Agrikom Agricultural Development

Directions Contact the business

Agrikom Agricultural Development Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Agrikom Agricultural Development, Kombolcha, Kombolcha.

What We Offer?
✅ Animal Feed & Silage
✅ Dairy Excellence – Fresh milk
✅ Supply poultry, beekeeping, and dairy equipment.
✅ Farm-to-Table Freshness – locally sourced flavors at Addis Ta'em restaurant.
✅ Seedling Acclimatization

15/09/2026
12/09/2026

የመሬት ካሳ የማግኘት መብት!
********
ከህጋዊ ይዞታው በልማት ምክንያት የተነሳ ሰውን መልሶ ሟቋቋም የመንግስት ግዴታ ነው። የተነሺውም መብት ነው።
በመሆኑም ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ሰፍረዋል።

(1) ካሳ የማግኘት መብት:-

በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1161/11 አንቀፅ 8(1)(ሰ) ስር የልማት ተነሺውን ማስነሳት የሚቻለው ለተነሺው ካሳ ከተፈለ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት ከሰጠ በኋላ መሆን እንዳለበት አዋጁ ይደነግጋል፡፡በመሆኑም ሰዎች በይዞታቸው ካሳም ሳይከፈላቸው ምትክ ቦታም ሳይሰጣቸው እንዲነሱ ተደርጎ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸው የነበሩ ባለይዞታዎች በጣም ብዙ የነበሩ በመሆኑ ይህ አዋጅ ህዝቡ ውስጥ የነበረው ችግር ለመፍታት ተነሺዎች ከመነሳታቸው በፊት አስቀድመው ካሳ እና ምትክ ቦታ ማግኘት እንዳለባቸው መደንገጉ በሕግ ደረጃም ቢሆን ጥሩ የሚባል ነው፡፡

(2) ካሳ በወቅቱ ካልተከፈላቸው መልሶ የመያዝ መብት

ተነሺዎች የካሳ ግምት በጹሑፍ እንዲያውቁ ከተደረገ ቀን ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካሳ ካልተከፈላቸው በመሬት ይዞታቸው ከቋሚ ተክልና ግንባታ በስተቀር ሌሎች ስራዎች መስራት ይችላሉ በማለት ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሳ ካልተከፈው በፕላን የሚፈቀድ እና ቀጣይ የቦታውን የልማት ወጪ በመንግስት ላይ የማያበዛ በመሬቱ ላይ ማንኛውም ስራ መስራት ይችላል በማለት ይደነግጋል።

ቢሆንም ግን ይህ ድንጋጌ እጅግ አሻሚ ነው ምክንያቱም መንግስት ካሳ ካልከፈለ በፕላን መሰረት ባለይዞታ ማንኛውንም ዓይነት ስራ መስራት እንደሚችል ከተደነገገ በኋላ በመንግስት የልማት ወጪ የማያበዛ ስራ ማለቱ ምን ማለት ነው? እጅግ በጣም ግልጽ ነት የጎደለው ነው፡፡

(3) ተመጣጣኝ ካሳ ክፍያና ምትክ ቦታ

አዲሱ አዋጅ በመሬቱ ላይ ለተፈራ ንብረት፣ ቋሚ ማሻሻያ ባለይዞታው ንብረቱን ማዘዋወር የሚችል ከሆነ የማዘዋወሪያ ወጪ ወይም የትራንስፖርት/የማጓጓዣ ወጪ ከመክፈሉ በተጨማሪ ከገጠር መሬት ይዞታ ለሚነሳ የመሬት በላይዞታ ተነሺ ከተወሰደበት መሬት ተመጣጣኝ የሆነ ምትክ መሬት እና መሬት ይዞታው ከመልቀቅ በፊት ባሉ ሶስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ምርት ያመረተበትን ምርት በወቅታዊ ዋጋ ተሰልቶ በ15 ተባዝቶ ይከፈላል በማለት ይደነግጋል፡፡

(4) የልማት ተነሽ ድጋፍ

በአዋጁ አንቀጽ 2(4) የልማት ተነሽ ድጋፍ የመሬት ባለይዞታ ከመሬቱ በጊዜያዊም ሆነ በቋሚነት ሲነሳ ከአዲሱ አከባቢ ጋር መላመድ እንዲችል ከንብረት እና ከልማት ተነሽ ካሳ በተጨማሪ በዓይነት ወይም በገንዘብ የሚሰጥ ድጋፍ ነው፡፡ it is promising move አዲስ እና በጣም ጥሩ የሚባል ነው ነገር ግን ይህ ነገር የሚወሰነው በክልሎች መመሪያ ነው፣ መች ይሁን የሚወጣው? ባይወጣስ?

