ከስጋት ህይወት በማላቀቅ የተሻለ ምትክ እና ካሳ አግኝተው ለኑሮ ምቹ በሆነ አካባቢ የሚኖሩበትን ሁኔታ መፍጠር አስችሏል።

በገደላማእና የጤና ጠንቅ ፣ የፀጥታ ስጋት ሆነው በቆዩ አስቸጋሪ የቀበና ወንዝ ዳርቻ ቦታዎች የነበሩ ነዋሪዎችም "በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ " እንደሚባለው በአንድ በኩል ብዙ ትዝታ ያሳለፉበት እና የህልውና አደጋ ተጋርጦበት የቆየው የቀበና ወንዝ ለከተማችን ነዋሪ ጥቅም ላይ እንዲውልና ወደቀድሞ ዝናው እንዲመለስ የሚያስችል ልማት በመሰራቱ ፤

በሌላ በኩል ደግሞ በወንዙ መበከልና በአፈር መሸርሸር ምክንያት የስጋት ህይወት ከሚኖሩበት አካባቢ ወጥተው ፣ ተገቢውን ካሳና ምትክ አግኝተው የተሻለ መሰረተ ልማት ወዳለበት አካባቢ በመሄዳቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ መሆኑን ሲናገሩ ይደመጣል።

የብዙዎች የልጅነት ትውስታ ፣ ለነዋሪዎች የንፁህ ውሃ ምንጭ ሆኖ የቆየው የቀበና ወንዝ ተፋሰስ በባለቤትነት በእንክብካቤ ባለመያዙ የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል።

ከነፋሻማው የእንጦጦ ተራራማ አካባቢ ኩልል ብሎ የሚወርደው የቀበና ወንዝ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ፈሳሽ እና ደረቅ ቆሻሻዎች መጣያ እንጅ የተዜመለት ስመ ገናናው ቀበና አይመስልም ነበር።


በተፈጥሯዊና በሰው ሰራሽ መስህቦች ከተዋበው የእንጦጦ ተራራ ተነስቶ ፒኮክ መናፈሻ የሚደርሰው የቀበና ወንዝ ዳር ፕሮጀክት የአካባቢውን ብቻም ሳይሆን የከተማችንን የቱሪስት መዳረሻነት ከፍ አድርጓል።

የተለያዩ ሀገር በቀል እፅዋትን ፣ ለከተማችንም ተጨማሪ የውሃ አቅም የሚሆኑ ምንጮችን ፣ አዕዋፋትን እና እፅዋትን በስሩ የያዘው እንጦጦ እና አካባቢው በቀበና ወንዝ ዳር ፕሮጀክት መለስተኛ የውሃ ግድቦችም ስለተገነቡለት ለከተማችን ነዋሪዎች ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ግልጋሎት ባሻገር ለእፅዋት ፣ ለእንስሳት እንዲሁም ለአዕዋፋት መበራከት ሚናው የጎላ ነው።

በቀበና ወንዝ ዳርቻዎች የተገነቡ መለስተኛ ግድቦች የውሀውን ንፅህና ከመጠበቅ ባሻገርም በጋም ክረምትም የሚፈስ ወንዝ እንዲሆንም ትልቅ አቅም ይፈጥሩለታል።

በትክክለኛ የልማት አቅጣጫ ፣ የትናንት ትውስታን መለስ ብሎ በቃኘ ፣ ነገን አሻግሮ በተመለከተ ሰው ተኮር እሳቤ ፣ ቃልን በተግባር በተረጎመ ትጋት ወደ ነበርነት ተቀይሮ የነበረው የቀበና ወንዝ ዳግም ማንሰራራት ችሏል።

ከእንጦጦ ጀምሮ ያለው የቀበና ወንዝ ዳርቻም አልፎ ለመሄድ ከሚያስቸግር ብክለት ወጥቶ ለአካባቢው እንዲሁም ለከተማችን ተጨማሪ የቱሪስት ማዕከል ሆኗል።

ይህ ደማቅ የታሪክ አሻራ ውጤታማነቱ የሚረጋገጠው በአግባቡ በመገልገል የከተማችንን ፀጋዎች ለመጪው ትውልድ ማሸጋገር ሲቻል በመሆኑ ከዳግም ብክለት መከላከልና መጠበቅ ከሁላችንም ይጠበቃል::

