M kishere Dira busekut&samebusa

Directions Contact the business

M kishere Dira busekut&samebusa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from M kishere Dira busekut&samebusa, Grocers, Dire Dawa.

መንግሥት ካሸነፈ በኋላ የተሸነፈውን ኃይል በፕሪቶሪያው ስምምነት አስቀምጦ ተደራድሮ፣ በችግር ውስጥ የነበሩ ኃይሎችን ቀልቦ እና ብዙ ድጋፍ ሰጥቶ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል። ጠቅላይ...
11/08/2026

መንግሥት ካሸነፈ በኋላ የተሸነፈውን ኃይል በፕሪቶሪያው ስምምነት አስቀምጦ ተደራድሮ፣ በችግር ውስጥ የነበሩ ኃይሎችን ቀልቦ እና ብዙ ድጋፍ ሰጥቶ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የሕወሓት ታጣቂዎች ላይ የተሰነዘረው የድሮን ጥቃት በአላማጣበራያ አላማጣ ወረዳ መርዋ በተሰኘች አካባቢ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ተሰብስበው በነበሩ የህወሓት...
11/08/2026

የሕወሓት ታጣቂዎች ላይ የተሰነዘረው የድሮን ጥቃት በአላማጣ

በራያ አላማጣ ወረዳ መርዋ በተሰኘች አካባቢ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ተሰብስበው በነበሩ የህወሓት ታጣቂዎች ላይ ትናንት ሐምሌ 4 ቀን፣ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ ። በጥቃቱ በርካታ ሰዎች ሳይጎዱ እንዳልቀረና ጉዳተኞች ወደ አላማጣ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ።

ሰበር ዜናየሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደረሱነሐሴ 5/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8/2...
11/08/2026

ሰበር ዜና

የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደረሱ

ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አጀንዳዎቹ 500 አባላት ባሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛሉ፡፡ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት 500 አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካካረ ይገኛል፡፡

በዚህም በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ለይ ሲመካካሩ የቆዩት ሁለት ቡድኖች ዛሬ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም በተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ላይ ተፈራርመዋል፡፡

የሌሎች አጀንዳዎች ተመካካሪዎችም በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ የአጀንዳ ሃሳቦቻቸውን የጋራ አድርገው በቃለ ጉባኤዎቻቸው ላይ በመፈራረም እንደሚስማሙ ይጠበቃል፡፡

Ethiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

“ሌብነትን አስቁሙልን ፣ ሕዝብ የሚጠብቀው መፍትሄ"/ አዋጩ የሰላም መንገድ፤ምክክር
11/08/2026

“ሌብነትን አስቁሙልን ፣ ሕዝብ የሚጠብቀው መፍትሄ"/ አዋጩ የሰላም መንገድ፤ምክክር

ሬጅመንቱ በፈረስ ቤት ከተማ  ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አደረገ ።በምስራቅ ዕዝ ስር የሚገኘው ሬጅመንት በምዕራብ ጎጃም ዞን  በፈረስ ቤት ከተማ ከተሰጠዉ ሰላም ማስከበር ግዳጅ ጎን ለጎን ...
11/08/2026

ሬጅመንቱ በፈረስ ቤት ከተማ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አደረገ ።

በምስራቅ ዕዝ ስር የሚገኘው ሬጅመንት በምዕራብ ጎጃም ዞን በፈረስ ቤት ከተማ ከተሰጠዉ ሰላም ማስከበር ግዳጅ ጎን ለጎን ኅብረተሰቡን በጉልበትና በገንዘብ በመደገፍ ለተቸገሩ ወገኖች ደራሽ መሆኑን ቀጥሏል ።

የሬጅመቱ አዛዥ ሻምበል አበራ ተስፈየ ድጋፋን አስረክበዉ እንደተናገሩት፣ ሠራዊቱ ሕዝቡን እንደ ራሱ ቤተሰብ በመቁጠር ከኪሱ ካለዉ በመቀነስ ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው ለስድስት እማዉራዎች ቅድሚያ በመስጠት ከሠራዊቱ በተሰበሰበ 16 ሺ 300 ብር የምግብ ቁሳቁሶች እና ለወቅቱ ተስማሚ የሆኑ አልባሳትን በመግዛት አከፋፍለናል ብለዋል ።

