01/02/2026
📌 በታሪክ መድረክ ላይ እንደ ሸማ የሚለዋወጥ ማንነት ይዘው የሚቀርቡ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ትላንት "ስለ ጦርነቱ መለኮስ አናውቅም" በሚል የየዋህነት ካባ ተሸፍነው ሲያለቅሱልን ከርመው፣ ዛሬ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት እንደ ርካሽ የፖለቲካ "ማሟሟቂያ" ግብዓት ማቅረባቸው የሞራል ዝቅጠት የመጨረሻው ጥግ ነው።
📌 ይህ ድርጊት ተራ ውሸት ሳይሆን፣ የትውልድን ደም ለስልጣን ማቆያነት የመጠቀም ስልታዊ ክህደትና የህሊና መታወር ማረጋገጫ ነው፤ በአንድ ወቅት ሰለባ መስለው ሲቆዝሙ፣ በሌላ ወቅት ደግሞ የጥፋቱ መሃንዲስ መሆናቸውን በታላቅነት ስሜት ሲያወሩ የሚታዩት እነዚህ "የቁም-ሙታን" ፖለቲከኞች፣ ታሪክን እንደ ፈለጉ የሚዘውሩት የመሰላቸው ቢሆንም፣ በመጨረሻ ግን በገነቡት የውሸት ማዕበል ተውጠው መቅረታቸው የማይቀየር የፍትህ ህግ ነው።