Pawe Agricultural Research Center

Pawe Agricultural Research Center The center was established in 1986, a year after a devastating famine, to support settlers in the region by providing improved technologies.

it evolved into one of EIAR's main research centers.

05/05/2026
የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክትበፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ6 ዓመት ተመራማሪነት እና የስራ ሂደት ተጠሪ ሆነው ያገለገሉ፣ ለ4 ዓመታት ደግሞ የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ሆነው...
30/04/2026

የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት

በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ6 ዓመት ተመራማሪነት እና የስራ ሂደት ተጠሪ ሆነው ያገለገሉ፣ ለ4 ዓመታት ደግሞ የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ሆነው ካገለገሉ በኋላ አዲስ ወደ ተከፈተው የወረኢሉ ግብርና ምርምር ማዕከል በመዛወር ከማቋቋም ባሻገር እስከ ተሾሙበት ቀን ድረስ ለ3 ዓመታት ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። በቆዩባቸው ጊዜያትም ተቋሙን ውጤታማ ያደረጉ ስራዎችን አከናውነዋል።

ለሀገርና ለወገን የሚተርፍ ዕውቀትና የሥራ ትጋት የታጠቁት የቀድሞ ሥራ ባልደረባችን አቶ ደሳለኝ ተሻለ፤ ላለፉት 13 ዓመታት በግብርናው የምርምር ዘርፍ ያሳዩት ቁርጠኝነት ዛሬ ለታላቅ አገራዊ ኃላፊነት አብቅቷቸዋል።

እነዚህን ተከታታይ ውጤታማ የሥራ ጉዞዎችን ተከትሎ፣ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ሆነው ተሹመዋል።

ከመሠረቱ ተነስተው ዕውቀትንና ልምድን አከማችተው፣ ዛሬ ለዚህ ከፍተኛ አገራዊ ኃላፊነት በመብቃትዎ ታላቅ ኩራት ይሰማናል።
ይህ ሹመት የልፋትዎ ውጤት፣ የትጋትዎ ምንዳ ነው። በአዲሱ የሥራ መስክዎ የኢትዮጵያን ግብርና ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩ ሙሉ እምነታችን ነው።"

ለዚህ ስኬትም የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል በመሉ የማዕከሉ ሠራተኞች ስም የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል።

(ፓዌ:-መጋቢት 29/2018 ዓ.ም) በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ለጥበቃ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት (EIAR) ስር በሚገኘው በፓዌ ግ...
08/04/2026

(ፓዌ:-መጋቢት 29/2018 ዓ.ም) በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ለጥበቃ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት (EIAR) ስር በሚገኘው በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ስር ለሚገኙ የጥበቃ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል።

ሥልጠናውን የሰጡት የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መርከቡ ደግዋለ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የጥበቃ ሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም እና ግንዛቤ ማሳደግ ነው።

ይህ ሥልጠና የማዕከሉን ደኅንነት እና የጥበቃ ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አሰረድተዋል። ተሳታፊዎቹም በሥራቸው ላይ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ጉዳዮች እና ስለሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ሰፊ ግንዛቤ አግኝተዋል።

በመጨረሻም፣ እንዲህ ያሉ አጫጭር ሥልጠናዎች የሠራተኞችን አቅም በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የማዕከሉ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ለምርምር ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::ፓዌ፣ ኢትዮጵያ – የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል (Pawe Agricultural Research Cent...
04/04/2026

የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ለምርምር ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::
ፓዌ፣ ኢትዮጵያ – የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል (Pawe Agricultural Research Center) ከመጋቢት 24 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሳጥ የነበረዉን የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን አጠናቋል።

