Abel Mena Halabo

Abel Mena Halabo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abel Mena Halabo, Grocers, Woliyta sodo, Sodo.

05/11/2025

✝️የአሰቸኮይ ግዜ ስልክ ቁጥሮች Part two ✅
➣በሰው እጅ ላይ እምኔታ ስታጣ.........1ኛቆ 13
➢አለም ከአንተ ጋር ስነጻጸር ትንሽ መስሎ ስሰማ መዝ 19
➣የጳውሎስ የደስታ ምስጢር ............ቆላ 3:12-17
➢ከሌሎች ሰዎች ጋር በሰላም ለመኖር ....ሮሜ 12
➢ፍሬ ለማፍራት ስትፈልግ............ዮሐ 15
➢የባንክ አካውንት ባዶ ስሆን..........መዝ 37
➢የጭንቀት ሀሳብ ስያስቸግርህ......መዝ 27
➢ሰዎች የወዳጅነት ስሜት ያሳዩ ስመስልህ...ዮሐ 15
👉በpart 3 ተለዋጭ ቁጡሮች አሉና በኮመንት
✍️part 3 ብላችሁ ጻፉ✍️
በተረፈ እንደተለመደው 🙏🙏🙏🙏✝️

14/10/2025

ጥሩ ምክር

እግዚአብሔር ይመሰገን እትዮጵያን እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች
08/09/2025

እግዚአብሔር ይመሰገን እትዮጵያን እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች

የሠው ልጅ መሰረታዊ  የህይወት  ህጎች!========================1. እራስህን እወቅ (Know Thyself):  •  ጥንካሬህን፣ ድክመትህን፣ እሴቶችህን እና ፍላጎቶችህን መረዳት...
12/04/2025

የሠው ልጅ መሰረታዊ የህይወት ህጎች!
========================
1. እራስህን እወቅ (Know Thyself):
• ጥንካሬህን፣ ድክመትህን፣ እሴቶችህን እና ፍላጎቶችህን መረዳት ለተሳካ እና ትርጉም ላለው ህይወት መሰረት ነው።

2. እውነትን ተናገር (Be Honest):
• ለራስህ እና ለሌሎች እውነተኛ መሆን መተማመንን ያሳድጋል እና ጥልቅ ግንኙነቶችን ይፈጥራል።

3. ኃላፊነትን ተቀበል (Take Responsibility):
• የራስህን ህይወት ባለቤት ሁን። ለድርጊቶችህ እና ለውሳኔዎችህ ኃላፊነት በመውሰድ ህይወትህን መቆጣጠር ትችላለህ።

4. ይቅር በል (Practice Forgiveness):
• ያለፈውን ቁርሾ መተው ለአእምሮ ጤንነትህ አስፈላጊ ነው። ይቅር ማለት ሌሎችን ብቻ ሳይሆን ራስህንም ነጻ ታወጣለህ።

5. አዳዲስ ነገሮችን ተማር (Seek Knowledge):
• በቀጣይነት መማር አእምሮህን ንቁ ያደርገዋል፣ አዳዲስ እድሎችን ይፈጥራል እንዲሁም የአለምን ግንዛቤ ያስፋፋል።

6. አመስጋኝ ሁን (Be Grateful):
• ለአንተ ላለው ነገር ማመስገን ደስታህን ይጨምራል እንዲሁም በአዎንታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት እንድታደርግ ይረዳሃል።

7. ጤናህን ጠብቅ (Take Care of Your Health):
• አካላዊ እና አእምሮአዊ ጤንነትህን መንከባከብ ለደስታ እና ለሙሉ ህይወት አስፈላጊ ነው። አመጋገብህን ተመልከት፣ እንቅስቃሴ አድርግ እና በቂ እረፍት አግኝ።

8. ግንኙነቶችን ገንባ (Build Relationships):
• ጠንካራ እና ደጋፊ የሆኑ ግንኙነቶችን መገንባት የስሜት ድጋፍን ይሰጣል እና የብቸኝነት ስሜትን ይቀንሳል።

9. አላማህን ፈልግ (Find Your Purpose):
• ሕይወትህን ትርጉም በሚሰጥ መንገድ መኖር የአእምሮ ሰላም እና እርካታን ያመጣል።

10. ተለዋዋጭ ሁን (Be Adaptable):
• ሕይወት ሁልጊዜ ለውጦችን ታመጣለች። ተለዋዋጭ መሆን እና ከአዳዲስ ሁኔታዎች ጋር መላመድ ጭንቀትን ለመቀነስ እና ስኬትን ለማረጋገጥ ይረዳል።

11. ለሌሎች መልካም ሁን (Be Kind):
• ለሌሎች ደግ መሆን ለአንተም መልካም ስሜት ይሰጥሃል። ደግነት ግንኙነቶችን ያጠናክራል እንዲሁም አዎንታዊ ተጽእኖ ይፈጥራል።

12. አደጋዎችን ለመውሰድ ዝግጁ ሁን (Take Risks):
• ከምቾት ቀጠናህ ውጪ መሄድ አዳዲስ እድሎችን እንድታገኝ እና እንድታድግ ይረዳሃል። ስሌት የተደረገባቸው አደጋዎች ወደ ትልቅ ስኬት ሊመሩ ይችላሉ።

13. ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም (Manage Your Time):
• ጊዜህን በአግባቡ ማቀድ እና ቅድሚያ መስጠት ግቦችህን ለማሳካት እና ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳሃል።

14. አሁን ላይ ኑር (Live in the Present):
• ያለፈውን መጸጸት ወይም ስለወደፊቱ መጨነቅ ብዙ ጊዜ ደስታችንን ይነጥቀናል። አሁን ላይ ትኩረት ማድረግ እና እያንዳንዱን ጊዜ መደሰት አስፈላጊ ነው።

15. ፅናት ይኑርህ (Be Persistent):
• ውድቀትን እንደ ማቆሚያ ሳይሆን እንደ ማሻሻያ ተመልከተው። ጽናት ግቦችህን እንድታሳካ ይረዳሃል።

02/10/2024

በእግዚአብሔር የምታምኑ እንድ ጽይሆን ተራራ ናቸው።

22/07/2024

የኩሪፍቱ ቃለ ሕይወት ጉዳይ በንግግር ለመፍታት እየተሞከረ ነው

| የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ዛሬ ቢሾፍቱ የሚገኘውን ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በኩርፍቱ ማዕከል በመገኘት አጠቃላይ የተፈጠረውን ችግሮች ተመልክተዉ ከከተማ አስተዳደር ተወካዮችም ጋር ምክክር አድርገዋል።

መሪዎቹ በቀጣይ የተፈጠረዉን ጉዳይ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስትያን ከፍተኛ አመራሮች ጋር እንዲሁም ከከተማ አስተዳደር ጋር የሚመካከሩ መሆኑን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።

12/07/2024

Address

Woliyta Sodo
Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abel Mena Halabo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category