Ethiopian Drama

Ethiopian Drama Ethiopian Drama, Movies, Music, Comedy and everything Ethiopian.

የቁንጅና አምባሳደራችን ሩት አዲስ አበባ ገብታለች!በ75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር (Miss World) ላይ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በኩራት ወክላ የተመለሰችው ውዷ እህታችን ሩት፣ ወደ እ...
08/09/2026

የቁንጅና አምባሳደራችን ሩት አዲስ አበባ ገብታለች!

በ75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር (Miss World) ላይ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በኩራት ወክላ የተመለሰችው ውዷ እህታችን ሩት፣ ወደ እናት ሀገሯ ስትመለስ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የክብር አቀባበል ተደርጎላታል።

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የብዙዎችን ቀልብ የሳበውና የብዙዎችን አንጀት የበላው አፍታ—የሩትና የአባቷ ስሜት ቀስቃሽ መገናኘት ነበር። በዓለም መድረክ ያሳየችውን ፅናትና ያመጣችውን ክብር ያዩት አባቷ፣ ልጃቸውን በሞቅታ አቅፈው ለረጅም ደቂቃዎች ፍቅራቸውን ሲገልጹ ይታዩ ነበር።

ሀዘኗን ወደ ብርታት ቀይራ፣ ባህሏንና ማንነቷን የሚያንጸባርቅ ባህላዊ አልባሳት አጊጣ ሀገሯን ስታስጠራ የቆየችው ሩት፤ ከአባቷና ከወዳጅ ዘመዶቿ ጋር ያሳየችው ይህ የስሜት ውህደት ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ፍቅርንና ጥንካሬን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስመስክሯል።

ሩት—ይህ አቀባበል ላሳየሽው የማይወላወል ጥረትና ለሀገርሽ ላስገኘሽው ክብር የሚገባሽ ጥቂት ስጦታ ነው።

እንኳን ወደ እናት ሀገርሽ በሰላም ተመለስሽ!

🇪🇹🙏

ጉርሻ page

ቢኒያም ሽብሬ ከማስተር ሀገረሰላም አርባ (ቦንጆ) ጋር በ Ethio Fight ይፋለማሉ!ከ16 ቀን በኋላ በጉጉት በሚጠበቀው የ Ethio Fight የትግል ውድድር ላይ፣ ቢኒያም ሽብሬ ከሌላኛው...
06/09/2026

ቢኒያም ሽብሬ ከማስተር ሀገረሰላም አርባ (ቦንጆ) ጋር በ Ethio Fight ይፋለማሉ!

ከ16 ቀን በኋላ በጉጉት በሚጠበቀው የ Ethio Fight የትግል ውድድር ላይ፣ ቢኒያም ሽብሬ ከሌላኛው ጠንካራ ተፎካካሪ ማስተር ሀገረሰላም አርባ (በቅፅል ስሙ "ቦንጆ") ጋር እንደሚፋለም ታውቋል።

ከአሜሪካ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ የገባው ቢኒያም ሽብሬ በአሁኑ ሰዓት ደማቅ አቀባበል እየተደረገለት የሚገኝ ሲሆን፣ የትውልድ አካባቢው የፈረንሳይ ሌጋሲዮን ወጣቶችም ለተፎካካሪው ልዩ የድጋፍ እና የአቀባበል ስነ-ስርዓት አዘጋጅተውለታል።

ሁለቱ ጠንካራ ስፖርተኞች የሚያደርጉት ይህ ታላቅ ፍልሚያ በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ግምትና ትኩረት አግኝቷል።

ይህንን ታላቅ ውድድር ጉርሻ ፔጅ በስፋት ሽፋን መስጠት ይጀምራል።

መልካም እድል ከወዲሁ ለሁሉም ተፋላሚዎች

Ethiopian Drama

💍❤️"አርቲስት ኤደን ሽመልስ ከተላከባት የሽምግልና ጥያቄ ‘እሺ’ ብላለች!ሽምግልናውን የላከው አርቲስትና ኮሜዲያን አንድነት አያሌው ሲሆን፣ በርካታ ታዋቂ አርቲስቶች በተገኙበት ሥርዓቱ በደስ...
05/09/2026

💍❤️

"አርቲስት ኤደን ሽመልስ ከተላከባት የሽምግልና ጥያቄ ‘እሺ’ ብላለች!

