Dunia abdi

Dunia abdi Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dunia abdi, Grocers, Sodo.

29/05/2026

መራጩ ሕዝብ ሰላሙ ተጠብቆ ድምፁን እንዲሰጥ አስተማማኝ ዝግጅት ተደርጓል - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2018(ኢዜአ)፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እና ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ፣ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በከፍተኛ ቅንጅት እና ቁርጠኝነት እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ በክልሉ እያከናወነ ያለውን መጠነ-ሰፊ የሰላም ማስከበር ሥራ አስመልክቶ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ድሪባ መኮንን በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው የቅድመ-ዝግጅት ምዕራፍ ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ከክልሉ እና ከፌዴራል የፀጥታ መዋቅሮች የተወጣጣ የጋራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ቀጣይነት ያለው ሥራ በትኩረት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላላ ምርጫውን ለማደናቀፍ እና በሕዝብ ላይ ሁከት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን የመለየት እና ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባሻገር በተከናወነው የተቀናጀ እና በተደራጀ የፀጥታ ማስከበር ሥራ፣ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት እጅግ ወሳኝ የሆኑት የምርጫ ቁሳቁሶች ያለምንም የፀጥታ እንቅፋት እና መስተጓጎል በተፈለገው ቦታ እና ጊዜ በሰላም መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።

የምርጫው ሂደት ፍፁም ሰላማዊ፣ ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተጀመረው የፀጥታ ጥበቃ እና የክትትል ሥራ ምርጫው ተጠናቅቆ ውጤት እስኪገለጽ ድረስ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

በመሆኑም የክልሉ ነዋሪዎች እና መራጮች በፍፁም ራስ መተማመን በምርጫው ዕለት በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን እንዲሰጡ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።

በየአካባቢው በልዩ ሁኔታ የተደራጀው የጋራ የፀጥታ ግብረ-ኃይልም አጠቃላይ የምርጫው ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሰላም እና የሕግ የበላይነትን የማስከበር ኃላፊነቱን በትጋት እንደሚወጣ መግለጻቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

29/05/2026
29/05/2026

በየትኛውም የምርጫ ጣቢያ 200 ሜትር ርቀት ውስጥ ሆኖ ለመዘገብ ባጅ የተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሚከተሉትን ግዴታዎች ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡-

👉 የሀገሪቱን እና የአካባቢውን ባህልና ልምድ ማክበር፤

👉 በቦርዱ የተሰጠውን የመታወቂያ ባጅ በሚታይ መልኩ በመያዝ መንቀሳቀስ፤

👉 የመራጭ ምዝገባ መረጃዎችን በሰነድ ላይ ሲሰፍሩ ወይም መራጩ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የምርጫ ምልክት ሲያደርግ አለመቅረጽ ወይም ፎቶግራፍ አለማንሣት፤

👉 ግለሰቡ በግልጽ እየተቃወመው መራጮችን እና ሌላ ማንኛውንም ሰው ፎቶ ወይም በተንቀሳቃሽ ምስል አለመቅረጽ እና ቃለ-መጠይቅ አለማድረግ፤

👉 የመራጮች ግላዊ ማንነትን በሚነካ አኳኃን መዝገብ፣ የመራጮችን ምዝገባ መታወቂያ ወይም ማንኛውንም ተመሳሳይ ሰነድ በፊልም አለመቅረጽ፣ ፎቶግራፍ አለማንሳት ወይም ኮፒ አለማድረግ፤

👉 የሕዝብን ሰብዓዊ መብትና መሠረታዊ ነፃነቶች ማክበር፤

👉 የቦርዱን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የፀጥታና የደኅንነት እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት አካላትን ሚና እና ሥልጣን ማክበር፣

👉 ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስለ ኃላፊነታቸው ምክር ወይም መመሪያ አለመስጠት፣

👉 መራጩ ድምፁን ለማን እንደሰጠ አለመጠየቅ፣

👉 የሕግ ጉዳዮችን በራስ አለመተርጎም እና የምርጫ ሂደትን የሚመለከት ሕጋዊ ያልሆነ መረጃ ወይም መመሪያ አለማስተላለፍ፣

👉 ለድምፅ መስጫ የተከለለ ቦታ ካሜራም ሆነ ሌላ የድምፅ ወይም የምስል መቅጃ መሣሪያ አለመጠቀም፣

👉 ከአድሎና ከወገንተኝነት በፀዳ አኳኋን ተግባራትን ማከናወን ይጠቀሳሉ።

21/09/18

29/05/2026
28/05/2026
28/05/2026

Address

Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dunia abdi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category