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልን! ይሁንላችሁ!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

29/06/2026
26/06/2026

በአዲስ አበባ ከተማ የክልል ምክር ቤት ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ አብላጫዉን መቀመጫ አገኘ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ-ግብር አካሄዷል፡፡

ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የምርጫ ክልል በተካሄደዉ የ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት አብላጫ መቀመጫ ያገኙትን ተወዳዳሪዎች ይፋ አድርጓል፡፡


በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 የምርጫ ክልሎች ለክልል ምክር ቤት ከቀረቡ 158 መቀመጫዎች መካከል ብልጽግና ፓርቲ 134 መቀመጫዎችን ሲያገኝ ኢዜማ 8 መቀመጫዎችን ማግኘቱን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡

ቦርዱ ይፋ ባደረገዉ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት መሰረት ፡-

👉 የአዲስ አበባ የምርጫ ክልል ብዛት - 10

👉 አጠቃላይ የክልል ምክር ቤቱ መቀመጫ ብዛት - 158

👉 ብልጽግና ፓርቲ - 134 መቀመጫዎች

👉 ኢዜማ ፓርቲ - 8 መቀመጫዎች

👉 አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 4 መቀመጫዎች

👉 ህዳሴ ፓርቲ - 2 መቀመጫዎች

👉የኦሮሞ ነጻነት ግንባር - 2 መቀመጫዎች

👉 ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - 2 መቀመጫዎች

👉 ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት - 2 መቀመጫዎች

👉 የወላይታ ህዝቦች የነፃነት ንቅናቄ - 1 መቀመጫ

👉 የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ - 1 መቀመጫ

👉 የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 1 መቀመጫ

👉 አቶ ዳንኤል ጌታቸዉ ጋረደዉ የግል ተወዳዳሪ - 1 መቀመጫ ማግኘታቸዉን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደዉ 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ 1 ሚሊዮን 957 ሺህ 676 መራጮች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 96 መቶ የሚሆኑት መራጮች በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
AMN

26/06/2026

የህዝብ ድምጽ አሸንፏል፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታለች!

መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲን በማፅናታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

የተከበራችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለፓርቲያችን ብልፅግና የሰጣችሁት ድምፅ የቃል ኪዳናችን ማሰሪያ በማድረግ የጣላችሁብን አደራ በላቀ ስኬት ለመመለስ እንተጋለን።

ይህ ምርጫ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት የሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሻገረበት ደማቅ የታሪካችን አካል ሆኖ ተመዝግቧል ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በተደረገው የከተማ ምክር ቤት ምርጫ፣ ፓርቲያችን ብልፅግና ከጠቅላላው 158 መቀመጫዎች ውስጥ 134፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ23ቱ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ 20 መቀመጫዎችን በማግኘት የህዝብን ሙሉ አመኔታና አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸንፏል።

በሌላ በኩል ከ158 የከተማ ምክርቤት መቀመጫዎች ውስጥ 11 የተፎካካሪ ፓለቲካ ፒርቲዎች 23 የግል ተወዳዳሪ 1 ወንበሮች ያገኙ ሲሆን አዲስ አበባ ከምትወከልበት ከ23ቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ
የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች 2 እንዲሁም የግል ተወዳዳሪ 1 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል።

ይህ እጅግ አስደናቂ ዉጤት እያደገ የመጣዉን የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል እና የህዝብን ፍትሐዊ ዳኝነት ያሳያል። በጥቅሉ ፓርቲያችን በአብላጫ ድምፅ ቢያሸንፍም በዋናነት ያሸነፈዉ መላው የመዲናችን ነዋሪ ፣ ሰላም እንዲሁም ልማት እና እያደገ የመጣዉ የዴሞክራሲ ባህል ነው።

የተከበራችሁ መራጮቻችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊት እስከ ለ‍ሊት በምርጫ ጣቢያዎች በመሰለፍ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ እንዲጠናቀቅና ለብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በመስጠት እምነት ለጣላችሁብን ለቀጣዩ ጉዟችንም የህዝብ አደራን በአግባቡ እንድንወጣ አቅማችን ለሆናችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በቀጣዩ የ5 ዓመቱ ጉዟችን ህዝባችን የሰጠንን ታላቅ አደራ በገባነው ቃል መሠረት ሌት ተቀን በመሥራት፣ የከተማችንን ብሎም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ተግባራዊ ምላሽ እንሰጣለን።

በተለመደው መልኩ ከህዝባችን ጋር በመተባበር በከተማችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞን በማሳለጥ የህዝባችን ኑሮ እና አኗኗር ለመለወጥ ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም እናረጋግጣለን!