ሽምግልናውን የላከው አርቲስትና ኮሜዲያን አንድነት አያሌው ሲሆን፣ በርካታ ታዋቂ አርቲስቶች በተገኙበት ሥርዓቱ በደስታ ተፈጽሟል።

ለጥንዶቹ ያማረ የፍቅርና የትዳር ዘመን እንመኛለን!"

🙏🙏🙏

📷Chere Wedding Photographer

ሰበር ዜና፦ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ የ75ኛውን የዓለም ቁንጅና ዘውድ አሸነፈች!በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ቀልብ ሲስብ የቆየው የ75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር (Miss Wor...
05/09/2026

ሰበር ዜና፦ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ የ75ኛውን የዓለም ቁንጅና ዘውድ አሸነፈች!

በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ቀልብ ሲስብ የቆየው የ75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር (Miss World) ፍጻሜ አግኝቶ የአሸናፊዎች ዝርዝር ይፋ ሆኗል!

የአሸናፊዎች ደረጃ፦

1ኛ (የዘውዱ ባለቤት)፦ 🇩🇴 ዶሚኒካን ሪፐብሊክ

2ኛ (1st Runner-Up)፦ 🇪🇸 ስፔን

3ኛ (2nd Runner-Up)፦ 🇲🇾 ማሌዢያ

* የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ተወዳዳሪ አስደናቂ ብቃት በማሳየት የዘንድሮውን የዓለም ቁንጅና ዘውድ መደፋት ችላለች!

• የኤርትራዋ ተወዳዳሪ በሕዝብ ድምፅና በጠንካራ ውድድር ወደ ታላቁ Top 6 በመቀላቀል የአፍሪካና የቀጣናችን ኩራት ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።

• ኤርትራ እና ደቡብ አፍሪካ ወደ መጨረሻው ዙር አልፈው ድንቅ የውድድር ጊዜን አሳልፈዋል።

ተፈፀመ

“ቢሮው September 9, 2026 ይከፈታል”📌 USCIS🇺🇸🇪🇹  (U.S. Citizenship and Immigration Services) በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ቢሮ (International...
05/09/2026

“ቢሮው September 9, 2026 ይከፈታል”

📌 USCIS🇺🇸🇪🇹 (U.S. Citizenship and Immigration Services) በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ቢሮ (International Field Office) ሊከፍት ነው የሚለው ዜና ዛሬ፣ September 4, 2026 ተዘግቧል።

እንደ ዘገባው ቢሮው September 9, 2026 እንዲከፈት ታቅዷል።

🇺🇸 USCIS በአዲስ አበባ ቢሮ ለምን ይከፍታል?

ይህ ቢሮ በቀጥታ የአሜሪካ ቪዛ የሚሰጥበት ቢሮ አይደለም።

USCIS በውጭ አገር የሚከፍታቸው የInternational Field Offices ዋና ተግባር የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን በቀጥታ ከውጭ አገር ማስተናገድ፣ ሰነዶችን ማረጋገጥ እና ከአሜሪካ ኢሚግሬሽን ሂደቶች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ማከናወን ነው።

🇪🇹 ለኢትዮጵያውያን ምን ይጠቅማል? ከተባለ

ቢሮው ከተከፈተ በኋላ በተለይ በኢትዮጵያ ያሉ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን አመልካቾች እና ከአሜሪካ ውጭ የሚኖሩ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሰነድ ማረጋገጫ፣ የጉዳይ ሂደት እና ሌሎች USCIS ኃላፊነቶችን በቀላሉ ሊያስተናግድ ይችላል።
ነገር ግን “USCIS ቢሮ ተከፈተ = አሜሪካ ቪዛ በቀላሉ ይሰጣል” ማለት አይደለም። የቪዛ ቃለ-መጠይቅና ቪዛ መስጠት በዋናነት የU.S. Department of State እና የU.S. Embassy ሥራ ነው። በእርግጥ የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባ አሁንም የimmigrant visa አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የState Department መረጃ ያሳያል።

⚠️ ሌላ አስፈላጊ ነጥብ

ይህ ዜና የሚመጣው አሜሪካ በ2026 የኢሚግሬሽን እና የቪዛ ማጣሪያን በጣም በጠነከረችበት ጊዜ ነው። ለምሳሌ፣ State Department ከJanuary 21, 2026 ጀምሮ ከ75 አገሮች የሚመጡ የimmigrant visa አመልካቾች ላይ ጊዜያዊ እገዳ እንዳስቀመጠ አስታውቆ ነበር፤ ኢትዮጵያም በዚያ ዝርዝር ውስጥ ነበረች።

🇺🇸🇪🇹 ቢሮው በተለይ ምን ያደርጋል?

