Dereje abebaw

Dereje abebaw እግዚአብሔር ይመስገን

25/04/2026

I got over 30 reactions on one of my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

5000 ብር የሚያሸልም ይገምቱ ይሸለሙ ጥያቄ💪በፕሪምየር ሊጉም ሆነ በአውሮፓ መድረክ የሚፎካከሩት እነዚህ ግዙፍ ክለቦች፣ የዓመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ ለመጨበጥ ዌምብሌይን ያናውጧታል። መድፈኞቹ...
22/03/2026

5000 ብር የሚያሸልም ይገምቱ ይሸለሙ ጥያቄ💪
በፕሪምየር ሊጉም ሆነ በአውሮፓ መድረክ የሚፎካከሩት እነዚህ ግዙፍ ክለቦች፣ የዓመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ ለመጨበጥ ዌምብሌይን ያናውጧታል። መድፈኞቹ ወይስ ሰማያዊዎቹ?

⚽️ ዋንጫው የማን ነው? 🔥
Arsenal 🔴 vs Ⓜ️ Man City
🗓 ዛሬ ከምሽቱ በ1:30

ማስጠንቀቂያ: ፔጁን Follow ካላደረጋቹ እና ይህን Post share ካላደረጋቹ ሽልማቱ ለሌላ ሰው ይሰጣል።
ህጎች:
1- ፔጁን follow ያድርጉ:
2- ግምትዎን comment section ላይ ያስቀምጡ:
3- Share ያድርጉ።
4- ጨዋታው ከተጀመረ ቦኃላ comment ማድረግ ኣይቻልም።
5- ኣንድ ሰው ከ 1 ጊዜ በላይ መገመት አይቻልም።
መልካም ዕድል🙏

አገሪቱ በህግ ሳይሆን በሚዲያ መዳኘት ከተጀመረ ሰነባብቷል። አትሌት ገለቴ ከባልዋ ደረሰባት የተባለው በደል ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በህግ መዳኘት ሲገባው ሚዲያ ላይ ስለተራገበ ብቻ ሰውዬው አጥ...
11/06/2025

አገሪቱ በህግ ሳይሆን በሚዲያ መዳኘት ከተጀመረ ሰነባብቷል።
አትሌት ገለቴ ከባልዋ ደረሰባት የተባለው በደል ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በህግ መዳኘት ሲገባው ሚዲያ ላይ ስለተራገበ ብቻ ሰውዬው አጥፊ አድርጎ በዚህ ልክ ልብስ አስወልቆ የፊጥኝ አስሮ እራቆቱ ፎቶ አንስቶ የጅምላ ፋርድ መስጠት ዛሬም የመንጋ ፍርድ የበላይነቱ እንደያዘ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

05/06/2025

ታክሲ ውስጥ ነኝ ጠዋት ነው

ከጎኗ ነኝ ድንገት የሆነ ነገር ክፍት አለ
ስዞር እያዛጋች ነው ......በነፃነት ነው እስከ መጨረሻ የከፈተቺው እጇን አፏ ላይ ጭና ማዛጋት አልፈለገችም ....

በርግጥ እንዳከፋፈቷ ምኗንም ብትጭንበት የምትሸፍነው አይመስለኝም

ገልመጥ አድርጊያት ዞርኩ ....

አራት ደቂቃ አልሆነኝም

ደግማ አዛጋች ይሄኛው ድምፅ አለው....
ልትበላኝ ነው እንዴ የሚያስብል ማዛጋት ነው

"ቡና ነው ?
ቁርስ ነው ?
እንቅልፍ ነው ወይ?" አልኳት ?

ዝም አለቺኝ

እጇን አፏ ላይ ለማድረግ የደከማት ልጅ ምን ብላ ከኔ ጋ ወግ ትገጥማለች እያልኩ በልቤ

ሌላ ወሬ ልወረውር ወደሷ ስዞር

እሷ ወደ እኔ ዞራ ስታዛጋ ተገጣጠምን ....