መልሶ ማቋቋም ፡- በአዋጅ አንቀጽ 16 የክልል መንግስት ወይም የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ አስተዳደር ለካሳ ክፍያ እና ለመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ያቋቁማል በማለት ይደነግጋል፡፡ መልሶ ማቋቋም ማለት በተወሰደው መሬት ምክንያት የሚያገኙት ጥቅም ለሚቋረጥባቸው ተነሺዎች ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ የሚያስችል የሚሰጥ ድጋፍ ነው ።
https://t.me/melakufek
https://www.facebook.com/share/
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-99aqd4Xta3c

የመጀመሪያው ዙር ስልጠና መስከረም 7 እና 8 /2019 ይሰጣል። 0911183437ላይ  በመደወል ቀድማችሁ ተመዝገቡ።
03/09/2026

የመጀመሪያው ዙር ስልጠና መስከረም 7 እና 8 /2019 ይሰጣል። 0911183437ላይ በመደወል ቀድማችሁ ተመዝገቡ።

📢 የተግባር ስልጠና ጥሪለኮምቦልቻ እና አካባቢው የእንስሳት አርቢዎችውድ የድልብ፣ የወተት ላሞች፣ የፍየልና ሌሎች የእንስሳት አርቢዎች!በእንስሳት እርባታ ሥራ ውስጥ መኖ ከዋና ዋና የምርትና ...
31/08/2026

📢 የተግባር ስልጠና ጥሪ

ለኮምቦልቻ እና አካባቢው የእንስሳት አርቢዎች

ውድ የድልብ፣ የወተት ላሞች፣ የፍየልና ሌሎች የእንስሳት አርቢዎች!

በእንስሳት እርባታ ሥራ ውስጥ መኖ ከዋና ዋና የምርትና የትርፋማነት ወሳኝ ምክንያቶች አንዱ ነው። የመኖ አያያዝና አጠቃቀም በእንስሳት ጤና፣ ምርታማነትና በእርባታ ሥራችን ትርፋማነት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው።

የእንስሳት መኖ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ሲሆን፣ በተለይ በደረቅ ወቅት የመኖ እጥረት ለአርቢዎች ከፍተኛ ፈተና እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ በእርጥበት ወቅት በብዛት የሚገኘውን አረንጓዴ መኖ በአግባቡ አዘጋጅቶ ለደረቅ ወቅትና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ማስቀመጥ የዘመናዊና ስኬታማ የእርባታ ሥራ ወሳኝ ስልት ነው።

🌱 ገፈራ (Silage) ምንድን ነው?

ገፈራ (Silage) ለገፈራ ተስማሚ የሆኑ አረንጓዴ የመኖ ተክሎችን በትክክለኛ የሳይንስ ዘዴ በማዘጋጀት፣ በተገቢው ሁኔታ በማጠንከርና አየር እንዳይገባ በማሸግ ለረጅም ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ የሚቀመጥ ጠቃሚ የእንስሳት መኖ ነው።

በተገቢው ወቅት ተሰብስቦ፣ በትክክለኛው ዘዴ ተዘጋጅቶና በጥራት ተይዞ የተቀመጠ ገፈራ ለረጅም ጊዜ ለእንስሳት ጥራት ያለው መኖ ሆኖ ያገለግላል።

ለገፈራ ተስማሚ ከሆኑ የመኖ ተክሎች መካከል፦

🌽 የበቆሎ ተክል
🌾 የማሽላ ተክል
🌿 የዝሆን ሣር
🌱 ሌሎች ለገፈራ ተስማሚ የሆኑ አረንጓዴ የመኖ ተክሎች

ይገኙበታል።

ነገር ግን ገፈራን ያለበቂ ግንዛቤና የቴክኒክ እውቀት ለማዘጋጀት መሞከር የመኖ መበላሸት፣ የከፍተኛ ወጪና የጉልበት ብክነት ሊያስከትል ይችላል። ስለዚህ የገፈራን አዘገጃጀት፣ አያያዝና አጠቃቀም በተገቢው መልኩ ማወቅ አስፈላጊ ነው።

🎓 በAGRIKOM የግብርና ልማት የተዘጋጀ

የ2 ቀን በተግባር የተደገፈ የገፈራ (Silage) ስልጠና

AGRIKOM የግብርና ልማት በእንስሳት እርባታ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ አርሶ አደሮችና የእርባታ ሥራ ባለሙያዎች ጥራት ያለው ገፈራ በራሳቸው ማዘጋጀት እንዲችሉ የተዘጋጀ የ2 ቀን በተግባር የተደገፈ ሙያዊ ስልጠና አዘጋጅቷል።

📚 የስልጠናው ዋና ይዘቶች

1️⃣ የገፈራ መሠረታዊ ግንዛቤ

ገፈራ (Silage) ምንድን ነው?

