Daniel Masso

Daniel Masso News

  አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ ...
29/04/2023

አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡

ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡

ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡

በኋላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡

" ? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡

" ፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡

" #እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡

በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡

"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡

አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ " #ድንቹ፣ #እንቁላሉ እንዱሁም ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡

#ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡

#እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡

#ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡

?" ችግር ስገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?"

✍ #በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!"
የትኛው ነህ? የትኛው ነሽ?

አስተማሪ ሆኖ ካገኙት #ላይክ እና #ሼር ያድርጉት
Via ዳኒ M

16/04/2023

- ይወለዳል ተባለ ተወለደ
- ይምታል ተባለ ሞቴ
- ይነሳል ተባለ ተነሳ
ዳግም ይመጣል ተባሌ እንጠብቀው...
እንኳን አደረሳችሁ🙏

01/04/2023

This is what you are seeing in the southern region from South Omo Jinka Wolaita Road.

ኑሮ በዜደ            በተለምዶ በበሬ ተጠምዶ ነበር ምታረሰው ድርቅ ገባ በረውም ሞቴ             ዘመን አመጣሽ ትራክተሩም እዛው ነው ለደቡብ.......  በሞተር እንሞክር
22/03/2023

ኑሮ በዜደ
በተለምዶ በበሬ ተጠምዶ ነበር ምታረሰው ድርቅ ገባ በረውም ሞቴ
ዘመን አመጣሽ ትራክተሩም እዛው ነው ለደቡብ....... በሞተር እንሞክር

የወንድማችንን ህይወት እንታደግ !!!!        ጤናው እንዲመለስ እንረዳዳ 👏   #እግዚአብሔር ሰላምና ጤና ያደላችሁ እናንተ ቅን አሳቢ የሀገሬ ህዝቦች  #መምህር  #አስማማው  #ከማይ ሁ...
16/02/2023

የወንድማችንን ህይወት እንታደግ !!!!
ጤናው እንዲመለስ እንረዳዳ 👏

#

እግዚአብሔር ሰላምና ጤና ያደላችሁ እናንተ ቅን አሳቢ የሀገሬ ህዝቦች #መምህር #አስማማው #ከማይ ሁላችንም የምናውቀው ወንድማችን ነው።

መምህር አስማማው ከማይ ሙላቱ በደ/ኦሞ ዞን በዎባ አሪ ወረዳ በሁለተኛ ደረጃ ና በመ/ደ/ት/ቤቶች ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ስያገለግል ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረበት የጭንቅላት ህመም በጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የሥነ አዕምሮ ህክም ስከታተሉ ቆይቶ ህመሙ ከባድና በፍጥነት ወደ ወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል Rerefer በተደረገው መሰረት "የጭንቅላት ዕጢው" በሥነ አዕምሮ ህክምና ዶክተሮች የጭቅላት ቀዶ ጥገና እንዲደረግለት የተወሰነ ስለሆነ በቀን 14/06/2015 ዓ.ም ቀጠሮ ለኦፕራሶን ሰለተቀጠረ የህክምና ወጪውም ከግማሽ ሚሊዬን /500,000/ በላይ የሚፈጅ መሆኑ የተገለፀልን ሰለሆነ መላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ይህ ወጣቱ ከጭንቅላቱ ደም ፈሳሽ እየወጣ እንቅልፍ እርቆታል
ይህን ልጅ በጋራ የተለመደውን እርብርቦሽ በማድርግ እንታደገው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ቤተሰቦቹ ይጠይቃሉ 👏

ሰለዚህ በወንድሙ በእንዳሻው ከማይ ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድባንክ አካውንት=1000040824107 ወይም በታማሚው መ/ር አስማማው ከማይ 1000364009279 ገቢ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ ስልክ =0928736830

//ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው!//

ስለመልካምነታችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን
ለአስተባበሩ፣መልእክቱን ላጋሩ፣በገጻቸው ላጻፉ የበጎነት ባለቤት የሆናችሁ አስተባባሪዎች እግዚአብሔር የነፍስ ዋጋ አድርጎ ይቀበልልን!!!!!!!!

🚹??   🚹??   በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት ነው። የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው ። ቅዱስ ጳውሎስ"...
05/02/2023

🚹?? 🚹??

በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት ነው። የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው ። ቅዱስ ጳውሎስ" ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን" ( 1ኛ ቆሮ 14:40) እንዳለው

ማንኛው ሰው ተፈጥራዊ ስሜት ይንሮው እንጂ እንደ እንስሳ ሳይሆን በስርዓት መሄድ ይኖርበታል አንድ ሰው በሂወቱ ሃላፊነት ካልወሰደ በስተቀር ማንም ሃላፊነት ሊወስድለት አይችልም።

ወንዱ ይሁን ሴቷ የእግዚአብሔር ሕግ ከማስቀደም ይልቅ ፋሽን እየተባለ ወንዱ በየቀኑ ሴቶችን እንደ ልብስ እየቀያየረ ፣ ሴቷም በየቀኑ ወንዶች እንደ ልብስ እየቀያየረች ወደ ሞት ይነዳሉ። ይህ የዝሙት መንፈስ የተጠናወተበት ሰው በስጋው ይሁን በነፍሱ የረከሰና የድያብሎስ መኖርያ ይሆናል። አላስተዋልም እንጂ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ በዋጋ የገዛን በመሆናችን በራሳችን ላይ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የማድረግ ስልጣን የለንም።
ሰለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን(1ቆሮ 3:16) ።

ታድያ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ ከተባልን የእግዚአብሔር መንፈስ መኖርያ እንሆን ዘንድ ከዝሙት መራቅ አለብን አለበለዚያ ንስሐ ሳንገባ በዝሙት ተጠምደን የምንኖር ከሆንን ግን ነፍሳችን ከእግዚአብሔር ፀጋ ተራቁታ ወደ ሲኦል ትገባለች ዝሙት የነፍስና የስጋ በሽታ መሆኑን የአምላክ ቃል እንዲህ ብሎ ያስተምረናል፦

🚺🚹 " ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ " ( 1ኛ ቆሮ 3:17) ።

✅ እስኪ ከመፅሓፍ ቅዱስ ስለ ዝሙት ምን እንደሚል አብረን እንመልከት፦

✅ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል "( ማቴ 5፥32)።

✅ " ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና" ( ማቴ 15:19)።

✅ " ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ።ጤና ይስጣችሁ " ( ሐዋ.ሥራ 15:28-29)።

✅ " በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ( ሮሜ 13:13)።

✅ " በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት
ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና( 1ኛ ቆሮ 5:1)።
✅ " መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው " ( 1ኛ ቆሮ 6:13)።
✅ " ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል" ( 1ኛ ቆሮ 6:18)።

✴✳ ታድያ ምን እናድርግ? ✳✴

✅ እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ ( ራእ.ዮሐ 2:10)። ይህ የህይወት አክሊል የሚገኘው በፆም ፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ ንስሐ ገብተን በቅዱስ ቁርባን መኖር፣ አስራት በኩራት በማውጣት ስንኖር ነው። ቅዱስ አምላካችን በማቴ 6:33። ላይ " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመ
ሸር ሸር ሸር ይድረስ ለወጣቶች via Dani

Monbasa
20/01/2023

Monbasa

ኬኒያ ጥምቀት የለም
19/01/2023

ኬኒያ ጥምቀት የለም

ናፍቆት ከኢቢኤስ ጋር ተለያየችመላው የኢቢኤስ ጋዜጠኞች በእንባ ሀዘን በተሞላበት ስሜት ሸኝተዋታል።ናፍቆት ከቅርብ ግዜ ውዲህ በተለይ በኢቢኤስ የጋዜጠኝነት ስራዋ ላይ ተወዳጅነትን እያተረፈች ...
18/01/2023

ናፍቆት ከኢቢኤስ ጋር ተለያየች

መላው የኢቢኤስ ጋዜጠኞች በእንባ ሀዘን በተሞላበት ስሜት ሸኝተዋታል።
ናፍቆት ከቅርብ ግዜ ውዲህ በተለይ በኢቢኤስ የጋዜጠኝነት ስራዋ ላይ ተወዳጅነትን እያተረፈች የመጣች ጎበዝ ምርጥ ወጣት ናት ፣
መዳረሻዋ በግልጽ ባይታወቅም ከነበረችበት ቦታ የተሻለ ቦታ እንደምናያት እርግጠኞች
ነን ፣
አስፋው መሸሻ ከራኬብ ቀጥሎ ናፍቆትን በእንባ ሸኝቷል ።
ናፍቂ በሄድሽበት ሁሉ ይቅናሽ ።

via dani 🙏🟩🟨🟥

😂
17/01/2023

😂

16/01/2023

(ኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ 26)
----------
1፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።

2፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም ፍሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

3፤ በሥርዓቴ ብትሄዱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም፥

4፤ ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም እህልዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።

በረሐው......
16/01/2023

በረሐው......

Address

Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daniel Masso posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Daniel Masso:

Shortcuts

Share

Category