Defaru gamo

Defaru gamo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Defaru gamo, Grocers, Gamo, Arba Minch'.

12/03/2026
ዉድ ኢትዮጵያዊያን ሀገር ዉስጥም ይሁን ከሀገር ዉጪ ያላችሁ፦ በጋሞ ዞን በደረሰ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካታ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ ይገኛሉ። ብዙ ወንድምና እህቶ...
12/03/2026

ዉድ ኢትዮጵያዊያን ሀገር ዉስጥም ይሁን ከሀገር ዉጪ ያላችሁ፦ በጋሞ ዞን በደረሰ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካታ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ ይገኛሉ። ብዙ ወንድምና እህቶቻችን ህይወታቸዉን አጥተዋል። የደረሱበት የማይታወቅ ወገኖቻችን ቁጥርም ቀላል አይደለም። በመሆኑም ደጋግ ኢትዮጵያዊን ድጋፍ እንድታደርጉ ዘንድ እንጠይቃችኋለን። የጋሞ ህዝብ ከራሱ በላይ ለሌላዉ የሚያስብ፣ ኢትዮጵያ ሠላም እንድትሆን ዋጋ የከፈለ ህዝብ ዛሬ አደጋ ደርሶት የዉድ ኢትዮጵያን የድጋፍ እጅ ይሻል። የዓይነትም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።
ፈጣሪ በምህረቱ ያስበን!

የጋሞ ዞን ባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ፌስቲቫል በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀመረአርባምንጭ፦ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)የጋሞ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ከዞ...
30/12/2025

የጋሞ ዞን ባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ፌስቲቫል በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀመረ

አርባምንጭ፦ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)

የጋሞ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ከዞኑ ስፖርት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዞናዊ የባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ፌስቲቫል በአርባምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በውድድሩ መጀመሪያ ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ተወካይና በመምሪያው የስፖርት አደረጃጀትና ፋሲሊቲ ልማት ቡድን መሪ አቶ እንግዱ ስበረው ተሳታፊዎች ውድድሩን በእህትማማችነትና በወንድማማችነት ስሜት እንዲሁም ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ እንዲያካሂዱ አሳስበዋል።

ስፖርት አብሮነትንና አንድነትን ይበልጥ ያጠናክራል ያሉት አቶ እንግዱ ተወዳዳሪዎች ያላቸውን ብቃት ተጠቅመው የሚመጣውን ውጤት በፀጋ መቀበል የስፖርታዊ ጨዋነት መገለጫ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በዞኑ ባህልና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ቡድን መሪ አቶ ህይወት በቀለ በበኩላቸው ውድድሩን የሚመሩት ልምድ ያላቸውና በሳል ዳኞች በመሆናቸውን ተወዳዳሪዎች ከአላስፈላጊ ክርክር ተቆጥበው ትኩረታቸውን ውድድሩ ላይ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በዚህ ውድድር የወርቅ መዳሊያ የሚሸለሙ ስፖርተኞች በቀጣይ ዞኑን ወክለው ክልላዊ መድረክ ላይ የሚሳተፉ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ህይወት ተወዳዳሪዎች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደረጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ዞናዊው የባህል ስፖርትና የባህል ፌስቲቫሉ በዛሬው ዕለት በልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ጨዋታዎች በአርባምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በሌሎች ውድድሮችም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

Address

Gamo
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Defaru gamo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category