Seid

Seid Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Seid, Grocers, Nekemt.

23/01/2025
22/01/2025
26/12/2024

"Don't give part-time people a full-time position in your life. "

12/10/2024

GOOD THINGS WILL HAPPEN

12/10/2024

GOOD THINGS WILL HAPPEN

https://alison.com/
18/08/2024

https://alison.com/

Free online courses with certificates. Join 8 million graduates and empower your career. Study, learn, certify, upskill with free online learning and training

18/08/2024

በህፃናት ላይ ለጨከኑ እጆች ምነው ህጋችን ላላ??

በባህርዳር ከተማ በ7 አመት ታዳጊ ህፃን በነበረችው ህፃን ሄቨን ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ የአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ወንጀል እንደ ተራ ወንጀል ታይቶ ወንጀለኛውን በይግባኝ ለማስለቀቅ አልያ ወላጅ እናቷን በማስፈራራት ለማስፈታት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን መስማት የሰው ልጅን የጭካኔ ጥግ እና የሀገራችን የፍትህ ስርዓት አደገኛ ወንጀለኛን ተቀላቢ አድርጎ የሚያኖር መሆኑን አመላካች ነው::

አቅፈን ለማሳም እና ለመንካት እንኳን የሚያሳሱንን ህፃናት እንስሳቶች እንኳን በራሳቸው ላይ የማይፈፅሙትን ነውረኛ ተግባር ያውም ባለትዳር የሆነ ሰው ያለምንም ሰብዓዊነት ህፃኗን ደፍሮ ሲያበቃ የአውሬነቱን ጥግ ማሳያ አንቆ መግደሉ ቃላት ሊገልፁት የማይችል የጭካኔ ተግባር ነው::

በዚህ ወቅት እንደ ሀገር እያለፍነው ያለው ከባድ መከራ ፣ሞት እና እልቂትን ለማስቆም ብዙ መሰራት ያለበት ስራዎች ቢኖሩም በተለያዩ ጊዜያቶች ድንገት የምንሰማቸው ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ፣እንቅልፍ የሚነሱ እና ልብን የሚያደሙ ወንጀሎች ያለንበትን አስከፊ ሁኔታ ከባድ ያደርገዋል::

እኛ ይህን ያህል ህመሙ ከተሰማን የወለደ አንጀት ፣ የአብራካቸው ክፋይን በዚህ መልኩ ያጡ ወላጆችን ስሜት ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል መገመት ይከብዳል::

ምን ያህል ከሰብዓዊነት ብናፈነግጥ ይሆን አይደለም ልንገድላቸው ይቅርና ለማየት የሚያሳሱንን ህፃናት ላይ እጃችንን ማንሳት ያስቻለን!?

ለነዚህ ወንጀለኞች ጥብቅና የሚቆም የህግ ባለሞያስ ምን አይነት የሞራል እና የሰብዓዊነት እንጥፍጣፌ ከውስጡ የወጣ ባለሞያ ይሆን??

የነገ ሀገር ተረካቢን በዚህ መሰሉ ፀያፍ ተግባር ያኮላሹ እና የቀጩ አውሬዎች እስከመቼ በእስር ቤት ውስጥ እየተቀለቡ ህይወታቸውን እንዲመሩ ይፈቀድላቸዋል!??

በየጊዜው የህፃናት እገታ፣ ግድያ፣ እና የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን በሚዲያ ብቻ ተዘግቦ እየቀረ እንድንላመደው እየተደረገ ይመስላል:: በየቦታው በግጭት እና በጦርነት እያለቀ ያለው ህዝባችንን የሚታደገው አጥቷል::

ወንጀለኞች ተይዘው ተገቢውን ቅጣት አገኙ የሚለውን የፍትህ ዜና ሳንሰማ ሌላ ተመሳሳይ ድርጊት መፈፀሙን እንሰማለን::