1. የሰነድ ማረጋገጥ ከኢሚግሬሽን ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የኢትዮጵያ ሰነዶች እውነተኛ መሆናቸውን USCIS ራሱ ያጣራል።

2. የኢሚግሬሽን ማጭበርበር ምርመራ የትዳር ጉዳይ፣ የቤተሰብ ግንኙነት፣ ሰነድ ወዘተ ላይ ጥርጣሬ ካለ USCIS በቀጥታ ምርመራ ማድረግ ይችላል።

3. DNA ምርመራ በተለይ የቤተሰብ ዝምድና ለማረጋገጥ DNA ማሰባሰብ/ሂደት ማካሄድ ከቢሮው ዋና ሥራዎች አንዱ ነው።

👨‍👩‍👧 ለቤተሰብ ስደተኞች ምን ማለት ነው?

ለምሳሌ አንድ ሰው በአሜሪካ ሆኖ ሚስቱን፣ ባልዋን፣ ልጁን ወይም ወላጁን ለማስገባት የimmigration petition ካቀረበ፣ በጉዳዩ ላይ የቤተሰብ ዝምድና ማረጋገጥ ካስፈለገ፣ አዲሱ የUSCIS ቢሮ በዚህ ሂደት ላይ ሊሳተፍ ይችላል።
እንዲሁም I-730 refugee/asylee following-to-join የመሳሰሉ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር ቀድሞውኑ የተያያዙ ነበሩ፤ USCIS በቀድሞ መረጃውም Addis Ababa ከI-730 ጉዳዮች የሚታወቅ ቦታ እንደነበር ጠቅሷል።

❗ ግን ይህን በግልጽ እንወቅ

USCIS ቢሮ = የአሜሪካ ኤምባሲ የቪዛ ቢሮ አይደለም።
ማለትም፦
❌ የTourist Visa ቪዛ አይሰጥም
❌ የStudent Visa ቪዛ አይሰጥም
❌ በዚያ ቢሮ ተገኝተህ “አሜሪካ ልሄድ” ብለህ ቪዛ አታገኝም

✅ የUSCIS የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን ይይዛል
✅ ሰነድ ያረጋግጣል
✅ የማጭበርበር ምርመራ ያደርጋል
✅ አስፈላጊ ሲሆን DNA ያሰባስባል።

📅 መቼ ይጀምራል?

September 9, 2026 ነው። እና አገልግሎቶቹ በappointment ብቻ እንደሚሰጡ USCIS ገልጿል፤ ያለ appointment በቀጥታ መግባት አይቻልም።

🤔 ለምን አሁን? ሆነ

USCIS የሚሰጠው ዋና ምክንያት የማጭበርበር መከላከልና የውጭ አገር ሥራውን ማጠናከር ነው። ከዚህ በፊት እነዚህ ሥራዎች በUSCIS እና በU.S. Department of State መካከል በመተባበር ይከናወኑ ነበር፤ አሁን ግን USCIS በኢትዮጵያ የራሱን ቀጥተኛ መገኘት እያቋቋመ ነው።

ይህ ሀሳብ አዲስ ብቻ አይደለም፤ USCIS ከዚህ በፊትም Addis Ababa ውስጥ ቢሮ ለመክፈት ሞክሮ ነበር፣ በ2013 ግን የState Department ፍቃድ አልሰጠውም።

«ተደብቄ ነው የገባሁት!... ማንም አያውቅም ነበር!» 😱የተወዳጁ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ ባለቤት ሀረገወይን ዘውዱ (ሐረጊቱ) ብዙዎች የማያውቋቸውን ያልተሰሙ የሕይወት ፈተናዎቿንና እውነታዎች...
05/09/2026

