18/06/2026
በአርጡማ ፋርሲ ወረዳ የመንገድና የድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተገመገመ፡፡
*******
ከሚሴ
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአርጡማ ፋርሲ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታና የጋራ የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።
በመስክ ጉብኝቱ ላይ የጨፋ-ቂጪጮ-ሀራ የመንገድ ፕሮጀክት እና የዲምቱ ቀበሌ የኮንክሪት ድልድይ ግንባታ የስራ እንቅስቃሴ በቦታው ተገኝቶ የተገመገመ ሲሆን፥ የፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሲራጅ ሙስጠፋ እና የገንዘብ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ ሙሄን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የወረዳ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለሙያዎች እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቶቹ የተቀመጠላቸውን ጥራት ጠብቀውና በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲበቁ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
ከመስክ ምልከታው ማጠናቀቂያ በኋላ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የምክክር መድረክ የተካሄደ ሲሆን፥ በውይይቱም የፕሮጀክቶቹን አጠቃላይ አፈጻጸም በመገምገም፣ በቀሪ ጊዜያት መከናወን ባለባቸው ወሳኝ ተግባራትና ሊወሰዱ በሚገባቸው መፍትሄዎች ዙሪያ ግልጽ አቅጣጫ መቀመጡን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።