ስልጠናው በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ቴክኒካል የመስክ እና ሁለገብ የምርምር ድጋፍ ሠራተኞች የምርምር ዕውቀታቸውን ለማሻሻል ያለመ ሲሆን፣ ስልጠናውም የምርምር ማሳ ላይ በሰፊው የተግባር ስልጠና ተሰጥቶበታል። የስልጠናው ዋና ዓላማ በማዕከሉ የምርምር ሥራ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ሠራተኞች የዕውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን በመሙላት የምርምር ውጤታማነትን ማሳደግ ነው።
ይህ ስልጠና በተለይ የምርምር ሥራዎችን በብቃት ለማከናወን የሚያስችሉ ዘመናዊ የምርምር ዘዴዎችን፣ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ቴክኒኮችን እንዲሁም የምርምር ግኝቶችን የማሰራጨት መንገዶችን ያካትታል።
በማዕከሉ የሚገኙ ልምድ ባላቸው ተመራማሪዎች የተሰጠው ይህ ስልጠና፣ ተሳታፊዎች በየዕለቱ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ላይ የተሻለ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል። የሁለት ቀናት ቆይታውም ሠራተኞቹ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ ልምዶችን እንዲለዋወጡ እና ከተመራማሪዎች ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የግብርና ምርምር ውጤቶችን በማሳደግና ለአ/አደሮዎች ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ይህ ዓይነቱ የውስጥ አቅም ግንባታ ስልጠናም የማዕከሉን አጠቃላይ አፈጻጸም ለማሳደግና ለሀገሪቱ የምግብ ዋስትና አስተዋጽኦ ለማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ተገልጿል።

(ፓዌ፡-መጋቢት 24/2018 ዓ.ም) በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ሁሉም  ምርምር ሥራ ሂደት በዘጋጀዉ ስልጠና በስሩ ለሚገኙ ቴክኒካል የመስክ  እና ሁለገብ የምርምር ድጋፍ ሠራተኞች ያላቸዉን...
02/04/2026

(ፓዌ፡-መጋቢት 24/2018 ዓ.ም) በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ሁሉም ምርምር ሥራ ሂደት በዘጋጀዉ ስልጠና በስሩ ለሚገኙ ቴክኒካል የመስክ እና ሁለገብ የምርምር ድጋፍ ሠራተኞች ያላቸዉን የምርምር ዕዉቀት ለማሻሻል ላይ ያተኮረ ስልጠና በሚመለከታቸዉ የማዕከሉ ተመራማሪዎች በተከታታይ ሁለት ቀን የሚቆይ አቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የሆርቲካልቸር ምርምር ፕሮግራም በተለያዩ የአትክልትና የፍራፍሬ ሰብሎች ላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም...
24/03/2026

በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የሆርቲካልቸር ምርምር ፕሮግራም በተለያዩ የአትክልትና የፍራፍሬ ሰብሎች ላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም አገር በቀል የሆኑ የፍራፍሬ ሰብሎችን ለቀጣይ ምርምር እንዲጠበቁና እንዲጠናከሩ የማቆያና የጥበቃ ተግባራትን በትኩረት ያከናውናል።
በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ከሚካተቱት አገር በቀል ፍራፍሬዎች መካከል “ትርንጎ” (Citron) ልዩ ትኩረት የተሰጠው ነው። ይህ ፍራፍሬ በከፍተኛ መጠን ትልልቅ ፍሬዎችን ማፍራት በመቻሉ ልዩ ባህሪ ያለው ሲሆን፣ እስከ 7.865 ኪ.ግ ክብደት፣ 43 ሴ.ሜ ርዝመት እና 47 ሴ.ሜ መጠነ ዙሪያ ያለው ፍሬ መሰብሰብ ተችሏል። ይህም በአካባቢው ለፍራፍሬ ምርት ልማት ከፍተኛ እድል እንዳለ የሚያመለክት ነው።

(የካቲት 22/2018ዓ.ም) ለተለያዩ ሰብሎች ውሃን በልኬትና በጊዜ ሰሌደ በመስጠት የመስኖ ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።በፓዌ ወረዳ ቀ2 መ...
02/03/2026