ሻምበል አበራ ተስፋየ ቀጥለዉም፦ ሬጅመንቱ ከአይነትና ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ፣ የሠራዊቱ አባላት አቅመ-ደካሞችን በጉልበታቸው በመርዳት ማህበራዊ አገልግሎቶችን መስጠታቸዉን ገልፀዉ ሠራዊቱ በቀጣይም ከተሰጠው ሀገራዊ የሰላም ማስከበር ግዳጅ ሳያወላውል፣ ከአካባቢው ሕዝብ ጎን በመቆም አቅም የፈቀደውን ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸዉ እማውራዎች ሠራዊቱ ላበረከተላቸዉ የአይነትና ለጉልበት ድጋፍ ምስጋናቸዉን ገልፀዋል ። መረጃው የምስራቅ ዕዝ ነዉ።

#በጎአድራጎት #ፈረስቤት #ኢትዮጵያ

ጦርነት የኋላ ማርሽ ነው! ✅​«ኦሮሞ አይገዛኝም! አማራ አይገዛኝም! ትግሬ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ወይም ሌላው ብሔር አይገዛኝም!» ብለህ ጫካ ገብተ...
09/08/2026

ጦርነት የኋላ ማርሽ ነው! ✅
​«ኦሮሞ አይገዛኝም! አማራ አይገዛኝም! ትግሬ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ወይም ሌላው ብሔር አይገዛኝም!» ብለህ ጫካ ገብተህ ከተዋጋህና መስዋዕት ከሆንክ፤
#እኔስ ብሆን? «ይህ ብሔር አይገዛኝም» ብዬ ጫካ የማልገባበት ምን ምክንያት አለኝ?
​«እስልምና አይገዛኝም! ኦርቶዶክስ አይገዛኝም! ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ ወይም ሌላው ሃይማኖት አይገዛኝም!» ብለህ ወደ ግጭት ካመራህ፤
#እኔስ በሃይማኖቴ ምክንያት ጫካ የማልገባበት ምን የተለየ ምክንያት አለኝ?
​አንተ ዘመነ ነው መሪዬ፣ ሌላው ደብረፅዮን ነው መሪዬ፣ ሌላው ደግሞ ጃል መሮ ነው መሪዬ ብሎ ሲዋጋ፤
#እኔስ ዶ/ር አቢይ ነው መሪዬ ብዬ የማልዋጋበትና ጫካ የማልገባበት ምን ምክንያት አለ?
​ግን እስኪ ቆም ብለህ አስብ፤ አንተ ጫካ ገብተህ ካሸበርክና ይህን መንግስት ብታወርድ፦
#እኔስ አንተ የወጣህበትን ጫካ ገብቼ እንደማልጥልህ በምን እርግጠኛ ሆንክ? አንተ የተሸሸግክበት ተራራና ዋሻ እኔንም እንደሚደብቀኝ አታስብም?
​ይባስ ብሎ ደግሞ፤ አንተን ያስታጠቁ የኢትዮጵያ ጠላቶች ነገ እኔንም እንደሚያስታጥቁኝ፣ አንተን የላኩህ ኃይሎች ነገ ደግሞ እኔን ጫካ ገብቼ እንድዋጋህ እንደሚልኩኝ እንዴት አልተገነዘብክም? ተሳክቶልህ እንኳን ይህን መንግስት ብታሸንፍ ላኪዎችህ እኔን ይልኩብሃል። ምክንያቱም የነሱ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ወድቃና ወደኋላ ቀርታ እንድንበላላ ማድረግ ነው!
​ለላኪዎችና ለሀገር ጠላቶች ዕድል አንስጥ!
ይህ ምስኪን ሕዝብ በቀን ሦስቴ እንዲበላና በሰላም እንዲኖር ዕድል እንስጠው።
​በሃሳብ እንሞግት! ማንም ወደ ጫካ አይግባ!
እኛ የሁሉም ብሔርና ሃይማኖት ስብስብ የሆንን የአንዲት ሀገር ልጆች ነን፤ ወደኋላ በጣም ቀርተናል፤ ጦርነት የኋላ ማርሽ ነው።
​ይልቅ በሃሳብ እንብለጥ፣ በሰላም እንኑር!
​Ani cipiixoo Qabadheen jira, jedhu warri Daawwee tokko.
ከፊንፊኔ ሰማይ ስር! 🇪🇹

20/07/2026

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when M kishere Dira busekut&samebusa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to M kishere Dira busekut&samebusa:

Shortcuts

Share

Category