Mesfen zeret

Mesfen zeret Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mesfen zeret, Grocers, A. A, Addis Ababa.

11/05/2026

የብልፅግና ጉዟችን፡ ከጠንካራ እሳቤ ወደ ተጨባጭ ስኬት!

ብልፅግና ፓርቲ ላለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገራችንን ወደ ተሻለ ከፍታ ለማሻገር በተለያዩ ዘርፎች ሰፋፊ የለውጥ ጉዞዎችን አድርጓል። በዚህም በዲሞክራሲ ግንባታ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በመሰረተ ልማት እና በዲፕሎማሲ መስኮች ጉልህ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

ፓርቲያችን "በመደመር" እሳቤ ላይ ተመስርቶ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ተጨባጭ ውጤቶችን ማምጣት ችሏል፤

በዲሞክራሲ ግንባታ፡ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት፣ የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ገለልተኝነት በማረጋገጥ እንዲሁም የዜጎችን የሀሳብ እና የመደራጀት ነፃነት በማክበር አዲስ እና አካታች የፖለቲካ ባህል እንዲዳብር መሰረት ተጥሏል። በምክክር እና በውይይት የሚያምን ማህበረሰብ ለመገንባት ትልቅ እርምጃ ተጉዘናል።

በኢኮኖሚው መስክ፡ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በተግባር በመተርጎም፣ በግብርናው ዘርፍ (በተለይም በስንዴ ልማት እና በበጋ መስኖ) የታዩት ስኬቶች የኢኮኖሚያችን ዋልታ ሆነዋል። ከዚህም ባሻገር ከተሞቻችንን ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ የሚያደርጉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በማፋጠን፣ የስፖርት ቱሪዝምን እና የከተማ ገጽታን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ አዳዲስ የኢኮኖሚ አቅሞችን መፍጠር ተችሏል።

በማህበራዊ ዘርፍ፡ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትምህርት፣ የጤና እና የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ስራዎች በስፋት ተሰርተዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንደ ጠንካራ ባህል በማስረፅ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አቅመ ደካማ ዜጎችን መደገፍ እና ማህበራዊ ትስስራችንን የጠነከረ ማድረግ ችለናል።

በዲፕሎማሲው መስክ፡- የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ክብር እና ሉዓላዊነት በማዕከል ያደረገ ዲፕሎማሲን ተግብረናል። ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትስስርን ስናጠናክር፣ ታሪካዊው የ'ብሪክስ' (BRICS) አባልነታችን የዚሁ ስኬታማ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተሰሚነታችንን ያረጋገጠ የዲፕሎማሲ ጉዟችን ማሳያ ነው።

በባለፉት የለውጥ ዓመታት ያገኘናቸው ስኬቶች የሁላችንም የጋራ ጥረት ውጤቶች ናቸው።
ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር፣ በአብሮነት እና በወንድማማችነት መንፈስ የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!
መንገዳችን መደመር ፣ ምርጫችን ብልፅግና ፣ መዳረሻችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ነው፤

መልካም የስራ ሳምንት!!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት



26/10/2025
17/09/2025

🇪🇹፦ የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬ መሆኑን ማሳያ "የማንሰራራት ጊዜ አሻራ፤ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ሆኖ "4" መፅሀፍትን ለሀገር ማበርከት ፤ የፃፈውን በመተግበር ታሪክ መስራት፤ የመፅሀፋን ሽያጭ ለትውልድ ት/ት ተቋማት መገንባት እና ለሌሎች ልማት ማዋል፤ ይህ ለኢትዮጵያ መታደል ነው!!

🇪🇹፦የመደመር ጥቅምን በተግባር ያሳየ፤
🇪🇹፦ መደመር የኢትዮጵያን የፓለቲካ ፤ የኢኮኖሚ ፤ የማህበራዊና የውጭ ግንኙነት ስብራቶችን የጠገነ፤
🇪🇹፦ በመደመር መፍጠር ፤ መፍጠን አልቆ መፈጸምን በተግባር ያሳየ፤
🇪🇹፦ የኢትዮጵያ ሀገራችን የከፍታ ሚስጥር መደመር መሆኑን ያስተማረን መሪያችን እንኳን 4ኛውን መፅሀፍ " የመደመር መንግስት " የሚለውን መፅሀፍ ለሀገርህ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ እንዲሁም ለአህጉርህ አፍሪካና ህዝቦቿ ለማበርከት በቃህ!!
🇪🇹፦ ከተስፋ ብርሃን ወደተጨባጭ ብርሃን በ2018 ዓ.ም የተቀመጠው ራዕይ መሳካቱን ማረጋገጫ ማህተም ነው !!
🇪🇹፦ መልካም ንባብ፤
☂️፦1 መደመር፤
☂️፦2 የመደመር መንገድ፤
☂️ ፦3 የመደመር ትውልድ፤
☂️፦4 የመደመር መንግስት፤
አይገርምም ወይ? በዚህ ሁሉ ወከባ እና ውጣውረድ ፈተናዎችን ወደዕድል በመቀየር አራተኛ መፀሀፍ ፅፎ የሚያስመርቅ ጀግና መሪ! ሌላው ደሞ ወሬ ሲሰልቅ ከረመ!
ልዩነቱ እየሰፋ ነው! ይችላል ይለያል የምንለው ለዚህ ነው!

የኢትዮጵያው የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መፀሀፍ "የመደመር መንግስት" መልካም ንባብ !!

Address

A. A
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesfen zeret posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category