28/04/2025
ልብ ሰባሪ ሀዘን አለህ ይዘንልህ
በሰላት የማይደራደረዉ ብርቱ ወንድሜ አሊ ከድር!
ከዉድ ወንድሜ አሊ ከድር ጋር በአካል አንድ ቀን ብቻ ነው የተገናኘነዉ። በስልክ በተለያዩ ጊዜያት ብንወያይም በአንድ ወንድማችን አማካኝነት ከአመት በፊት ተገናኝተን ረዘም ላለ ጊዜያት ወስደን ተወያየን፣ ተነጋገርን።
ወቅቱ ከስልጤ ዞን ሪፎርም፣ እድገትና ልማት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የበረከቱበት ጊዜ ነበር። በዞኑ የሚከናወኑት የልማት ሪፎርምና ሕዝባችንን ከማርካት አንጻር አናሳ በመሆኑ ጥያቄዎቼን በሶሻል ሚዲያ አማራጮቼ አቀርብ ነበር።
በአካል ለመገናኘት ወሰንና በሁለታችን መሀከል ያለ ወንድማችን በመኖሪያ ቤቱ አወያየን። ትኩረት ሰጥተን በቀጣይ ሪፎርም በሚደረገባቸዉ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደረስን። አንዳንድ የአደባባይ ትችቶችን ቀንሰን ዞኑን በሚጠቅሙ ና ይበልጥ በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ በሕብረት ለመስራት ተስማማን።
ከዛሬ ቡኅላ ትችት አልሰነዝርም አልኩት!
ከወንድሜ አሊ ከድር ጋር በእለቱ ረዘም ላሉ ሰዓቶች እየተወያየን ሳለ በመሀል ሁለት አበይት ነገሮችን አነሳብኝ። እጅግ ትኩረት ሰጠሁት፤ አዉፍም የመባባላችን መቋጫ ሚስጢሩም ይኸው ነዉ።
ይህን ጉዳይ በሕይወት እያለ መፃፍ አለብኝ/የለብኝም ነበር አላውቅም። ነገር ግን አሁን በድንጋጤ ስሜት ዉስጥ ሆኜ ከአመት በላይ የያዝኩትን ጉዳይ ወደሶሻል ሚዲያ አመጣሁት።
ሙጂብ በዞኑ ላይ ችግሮች የሉም ብዬ አልሞግትህም፤ አንዳንዶቹ በራሳችን ችግርና በአቅም ዉስንነት በሌላም በኩል በክልሉ አስተዳዳራዊ ጉዳዮች ይከሰታሉ። እዉነት ነው የስልጤ ዞን በተፈለገዉ መልኩ እድገት አላሳየም። "ሁላችንም የዚሁ ችግር ባለቤቶች ነን" በማለት እንደመሪ ለችግሮች ኅላፊነት በመዉሰድ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማድረግ ራዕዩን አጋራኝ።
ይቅርታ ተጠያይቀን ፣ ተቃቅፈን የተለያየንበት አጋጣሚ የተፈጠረዉ ወንድሜ አሊ ባስወነጭፋቸዉ ልብ በሚያሞቅ፣ ትሥፋ በሚጭር፣ መተማመንን በሚያጎለብቱ በአጭር አርፍተ ነገሮቹ ነዉ።
እኔ አለ ወንድሜ አሊ- እኔ እንደሌሎች ባለስልጣና ምቾት ላይ ነኝ ብዬ፣ ባለስልጣን ነኝ ብዬ አላህን አላምፅም ቢያንስ ሶላቴን የምስገድ ነኝ አለኝ። በራስ የመተማመኑን ፀዳል ፊቱ ላይ እያነበብኩበት፤ ቀጠለና እንደዘመኑ ባለስልጣናት ሴት የምቀያይር ሳልሆን እምነቴን የምጠብቅ ከእንደዚህ አይነት ነዉር የፀዳዉ ነኝ አለኝ።...
እኔም ተደሰትኩበት፣ ቀጣይ ጥያቄዎቼን ዋጥኳቸዉ፤ ...ብዙ ብዙ ነገሮች በአዕምሮዬ ላይ እየተመላለሱ ተነስቼ አቀፍኩት። ... ይሕን እፁብ ነገር ካሟላ ሌላው ትርፍ ነው ብዬ ለራሴ ነገርኩት...ተደሰትኩበትም: አላህ ይደሰትብህ🤲🏻
አላህ ይማርህ ፤አሏህ በእዝነቱ ይቀበልህ። አላህ ማረፊያህን ጀነተል ፊርደውስ ያድርግል። አሚን! 🤲🏽