የገፈራ ጥቅሞች

ገፈራ እና ሌሎች የመኖ አያያዝ ዘዴዎች

2️⃣ ለገፈራ የሚሆኑ የመኖ ዓይነቶች

ተስማሚ የመኖ ተክሎች ምርጫ

ተገቢውን የመከር ወቅት መለየት

3️⃣ የገፈራ አዘገጃጀት

የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

መኖ መቁረጥ

ትክክለኛ የመቁረጥ መጠን

ማሸግና ማጠንከር

አየር እንዳይገባ በትክክል መዝጋት

4️⃣ የገፈራ አያያዝና የጥራት ምርመራ

ገፈራን በትክክል ማስቀመጥ

ጥራት ያለውንና የተበላሸውን ገፈራ መለየት

የገፈራ መበላሸት ምክንያቶችና መከላከያዎች

5️⃣ የገፈራ አጠቃቀምና አመጋገብ

ለተለያዩ የእንስሳት ዓይነቶች አጠቃቀም

ገፈራን ከሌሎች መኖዎች ጋር በማቀናጀት መመገብ

🛠️ በተግባር የተደገፈ ስልጠና

ይህ ስልጠና በንድፈ ሀሳብ ብቻ አይወሰንም!

ሰልጣኞች በተግባር የገፈራ ዝግጅት ሂደቱን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በመሳተፍ ይማራሉ።

📌 ለእያንዳንዱ ተሳታፊ የገፈራ አዘገጃጀትና አያያዝ ሙሉ የስልጠና ማንዋል (Hard Copy) ይሰጣል።

📌 ተሳታፊዎች የተማሩትን እውቀት በቀጥታ በራሳቸው የእርባታ ሥራ ላይ ማዋል እንዲችሉ ከስልጠና በኋላ ክትትልና የቴክኒክ ድጋፍ ይደረጋል ።

📍 የስልጠና መረጃ

📍 የስልጠና ቦታ፦ ኮምቦልቻ – የመኖ ማዘጋጃ ማዕከል

📅 የስልጠና ጊዜ፦ 2 ቀናት

💰 የስልጠና ክፍያ፦ 1,950 ብር

📞 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ፦ 0911183437

ይመዝገቡ፤ በተግባር ይማሩ።

አዲሱ የገጠር መሬት አዋጅ!********በአዲስ በተሻሻለው የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 310/2018 የተካተቱ ነጥቦች፦የአማራ ክልል መንግሥት የነበረውን አዋጅ ቁጥር 252/2009 በመሻር አዲ...
30/08/2026

አዲሱ የገጠር መሬት አዋጅ!
********
በአዲስ በተሻሻለው የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 310/2018 የተካተቱ ነጥቦች፦

የአማራ ክልል መንግሥት የነበረውን አዋጅ ቁጥር 252/2009 በመሻር አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 310/2018 በሥራ ላይ አውሏል።

ይህ አዋጅ ከፌደራል የገጠር መሬት ሕግ (1324/2016) ጋር የተጣጣመ ሲሆን፣ ከመሬት ምዝገባ ጀምሮ እስከ ይዞታ ዝውውር፣ ከብድር ዋስትና እስከ መሬት ኪራይ እንዲሁም የባለይዞታዎችን መብትና ግዴታ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያሉና መሠረታዊ ለውጦችን ይዟል።

የባለይዞታዎችን መብት የሚያሰፉ 9 ዋና ዋና ነጥቦችን እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል።

1. የአዋጁ ተፈጻሚነት ወሰን (Scope of Application) አንቀጽ 3 በቦታ ረገድ (Territorial Scope)፦

በገጠር መሬት ላይ፦ በክልሉ ውስጥ በሚገኝ ማንኛውም የገጠር መሬት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