ሀገሪቱ ላይ ያለው የህግ ስርዓት ይህን መሰል ሰይጣናዊ ድርጊት በሚፈፅሙ ላይ የማያዳግም እና መቀጣጫ የሚሆን የቅጣት ብይን የማያስተላልፍ በመሆኑ ወንጀለኞችን ከጥፋታቸው ከማቀብ ይልቅ የልብ ልብ የሰጣቸው ይመስላል::

ህፃናት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የነገ ህይወታቸው እንዲጨልም እየተደረገ ወንጀለኛው ግን ታስሮ የሚቀለብበት፣ ህፃናትን በግፍ ገድሎ እና አካል አጉድሎ፣ የነገን ሀገር ተረካቢዎች በአጭር እንዲቀጩ ያደረገን ወንጀለኛ በነፃነት ህይወቱን እንዲመራ መፍቀድ የወንጀሉ ተባባሪ ከመሆን አልያ ወንጀሉን ከማስቆም ይልቅ የማበረታት ያህል ነው::

ህይወትን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ለሚያጠፉ እና ለህፃናት ደፋሪ አረመኔዎች ተገቢው መቀጣጫ ሞት እንጂ ሌላ ሊሆን አይገባም::

ሞትን የደፈረ ሞት ብቻ ነው ሊያቆመው የሚችለው!!!

ዛሬ ላይ በሌሎች ህፃናት ላይ ደርሶ የሰማነው ጥቃት እንዲሁም በሌሎች ወላጆች ላይ የደረሰው ሀዘን እና ስብራት ነገ በኛም ቤት ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለንም::

መንግስት ህግ እንዲከበር እና ህግ እንዲፈራ ማድረግ ካልቻለ ወንጀልን መዳፈር እየቀለለ ጥፋት በምድሪቱ ላይ መስፋፋቱ አይቀሬ ነው::

ፍትህ የሚሰፍነው ለአጥፊዎች ተገቢውን ቅጣት በመስጠት ብቻ ሳይሆን ዳግም ያንን ወንጀል ለመፈፀም ማንም እንዳይነሳሳ አሳማሚ የቅጣት ህግ ተግባራዊ ሲሆን ብቻ ነው::

ለህፃን ሄቨን ወላጆች ብቻ ሳይሆን ጉዳያቸው በአደባባይ ያልተሰማላቸው በዚህ መልኩ ልጆቻቸውን በደፋሪዎች ተነጥቀው ፍትህን አጥተው በቤታቸው አልቅሰው የቀሩ ብዙ ወላጆችን እንባ ማበሻው ጊዜ ቅርብ ሊሆን ይገባል:: ለነዚህ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም የዚህን መሰሉ ወንጀል ለሚፈፅሙ አውሬዎች መቀጣጫ እና ማቀቢያ ይሆን ዘንድ በሀገራችን የሞት ቅጣት በፍትህ ስርኣታችን ውስጥ ሊካተት እንደሚገባ የሚመለከተውን የመንግስት አካል ከወዲሁ ሊያስብበት እና አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድበት ለመጠየቅ እወዳለሁ::

የሞት ቅጣት ህፃናትን ለሚደፍሩ እና ለሚገድሉ ወንጀለኞች የተገባ ነው!

በተጨማሪም በመላው ሀገሪቱ በግጭት እና በጦርነት ውስጥ እያጣነው ያለው የንፁሀን ነፍስ ብዙ ነው:: ይህ እንባ፣ ይህ ሞት በሁሉም መልኩ ሊያበቃ እንደሚገባ ማሳሰብ ያሻል:: አይደለም የብዙሀን ነፍስ ቀርቶ የአንዲትም ነፍስ መጥፋት እንዲህ ሁላችንንም ሊያንገበግበን የተገባ ነው:: ግጭቶች፣ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች ፣አፈናዎች፣ አስገድዶ መድፈሮች ይቆሙ ዘንድ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍትህ ሁላችንም በአንድነት እንጩህ ዘንድ መልዕክቴ ነው!

Justice for Feven
18/08/2024

Justice for Feven

14/08/2024

LOVE

Address

Nekemt

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Seid posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category