ግማሽ ፊቴ አፏ ውስጥ የገባ አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ

ጨንቅላቴን ወዷሃላ ስቤ ረዳት ረዳት

ወራጅ ወራጅ ወራጅ ...አልኩ

ይሄው
ቀኑን ሙሉ ላንቃዋ ጎሮሮዋ መንጋጋዋ እንጥሏ አይኔ ላይ ሊውል ነው 😁

የጉድ ሀገር አለ
28/05/2025

የጉድ ሀገር አለ

23/05/2025

“ሴት ሆይ!”
**** ****
1) በምንም ምክንያት ባልሽ ላይ ጮክ ብለሽ አትናገሪ፡፡ ምክንያቱም ባል ላይ መጮህ የመናቅ ምልክት ነዉና፡፡ (ምሳሌ 15፣1)

2) የባልሽን ድክመት ለቤተሰቦችሽም ሆነ ለጓደኞችሽ ከቶም አትግለጪ፡፡ ምክንያቱም መልሶ ወዳንቺ ነገሩ ይመጣልና፡፡ አንቺ የእያንዳንዳችሁ ጠባቂ ነሽ፡፡ (ኤፌ 5፣12)

3) ከባልሽ ጋር ስትነጋገሪ የተለየ የአካል እንቅስቃሴንና ምልክትን አትጠቀሚ፡፡ ባልሽ እነዚያን እንቅስቃሴዎችሽን እንዴት እንደሚተረጉም አታዉቂም፡፡ ኃይለኛ እና ቁጡ ሴት ደስተኛ ቤት አይኖራትም፡፡ (ምሳሌ 15፣13)

4) ባልሽን በፍጹም ከሌሎች ወንዶች ጋር አታመሳስይዉ፡፡ የሌሎች ወንዶች ህይወት ምን እንደሆነ ከባልሽ በቀር አታዉቂም፡፡ ባልሽን ከሌሎች ጋር በማነጻጸር በራስ መተማመኑን ከነጠቅሽ ላንቺ ያለዉን ፍቅር ከልቡ ያጠፋዋል፡፡

5) የባልሽን ጓደኞች ህመም አታስታሚ ምክንያቱም ትጠያቸዋለሽና፡፡ የነሱን ህመም ሊያስታም የሚገባዉ ራሱ ባልሽ ሊሆን ይገባል፡፡ (ምሳሌ 11፣22)

6) ባልሽ ወዶሽ እንዳገባሽ እንዳትረሺ፡፡ አንቺ ሰራተኛዉ ወይም ሌላ አየደለሽምና የሚስትነት ኃላፊነትሽን ተወጪ (ዘፍ 2፣24)

7) ማንንም ባልሽ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አትፍቀጂ፡፡ሌሎች ያሻቸዉን ሊያደርጉ ይችላሉ ባልሽ ግን ያንቺዉ ኃላፊነት ነዉ፡፡ (ኤፌ 5፣33)

😎 ባልሽ ባዶ እጁን ወደቤት ቢመጣ አትዉቀሺዉ ይልቁንም አረታችዉ፡፡

9) ከቶም አባካኝ አትሁኚ፡፡ የባልሽ ላብ የማያባክኑት እጅግ ዉድ ነዉና፡፡

10) ለግብረ ስጋ ግንኙነት በፍጹም ያመመሽ በማስመሰል ባልሽን አትከልክይዉ፡፡ ባልሽ እስከ ፈለገዉ ሁኚለት፡፡ ለባል የግብረ ስጋ ግንኙነት መሰረታዊ ነዉ፡፡ አንቺ ግን በተደጋጋሚ ከለከልሺዉ ከሌላ ሴት ጋር እንዲወሰልት በር ትከፍቺለታለሽ፡፡ ወንድ በፍፁም የስጋ ግንኙነትን ለረጅም ጊዜ ተቋቁሞ መዝለቅ አይችልምና፡፡ (መኃልይ 7፣12)