«ተደብቄ ነው የገባሁት!... ማንም አያውቅም ነበር!» 😱

የተወዳጁ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ ባለቤት ሀረገወይን ዘውዱ (ሐረጊቱ) ብዙዎች የማያውቋቸውን ያልተሰሙ የሕይወት ፈተናዎቿንና እውነታዎችን በይፋ አጋራች!
ብዙዎቻችን የምናውቃት የዝነኛውና ተወዳጁ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የሕይወት አጋር መሆኗን ብቻ ነው።
ነገር ግን ከዚህ ታዋቂ ስም ጀርባ ያለፈችበት የሕይወት ውጣ ውረድ፣ በድብቅ የጀመረችው የጥበብ ጉዞና ዛሬ ላይ የደረሰችበት ማንነት እጅግ አስደናቂና ያልተጠበቀ ነው።
ሐረገወይን በቤተሰቧ ውስጥ በሰባት ወንዶች መሃል ብቸኛ ሴት ሆና ያደገች ብርቱ እንስት ናት። ገና በወጣትነቷ ወደ ጥበቡ ዓለም ለመግባት ቤተሰቦቿ እንደማይፈቅዱላት ስታውቅ፣ «የቋንቋ ትምህርት አለኝ» በሚል ሰበብ ከቤተሰብ ተደብቃ ነበር በመከላከያ የባህል ክፍል ውስጥ በውዝዋዜ ሙያ ተወዳድራ የተቀጠረችው። በውዝዋዜው ዓለም በርካታ ፈተናዎችን አልፋ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ሰርታለች። ከዚያም አልፎ ከቀድሞ ኮሜዲያኖች ጋር ጭምር እርጉዝ በነበረችበት ወቅት አስቂኝ ድራማዎች ላይ ተሳትፋ እንደነበር በሳቅና በናፍቆት ታስታውሳለች።
ይሁን እንጂ ትልቁ ፈተና የመጣው ትዳር ከያዘች በኋላ ነበር። ብዙ ጊዜ በማኅበረሰባችን ውስጥ የታዋቂ ሰው ባለቤት ስትሆን ሰዎች አንቺን እንደራስሽ ማንነት ሳይሆን እንደ «የእከሌ ሚስት» ብቻ የመመልከት አባዜ አለባቸው።
በተለይ ከወሊድ በኋላ ያጋጠማትን የሰውነት ክብደት ለውጥ አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያውም ሆነ በአካባቢዋ የተሰነዘሩባት ትችቶች ቀላል አልነበሩም። ክብደቷን ለመጨመር አብሽ ስትጠጣ የነበረችበትን፣ በኋላም በስፖርት ክብደቷን ስትቀንስ «ምነው ከሳች? ምን ሆና ነው?» የሚሉ አጉል ወሬዎች ሲነዙባት እንደነበር በግልጽ ተናግራለች። እርሷ ግን እንዲህ ላሉ አሉባልታዎች ጆሮ ሳትሰጥ፡ «ሰዎች በራሳቸው መነፅር ሊፈርዱብሽ ይችላሉ፤ ዋናው ነገር አንቺ ራስሽን ማወቅሽና በራስሽ መተማመንሽ ነው» በሚል በሳቅ ታሳልፈዋለች።
ሐረግ የባለቤቷን ስም ተገን አድርጋ እጅ አጣጥፋ የተቀመጠች ሴት አይደለችም። ልጆቿን ክርስቲያንን እና ኪያምን በገዛ እጇ ለማሳደግ ለዓመታት ሙሉ ትኩረቷን ለቤቷና ለልጆቿ ከሰጠች በኋላ፣ ዛሬ ላይ የራሷን የንግድ አሻራ ማሳረፍ ችላለች። «ሀጊ የውበት ማሰልጠኛ» (Hagi Beauty School) የተሰኘ ተቋም በመክፈት በርካታ ወጣቶችን በሜካፕ፣ በፀጉር እና በውበት ጥበብ ሙያ እያሰለጠነች ራሳቸውን እንዲችሉ እያደረገች ትገኛለች።
«የግሩም ሚስት መሆኔን አከብረዋለሁ፤ እወደዋለሁ፤ እርሱም ትልቅ ደጋፊዬ ነው። ነገር ግን እኔ ሐረግ ነኝ! የራሴ ስራና ማንነት ያለኝ ሴት ነኝ» በማለት አንዲት ሴት ከማንም ጥላ ስር ሳትሸሸግ የራሷን ስም ማስጠራት እንዳለባት አስመስክራለች። በማሰልጠኛዋ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን በማብቃት ብቻ ሳትወሰን፣ ማልዳ ተነስታ የቤቷን ማዕድ በራሷ እጅ የምታዘጋጅ፣ ቤተሰቧን በሙሉ ፍቅር የምትንከባከብ እውነተኛ እናትና ታታሪ የንግድ ባለቤት ናት።
ይህ የሐረገወይን ታሪክ ለብዙዎቻችን ሴቶች ትልቅ ማስተማሪያ ነው፤ የትዳር አጋርሽ የቱንም ያህል ዝነኛ ቢሆን፣ የራስሽን ህልም ከመኖርና የራስሽን ማንነት ከማሳየት ወደኋላ ማለት የለብሽም! 👏
የራስሽን ማንነትና ክብር በራስሽ ጥረት ስትገነቢው ውበትሽ ሙሉ ይሆናል!