በከተማ አስተዳደሮች ሥር ባሉ የገጠር ቀበሌዎች፦ በከተማ አስተዳደር ሥር ቢሆኑም የገጠር ይዘት ባላቸውና በገጠር ቀበሌነት በተዋቀሩ አካባቢዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

ርክክብ ባልተፈጸመባቸው የከተማ ወሰን መሬቶች፦ አንድ አካባቢ ወደ ከተማ ወሰን እንዲገባ ተደርጎ፣ ነገር ግን በከተማውና በገጠር መሬት አስተዳደር መካከል የይዞታ ርክክብ እስካልተፈጸመ ድረስ በዚህ አዋጅ መመራቱን ይቀጥላል።

በይዞታና ጉዳዮች ረገድ (Subject Matter Scope)፦

በሁሉም የይዞታ ዓይነቶች፦ በግል፣ በወል (በጋራ) እና በመንግሥት የገጠር መሬት ይዞታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

የሕግ ተቃርኖን ለመፍታት፦ የገጠርና የከተማ መሬት አስተዳደር ወሰን ላይ ይፈጠሩ የነበሩ ግራ መጋባቶችን ለመቅረፍ እንዲቻል፣ የገጠር መሬት ይዞታ ምን ማለት እንደሆነና የሚገኝበትን አስተዳደራዊ ወሰን በማያሻማ ሁኔታ ይገልጻል።

ልዩ ሁኔታዎች (Exceptions)፦

ልዩ ጥበቃ የሚደረላቸው መሬቶች፦ ለደን ልማት፣ ለዱር እንስሳት ጥበቃና ለማዕድን ልማት ተከልለው የተያዙ መሬቶችን በተመለከተ፣ አዋጁ እንደ አስፈላጊነቱ ተፈጻሚ ቢሆንም፣ በዘርፉ የወጡ ልዩ ሕጎች (Specific Laws) ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚችል ይጠቁማል።

2. የመሬት ማግኘት መብትና ተጠቃሚነት (አንቀጽ 4-8)

ነፃ መሬት፦ በግብርና መተዳደር የሚፈልግ የክልሉ ነዋሪ (ዕድሜው 18+) መሬት በነፃ የማግኘት መብት አለው።

ቅድሚያ የሚሰጣቸው፦ ወላጅ የሌላቸው ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና ወጣቶች ልዩ ትኩረትና የቅድሚያ መብት ይሰጣቸዋል።

የመብት ቆይታ፦ የአርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮችና የሃይማኖት ተቋማት መብት የጊዜ ገደብ የሌለው (ለዘላለም) ነው። መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግን ለሥራቸው አስፈላጊ እስከሆነ ጊዜ ብቻ ይፈቀድላቸዋል።

3. የይዞታ ዝውውር (ኪራይ፣ ስጦታና ውርስ)

ኪራይ (አንቀጽ 9)፦ ባለይዞታው ከግማሽ የማይበልጥ ይዞታውን ማከራየት ይችላል። (አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ግን ሙሉውን ማከራየት ይችላሉ)። የጊዜ ገደብ፦ ለቋሚ ተክል እስከ 30 ዓመት፣ ለሰብል እስከ 10 ዓመት።

ስጦታ (አንቀጽ 11)፦ ለሥጋ ዘመድ ወይም "በይጦረኛል" ውል ለማንኛውም ሰው በጽሑፍ መስጠት ይቻላል።

ውርስ (አንቀጽ 12)፦ ማንኛውም ሰው (የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ) በኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ በፍትሐ ብሔር ሕጉ መሠረት መሬት መውረስ ይችላል። ይህም ቀደም ሲል የነበረውን ገደብ ያነሳ ትልቅ ለውጥ ነው።

4. ንብረት መሸጥና በጋራ ማልማት (አንቀጽ 13-19)

የንብረት ሽያጭ፦ በመሬት ላይ የለማ

Great opportunity
27/08/2026

Great opportunity

22/07/2026

With Amhara Livestock and Fisheries Resources Development Bureau – I just got recognized as one of their top fans!

16/07/2026
02/02/2026

Today is World Wetlands Day.

This year’s theme, Wetlands and traditional knowledge: Celebrating cultural heritage, recognises the role of Indigenous and local knowledge in caring for wetlands over generations.

Wetlands are repositories of centuries of human wisdom, shaping how communities grow food, manage water, and live in harmony with the land.

Protecting them is also about protecting that knowledge.

Address

Kombolcha
Kombolcha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agrikom Agricultural Development posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Agrikom Agricultural Development:

Shortcuts

Share