18/08/2026
እንኳን እየሰደቡህ እየመቱህ 'አትንኩኝ' ማለት አትችልም፤ ተነስተህ ከሚመቱህ ሰዎች ተነጥለህም አትሄድም፤ ራስህን አትከላከልም .. ጊዜ አስሮሃላ
እንዳውም ፈገግ ትላለህ.. በል የተባልከውን ትላለህ.. ዝቅ ብለህላቸው ይመቱሃል... ይትፉብህም .. ይስደቡህም .. ፈገግ ትላለህ.. ጊዜ ጥሎሃላ
ምክንያቱ ምንም ሊሆን ይችላል.. በምንም መንገድ ይሁን አሁን ሜዳው የ'ነሱ ነው ... አገዛዙ የ'ነሱ ነው.. እመር ብለህ ብትነሳ ምንም እንደማታመጣ ታውቀዋለህ.. እንዳውም የባሰ ሊመጣብህ እንደሚችል ታስብና ዝም.. ልክ እጁን በሰንሰለት ታስሮ ዘብጥያ እንደወረደ ታሳሪ ጊዜ በሚባል ካቴና ታስረሃል..
እንዳውም ያስብሉሃል... እንዲመቱህ ልትለምናቸው ትችላለህ..
ውስጥህ እየተንቦገቦገ ያለውን የንዴት እሳት በጥርስ ፈገግታ አዳፍነህ ዝም
ክብርህን አይነኬ ባይነትህ ልብህ ላይ ሲንተከተክ አይንህ ውስጥ ቀብረህ ጭጭ
ጊዜው ያንተ አይደለማ...
ምን እሷን ትላለህ... አንተ ራስህ ብለህ ማንም ክፍት ምላሱን ሲዘረጋብህ ዝም ብለህ አላለፍክም?.. የያዘህ አልያዘህም?
ጊዜ ይይዛል...
ጊዜ ባለጌ ነው...
አሁን ለእሷ.. ጊዜ ባለጌ ነው..
በኋላ ደግሞ ለእነሱ ይባልጋል... ወየውላቸው
አሁን ህግ የሚቀጣቸው አይደለም ያስፈራኝ.. ኋላ ካርማቸው ሲመጣላቸው ነው.. ኋላ የዘሩትን ሲሰበስቡ ነው...
(እኔን እህቴን😔)