(የካቲት 22/2018ዓ.ም) ለተለያዩ ሰብሎች ውሃን በልኬትና በጊዜ ሰሌደ በመስጠት የመስኖ ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
በፓዌ ወረዳ ቀ2 መ-30 ቀበሌ/ዳንጉር ጎጥ በፓዊ የግብርና ምርምር ማዕከል አማካኝነት የተሰሩ የመስኖ ምርምር ስራዎች ላይ ከአርሶ አደሮችና ማሳ ቅድመ- ማስተዋወቅ ሰርቶ ማሳያ ያለዉን ስንዴ፥ ሽንኩርትና እና ሽንብራ ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር የመስክ ጉብኝት እና ምዘና አድርጓል፡፡
የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ተወካይ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ታፈረ ሙሉአለም እንደገለፁት ምርምር ማዕከሉ በመተከል እና በአዊ ዞን በርካታ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የተሻለ ምርት የሚሰጡ የመስኖ ስንዴ ሰብል ዝሪዎችን በባለፉት አመታት በፊት ምርምር ማዕከሉ በመለየት ወረር ሁለት የተባለ ዝርያ ምርታማ መሆኑንና አሁን ደግሞ ዉሃ አሰጣጥ ሰሌዳ ማዉጣት የአ/አደሮች ጊዜና ጉልበት ይቆጥባል በማለት ገልፀዋል።
የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈርና ዉሃ አያያዝ ምርምር የስራ ሂደት ተጠሪ የሆኑት ዶ/ር የኔሰው አሳየ እንደገለፁት በለስ ተፈሰስ የመሬቱ መልካዓ-ምደራዊ አቀማመጥ፥ የአፈር ባህርይ እና አካባቢው ከፍተኛ የሆነ የከረሰ-ምድርና ገፀ-ምድር የውሃ አቅም በመኖሩ ለመስኖ ልማት ምቹ ነው። በመሆኑም በምርምር የተደገፈ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችና ምክረ-ሀሳቦችን ለተጠቃሚዎች ማስተዋወቅ የመሰኖ ምርታማነትን በማሻሻል የምግብ ሉዓላዊነትን እና ዋስትና ማርጋገጥ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
የመስኖና ዉሃ እቀባ ተመራማሪ የሆኑ አቶ ደመቀ ታመነ እና አቶ ተመስገን ፋንታሁን ሀገሪቱ በትኩረት እያሰራችበት ያለዉን የበጋ ስንዴ ትክክለኛዉን የመስኖ የጊዜ ሰሌዳ መጠቀም የመስኖ ዉሃን ከመቆጠብ በተጨማሪ ምርትና ምርታማነትን እንደሚጨምር አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም የመስኖና ዉሃ እቀባ ተመራማሪ ወ/ሮ አበባ ሀሰን ለሽምብራ ተጨማሪ ዉሃ በተፈለገዉ ጊዜ መስጠት ምርትና ምርታማነትን እንደሚጨመር አስረድተዋል፡
የፓዌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ አደነ እንደገለፁት ፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል አ/አደሮች ለተሻለ ምርት እንዲያገኙ የተደረገዉ የምርምር ስራ አበረታች መሆኑን በመግለጽ አ/አደሮች የተሰሩትን ቴክኖሎጅዎችን ተቀብለዉ ተግባራዊ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ምርምር ማዕከሉ አረሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እያበረከተ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ተሳታፊ አርሶ አደሮች አመስግነው በቀጣይ አዳዲስ ሌሎች የመስኖ ስራ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

🎓 እንኳን ደስ አለዎት! የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል  ከአስርት አመታት በላይ በተመራማሪነትና በአሁኑ ሰዓት የአፈርና ወሃ አያያዝ ምርምር ስራ ሂደት...
13/02/2026

🎓 እንኳን ደስ አለዎት!
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ከአስርት አመታት በላይ በተመራማሪነትና በአሁኑ ሰዓት የአፈርና ወሃ አያያዝ ምርምር ስራ ሂደት ተጠሪ ሁኖ እያገለገሉ ያሉ ለዶ/ር የኔሰው አሳየ የዶክትሬት (PhD) ዲግሪን ከባህዳር ዩንቨርሲቲ በአመርቂ ዉጤት ስለተመራቁ ምርምር ማዕከሉ እንኳን ደስ አላህ ለማለት ይፈልጋል ።
ይህ ታላቅ ስኬት የብዙ ዓመታት ጥረትና ትጋት ፍሬ ሲሆን ለማዕከላችንና ለሀገራችንም ጭምር ኩራት ነው።
በቀጣይ የምርምርና ሙያዊ ጉዞዎ የበለጠ ስኬት እንዲሆንልዎት እንመኛለን።
👏 በድጋሜ እንኳን ደስ አለዎት!