11) ባልሽን ከዚህ ቀደም ከሌላ ወንድ ጋር (ከቀድሞ ፍቅረኛሽ ጋር) ግንኙነት አድርገሽ ምታዉቂ ከሆነ ግንኙነት ካደረግሺዉ ሰዉ ጋር የሱን የስጋ ግንኙነት በፍጹም አታነጻጽሪ፡፡ የሄ ትዳርሽ በቀድሞ ግንኙነትሽ ከቶ አይካካስምና፡፡ (መኃልይ 5፣9)

12) ለባልሽ በአደባባይ መልስ አትስጪዉ፡፡ እሱ በአደባባይ ተናግሮሽ ቢሆንም እንኳን ነገሩን በልብሽ ያዥዉ፡፡ (ምሳ 31፣23)

13) ባልሽ ላይ በልጆቻችሁ ፊት አትቆጪ ወይም አትቋቋሚዉ፡፡ ብልህ ሴት ይህን አታደርግምና፡፡ (ኤፌ 4፣31)

14) ባልሽ በሚሰነዳዳበት ጊዜ ታሰማምሪዉ እና ሚያስፈልገዉን ታሟይለት ዘንድ አትዘንጊ፡፡ (ምሳ 12፣4)

15) ጓደኞችሽ ለባልሽ እጅግ እንዲቀርቡት አታድርጊ፡፡

16) በመዋቢያ እና በመጣጠቢያ ክፍልሽ ከቶ አትቻኮይ፡፡ ዉበትሽን ጠብቂ፡፡ ባልሽ በሌሎች ቆነጃጅት ተከቦ ሊዉል ስለሚችል እንዳይሰናከል ሁሌም ዉብ ሁኚ፡፡ (1ሳሙ 25፣3)

17) ወላጆችሽ ወይም ቤተሰቦችሽ ወይም ጓደኞችሽ የህይወትሽ ወሳኝ እንዲሆኑ አትፍቀጂላቸዉ፡፡ እነሱ ስላንቺ ትዳር ዉሳኔ እንዲሰጡ አትጠብቂያቸዉ፡፡ ማድረግ ካለብሽ ካለማንም ጣልቃ ገብነት በራስሽ አድርጊዉ፡፡ (ሉቃ 21፣16)

18) ገንዘብን የፍቅርሽ መሰረት አታድርጊዉ፡፡

19) ባሎች ትኩረት የምትሰጥንና በትኩረት የምታደምጥን ሚስት እንደሚፈልጉ በፍጹም እንዳትዘነጊ፡፡ ለሱ የሚሆን ጊዜ በፍጹም እንዳታጪ፡፡ መልካም ንግግር የደስተኛ ቤቶች መሰረት ነዉ፡፡
(ገላት 6፣9)

viya efoy

የህክምና ባለሞያዎች ስራ ለማቆም ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ተጠናቀቀ፤ ከዚያስ?
12/05/2025

የህክምና ባለሞያዎች ስራ ለማቆም ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ተጠናቀቀ፤ ከዚያስ?

08/05/2025
ክንደ ብርቱዋ እስራኤል  ይቺ የተቀደሰች ምድር የድህነቴ መነሻ፣ የገናናዉ አምላካችን የዓለም ሁሉ ጌታ የታላቁ ንጉስ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተማ (Holly land) የከበሩ ...
02/05/2025

ክንደ ብርቱዋ እስራኤል

ይቺ የተቀደሰች ምድር የድህነቴ መነሻ፣ የገናናዉ አምላካችን የዓለም ሁሉ ጌታ የታላቁ ንጉስ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተማ (Holly land) የከበሩ ነብያቶች፣ የንጉሶች መናገሻ፣ የቃልኪዳን ሕዝቦች ሀገር፣ ቅድስት ምድር እስራኤል የሚታደግሽ እግዚአብሔር በዙፋኑ አለ🙏🇮🇱❤

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dereje abebaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category