ይህ ድል የብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ድል ነው!

ዲሞክራሲን እያፀናን ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ እያስተናገድን፣ በአንድነትና በፓርቲያችን መሪነት ወደ ላቀ ከፍታ እንጓዛለን።

ምርጫውን በማስፈጸም፣ በመታዘብ ፣ ሰላምን በማስጠበቅ ዉጤታማ ስራ የሰራችሁ እንዲሁም የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም በማሳየት ረገድ የሀገሪቱን ህግና ስርዓት ተከትላችሁ የዘገባችሁ የሚዲያ ተቋማት ከሁሉ በላይ የሀገራችሁ ዴሞክራሲ አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመድ የበኩላችሁን የተወጣችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

በመጨረሻ በሀገር አቀፍም ሆነ በከተማ ደረጃ የፖለቲካ ልዩነት ወደ ፖሊሲ አማራጭ በማሳደግ በዚህ ምርጫ ላይ ተፎካክራችሁ በህዝብ ይሁንታ ወንበር በማግኘት የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል ለመሆን የበቃችሁ የ11 ፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎችና አንድ የግል ተወዳዳሪ በሰላማዊ መንገድ ህዝባችሁን ለማገልገል ዕድል በማግኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! እንኳን ደስ አላችሁ

የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

26/06/2026

የምንገነባው መተማመንን፣ ፅናትን፣ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን፣ ክብራችንን በጥቅሉ የኢትዮዽያን የብልፅግና መንገድ ነው።

፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

26/06/2026

ከፍሬው የምንቋደሰው መልካም ዘር! ለልጆቻችን የምናወርሰው ቋሚ ቅርስ! የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር!

ተስፋን እንትከል!

ልምላሜ ፀጋ ነው ። ልምላሜ ብልፅግና ነው፡፡ ልምላሜ የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ነው። ልምላሜ ለገፀ ምድር እና ለከርሰ ምድር ውሀችን አቅም ነው።

የምንተነፍሰው ንፁህ አየር ፣ የምንጠጣው ንፁህ ውሀ ፣ የምንመገበው ምግብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከምንተክላቸው እና ከምንከባከባቸው እፅዋት ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው።

የደን ሀብቷ በተመናመነ ሀገር ፣ አረንጓዴ ልማት በሌለባት ከተማ ፣ በተራቆተ አካባቢ ዘላቂ ዕድገትና ብልፅግና ማረጋገጥ ከባድ ነው ፤ ለኑሮ ምቹ ሁኔታ የሚፈጠረው ፣ የነገ ተስፋችን ብሩህ የሚሆነው ከተፈጥሮ የተጣጣመ ዕድገት ሲኖር ብቻ ነው።

የአየር ንብረት መዛባት ጦሱ ለሁሉም ሀገራት ፣ ለሁሉም ፍጥረታት ቢሆንም በተለይም ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ታዳጊ ሀገሮች ከባድ ፈተና ነው፡፡

የኋላ ታሪካችንን መለስ ብለን ብንመለከት ሀገራችን ለድርቅ በተጋለጠችባቸው ዓመታት ሁሉ ህዝባችን ከባድ ዋጋ ከፍሏል። በአየር ንብረት መዛባት እንደ ሀገር የተከሰተው ስብራት ህመሙ አሁንም ድረስ ከህዝባችን ስነ ልቦና ላይ አለ።

ድርቅ ፣ ጎርፍ እና ሌሎችንም በአየር ንብረት መዛባት የሚመጡ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን መቋቋም የምንችለው እጆቻችንን አፈር በማስነካት አረንጓዴ አሻራችንን በማሳረፍ ብቻ ነው።