(ፓዌ፡-የካቲት  05/2018 ዓ.ም) የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የወረዳ ባለሙያዎችን ጨምሮ ለተመረጡ የአካባቢው አ/አደሮች የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻል፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ማሳደግ፣የእ...
12/02/2026

(ፓዌ፡-የካቲት 05/2018 ዓ.ም) የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የወረዳ ባለሙያዎችን ጨምሮ ለተመረጡ የአካባቢው አ/አደሮች የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻል፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ማሳደግ፣የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋት እና የወተት ላም እርባታ ሥራን ማዘመን ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የእንስሳትን ዝርያ በማሻሻል ጤናን በመጠበቅና የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በማሻሻል የዜጎችን የስጋና የወተት ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል የምርምር ውጤት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ምርምር ማዕከሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ አበበ ተነግሯል ፡፡

ስልጠናዉን የሰጡት የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሐብቴ አረጋ የወተት ላም እርባታ ለዜጓች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ከመሆን ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና እንዳለዉ በመግለፅ ምርምር ማዕከሉ በእንስሳት ምርምር የስራ ሂደት የአርብቶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም የአካባቢውን አ/አደር ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በወተት ላም ምርምር ፕሮግራም ከሚሰሩት የምርምር ስራዎች አንዱ የሆነው የአካባቢ ከብት ዝሪያዎችን በመጠበቅና ለማሻሻል የወተት ምርታማነትን ማሳደግ ይገኝበታል ብለዋል።
ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻል፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ማሳደግና የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን የማስፋት እንዲሁም የንብና የዶሮ እርባታ ስራ ውጤት በሚያስገኝ መልኩ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

ምርምር ማዕከሉ በዛሬዉ ዕለት እንስሳት ምርምር ስራ ሂደት ክፍል ባዘጋጀው ስልጠና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በፓዌ ወረዳ የወረዳና ቀበሌ ባለሙያዎች እንዲሁም ከፓዌ ከተማ 02 ቀበሌ የተመረጡ አርብቶ አደሮች በተገኙበት የአቅም ግንበታ ስልጠና ተሰጥቷዋል።

PARC Center-Level Annual Research Review (2025/26)Pawe Agricultural Research Center successfully conducted its 2025/26 C...
02/02/2026

PARC Center-Level Annual Research Review (2025/26)
Pawe Agricultural Research Center successfully conducted its 2025/26 Center-Level Annual Research Review over four consecutive days (18-21/05/2018 E.C). The review meeting was organized with the participation of senior and experienced resource persons assigned by EIAR from Jimma and Debre Markos Agricultural Research Centers, alongside senior researchers from PARC. Completed, ongoing, and newly proposed research activities were critically reviewed, with particular emphasis on newly initiated research proposals to ensure their scientific relevance, methodological soundness, and alignment with national research priorities. During the review sessions, each research process presented the research outputs, progress reports, and proposed plans. Senior researchers from PARC and the invited external resource persons rigorously evaluated the research activities and proposals. Constructive comments, technical feedback, and practical recommendations were provided to each research process and program, with the aim of improving research quality, strengthening methodologies, and ensuring relevance for program-level and national-level research reviews. Following thorough technical evaluation, the newly proposed research activities were reviewed, refined, and approved at the center level with critical guidance from senior researchers and external researchers. The review carried out with a comprehensive plenary discussion led by the delegated resource persons and the Center Director. Key cross-cutting issues, common challenges, research gaps, and strategic directions were identified and summarized. The meeting also emphasized the importance of incorporating the provided feedback into revised research proposals and implementation plans, strengthening inter-process collaboration, and ensuring effective documentation and follow-up of agreed action points. Overall, the Center-Level Annual Research Review was successful in enhancing the quality, relevance, and coherence of PARC’s research portfolio and in preparing well-refined research outputs and proposals for subsequent program-level and national research evaluations.

Address

Metekel, Pawe
Addis Ababa
25

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pawe Agricultural Research Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Pawe Agricultural Research Center:

Share