Dewa Abalmekarim

Directions Contact the business

Dewa Abalmekarim Rabbiin sifa umamtotaarra qulqullahaadha

29/09/2026
29/09/2026
29/09/2026

إنا لله وإنا إليه راجعون
"ሁሉ ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት..."
በታላቁ ሼኻችን ሼህ አዲል አባት አሸይክ አህመድ ሸሪፍ ህልፈተ ሕይወትየተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ

አላህ (ሱ.ወ) አባታችንን በጥሩ ምህረቱና በሰፊው እዝነቱ ይቀበላቸው፤ ከፍተኛዋን ጀነት "ጀነተል ፊርደውስን" ይወፍቃቸው። በብርሃን የተሞላና የጀነት ጨፌ የሆነ ቀብር ይስጣቸው።
ለከበሩት ሼኻችን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ አላህ በቂያቸውን የሆነውን "ሰብረን ጀሚል" (መልካምና ጥልቅ ትዕግስትን)፣ መጽናናትንና አጅርን ይለግሳቸው።
ዓላሁመ ኡግፊር ለሁ ወርሐምሁ፣ ወዓፊሂ ወዕፉ ዓንሁ... አሚን!

29/09/2026

የኡስታዝ ዓዲል አባት ሀጅ አህመድ ዓብዱል ቃድር አርፈዋል ።

إنا لله وإنا إليه راجعون

የታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓም የኡስታዝ ዓዲል አህመድ አባት ሀጂ አህመድ አብዱልቃድር ሸሪፍ ወደ አኺራ ሕይወት መሸጋገራቸውን በመስማታችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።

በዚህ አሳዛኝ የሀዘን ወቅት ከኡስታዝ ዓዲል አህመድና ከመላው ቤተሰባቸው፣ ዘመድ አዝማድና ወዳጆቻቸው ጎን በመቆም፣ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ብርታትና ትዕግሥት እንዲሰጣቸው እንለምናለን።

እንዲሁም አላህ ለሟቹ ምሕረቱንና እዝነቱን አድርጎ፣ መቃብራቸውን ከጀነት ጨፌዎች አንዱ ያድርግላቸው፤ ጀነተል ፊርደውስንም ይወፍቃቸው።

የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ከዙሁር ሰላት በኋላ በኮልፌ የሙስሊሞች መቃብር ይፈጸማል።



إنا لله وإنا إليه راجعون

29/09/2026

ባለፉት የለውጥ አመታት በተሰጠኝ ሀገራዊ ሀላፊነት በምችለው ሁሉ ከመላው የከተማ እና መሰረተ ልማት ቤተሰቦች ጋር በመሇን ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበናል ፣የኢትዮዽያ ከተሞች ለዉጥ ህያው ምስከር ናቸው።
በቀጣይ በተጣለብኝ ሀገራዊ አደራ እና ሀላፊነት ከየትኛውም ጊዜ በላቀ ትጋት እና ውጤታማነት ለማገልገል ቃል እገባለሁ ።ለተሰጠኝ እድል እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ።

Baroottan jijjiiramaa darbaniif amantaa ol'aanaa mootummaan nutti kennamee ture anaa fi hoggansi akkasumaas hojjattoonni fi maatiin Ministeera Misoomaa Magaalaa fi Bu'uuraalee Misoomaa hundii waliin tahun bahanneen jijjiirama qabatamaan galmaa'ef ragaan jijjiirama magaaloota Itoophiyaa ti.

Har'as ittii gaafatamummaa dabalataa ol'aanaa mootummaan natti keenname hoggansaa fi hojjattoota akkasumaas qaamoolee qooda fudhattootaa hunda waliin qindoominaan hojjannee bu'aalee caalan galmeessuuf kan hojjannu taha.
Amantaa ol’aanaa naaf keenname kanaafiis gammachuu natti dhagahame ibsaa, ulfaadhaa!!galatoomaa !!Alamagan!!

29/09/2026

"ከዘር አጥፊዎች ጋር እጅ አንጨባበጥም!" ያለው እና እስራኤልን በሜዳም በሞራልም የረታው የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል

መስከረም 18/2019

በአውሮፓ የሀገራት ሊግ (UEFA Nations League) መርሃ ግብር እስራኤልን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ያሸነፈው የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን፤ ተጫዋቾቹ በጋዛ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በመቃወም በሜዳ ውስጥ ባሳዩት ጠንካራ 'የህሊና አቋም' የዓለምን ትኩረት ስቧል።

በሃንጋሪ በገለልተኛ ሜዳ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ፣ አየርላንዳውያኑ ከተለመደው የስፖርታዊ ጨዋነት ሥነ-ሥርዓት ውጭ የእስራኤል ተጫዋቾችን እጅ ለመጨበጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የሁለቱ ሀገራት አምበሎች የባንዲራ ልውውጥ ያላደረጉ ሲሆን፤ የእስራኤል ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅትም የአየርላንድ ተጫዋቾች አንገታቸውን በመድፋት ለፍልስጤማውያን ያላቸውን አጋርነት እና በዘር ጭፍጨፋው ላይ ያላቸውን ጥልቅ ተቃውሞ አሳይተዋል።

እንደ BBC Sport፣ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሄይሚር ሃልግሪምሰን ከጨዋታው በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ ተጫዋቾቻቸው በወሰዱት ደፋር አቋም በጋዛ ስላለው ሁኔታ "በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ግንዛቤ መፍጠር ችለዋል" በማለት ድርጊታቸውን አድንቀዋል። በተለይም የቡድኑ ግብ ጠባቂ ጋቪን ባዙኑ፤ "በጋዛ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ ከእስራኤል ጋር መጫወት ስህተት ነው" በማለት ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ራሱን ከስብስቡ ማግለሉ በእስራኤል ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ ጫና ይበልጥ አጠናክሮታል።

ስፖርትን ከሰብዓዊነት ነጥሎ ማየት እንደማይቻል በተግባር ያሳየው የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን፤ ተጫዋቾቹ ለሟቾች መታሰቢያ ያሰሩትን ጥቁር የክንድ ባንድ (Black armbands) ለብሰው ወደ ሜዳ ገብተዋል።

በጨዋታው ሶስተኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጃክ ሞይላንም ኳስ ከመረብ ካሳረፈ በኋላ የክንድ ባንዱን በማውለቅ እና የሀገሩን አርማ በመሳም ታሪካዊ አቋሙን አንጸባርቋል።

በአየርላንድ "ጨዋታው ይቁም" (Stop The Game) በሚል በ "Irish Sport for Palestine" አስተባባሪነት የተቀሰቀሰው ይኸው ማህበራዊ ንቅናቄ፤ እስራኤልን በስፖርቱ መድረክ እንድትገለል እያደረጋት ይገኛል።

እስራኤል ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በጋዛ በከፈተችው አረመኔያዊ ወታደራዊ ጥቃት እስካሁን ከ73 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ታማኝነቱን ያረጋገጠለት የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ክሶችን በተደጋጋሚ የምታስተባብለው እስራኤል፤ በአየርላንድ ስፖርተኞች የገጠማት ይህ የተግባር ተቃውሞ በዲፕሎማሲውም ሆነ በስፖርቱ ዓለም ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባታል።

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dewa Abalmekarim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dewa Abalmekarim:

Shortcuts

Share

Category