ትናንትን በጥልቀት በመረዳት ፣ ነገን አሻግረው የተመለከቱት ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ያስጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ባለፉት ዓመታት የሀገራችን የመራቆት ግስጋሴ በመግታት የልምላሜ ፀጋን አጎናፅፏታል።

ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ ህፃናት ፣ አረጋዊያን ፣ የፀጥታ አካላት ፣ መምህራን ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ አትሌቶች ፣ አርቲስቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ሀደስንቄዎች ፣ አካል ጉዳተኞች ፣ ተቋማት ፣ ሰራተኞች ፣ በየደረጃው የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች ፣የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ለአንድ ሀገራዊ ዓላማ በጋራ የቆሙበት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ፅኑ መሰረት ሆኗል።

በየዓመቱ ሚሊዮኖች የተሳተፉበት ይህ መርሀ ግብር እንደ ሀገር 48 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል አስችሎናል ፤ ለጎረቤት ሀገራትም ተርፈናል።

ከጥልቅ ጉስቁልና እየወጣች ፣ የምትታወቅበት የነበረውን የቆሸሸ ገፅታ እያስወገደች እንደ ስሟ ውብ አበባ መሆን ለጀመረችው አዲስ አበባ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ሚና ከፍ ያለ ነው፡፡

በአረንጓዴ ልማት መለኪያ የከተሞች ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ 30 በመቶ ሲሆን ፤ በ 2010 ዓ.ም ከተማችን የነበራት የአረንጓዴ ልማት ሽፋን 2 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ ነበር። ይህ አሀዝ ከተማችን መንገዶቿ ፣ ወንዞቿ ፣ ሰፈሮቿ በከፍተኛ ሁኔታ ከመበከላቸው በተጨማሪ የነበራት መራቆት ለኑሮ አስቸጋሪ ወደመሆን እየተሸጋገረች እንደ ነበር ማሳያ ነው።

አዲስ አበባን ውብ ፣ ፅዱ እንዲሁም አረንጓዴ ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ እና በህዝባችን የተደረገው የተናበበ እና የተቀናጀ ርብርብ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል።

ከተማችን አሁን ላይ በፈጣን ልማቷ እንዲሁም በፅዳቷ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ለጎብኝዎች ተመራጭ ሆናለች። በአረንጓዴ ልማቷም ከ2 ነጥብ 8 በመቶ ተነስታ አሁን ላይ 24 በመቶ ደርሳለች።

በርካታ ስብራቶቻችንን እየጠገነ ከተማችንን ተምሳሌታዊት ከተማ ያደረገው ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጐች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ያስቻለው ልማታችን ሰው ተኮር ነው ።

ነገን አሻግሮ በሚመለከተው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብራችን የተደገፈው ልማታችን ዘላቂ ዕድገትን ታሳቢ ያደረገ ነው።

የዘንድው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል እንደ አዲስ አበባ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በሻሌ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ተበስሯል።

አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ሁላችንም ከፍሬው የምንቋደሰው መልካም ዘር ፣ ለልጆቻችን የምናወርሰው ቋሚ ቅርስ ነው፡፡

ችግኝ ስንተክል አፈርን ከመሸርሽር ስለምንታደግ ለምርታማነት ከፍ ማለት ጉልህ አሻራ እናሳርፋለን ።

የምንተክለው የምንተነፍሰውን ንፁህ አየር ነው። የምንተክለው የነገ ጥላችንን ነው። የምንተክለው የነገ ምግባችንን ጭምር ነው፡፡

አፕል ፣ ሎሚ ፣ ብርቱካ ፣ ማንጎ ፣ ሙዝ እና ሌሎችም አትክልት እና ፍራፍሬዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብራችን አካል ስለሆኑ የምግብ ዋስትናችን እና የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ከሚደረገው ብርቱ ጥረት ጋርም ተመጋጋቢ ነው ።

የከተማችንን ስታንዳርድ በጠበቀ መልኩ ፣ በዋና ዋና መንገዶች ፣ በመኖሪያ አካባቢዎች እንዲሁም በየተቋማቱ በሚደረጉ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሞች በንቃት በመሳተፍ ለትውልድ የሚሸጋገር ደማቅ ታሪክ እንፃፍ።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ati Eenyu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category