ህፃን ልጅ አግታ 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡ ወንጀል ፈፃሚዋን በቁጥጥር ለማዋል በተደረው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና...
03/09/2026

ህፃን ልጅ አግታ 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

ወንጀል ፈፃሚዋን በቁጥጥር ለማዋል በተደረው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ መቅደስ ሞገስ የተባለች የቤት ሰራተኛ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ አቶ ሰለሞን ፋንታሁንና ወ/ሮ ሄለን ኃይለሚካል መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ለሶስት ወራት ስትሰራ ቆይታ ቤተሰብ ለመጠየቅ ፈቃድ ጠይቃ ሳትመለስ ትቀራለች፡፡

ወንጀል ፈፃሚዋ ከአንድ ግብረ አበሯ ጋር በመሆን ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ ወደ አሰሪዎቿ ሰፈር በመምጣት የሰባት ዓመቷን ህፃን ፊዮና ሰለሞንን ከምትጫወትበት ስፍራ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ይዛ ትሰወራለች፡፡

የግለሰቧ ግብር አበር ለህፃኗ ወላጅ 3 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉት በስልክ ይገልፅላቸዋል፡፡ ቤተሰቧ የግለሰቡን ዛቻ በመፍራት 370ሺ ብር በባንክ ገቢ ያደርጉለታል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በቴክኖሎሎጂ በመታገዝ ባደረገው ክትትል ግለሰቧ ህፃኗን አግታ ወደ አማራ ክልል ይዛ መሰወሯን ይደርስበታል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዋን በጎንደር ከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ጫካ ውስጥ በተደረገ ክትትል እና ጥቆማ እንደተያዘች ዋና ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል፡፡

ህፃኗ በጥሩ ደህንነት ላይ እንደምትገኝ የገለፀው ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዋን በቁጥጥር ለማዋል በተደረው ጥረት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እና የጎንደር ከተማ ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች የፀጥታ ተቋማት ላደረጉት ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ሰዎች የቤት ሰራተኛ ሲቀጥሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ዋና ጠቅላይ መምሪያው መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

Addisababapolice

ሰማይ ላይ የተጻፈ ስማችን!የጉዞ ማስታወሻተስፋዬ እሸቱ (ረዳት ፕሮፌሰር)ከሰሞኑ ጣሊያን በነበረን የትያትር ሥልጠና “I am from a place where…” የሚል የጌም መልክ ያለውና ወደዋ...
31/08/2026

ሰማይ ላይ የተጻፈ ስማችን!
የጉዞ ማስታወሻ
ተስፋዬ እሸቱ (ረዳት ፕሮፌሰር)

ከሰሞኑ ጣሊያን በነበረን የትያትር ሥልጠና “I am from a place where…” የሚል የጌም መልክ ያለውና ወደዋነው ጉዳይ የሚያንደረድር አንድ ጨዋታ እንጫወት ነበር።
አጨዋወቱ ቀላል ነው። በክብ ተቀምጠን አንድ ሰው መሀል ይቆማል። “I am from a place where…” ብሎ ከመጣበት ማኅበረሰብ፣ ባህል ወይም የኑሮ ልምድ ጋር የሚያያዝ አንድ ነገር ይናገራል። የተናገረውን ሐሳብ የሚጋሩ ሰዎች ከወንበራቸው ተነስተው ቦታ ይቀያየራሉ። ቦታ ያጣው ደግሞ መሀል ቆሞ የራሱን “I am from a place where…” ይናገራል፤ ጨዋታውም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል።
አብዛኛውን ጊዜ የሚያነሷቸው ጉዳዮች ከእኔ ልምድ ጋር የማይገጥሙ፣ እኔም የማልጋራቸው ስለነበሩ ከመቀመጫዬ አልተነሳሁም። ዝም ብዬ የሚሉትን እከታተል ነበር። ድንገት አንዷ አሜሪካዊት፣ “የመጣሁት በነጭና በጥቁር መካከል ኢፍትሐዊነት ካለበት ቦታ ነው” አለች። ብዙዎቹ ተነሱ። እኔም አሰብኩ። በአገሬ የነጭና የጥቁር መከፋፈል በዚያው መልክ ባይኖርም፣ እኔ ጥቁር ነኝ። ስለጥቁር ማንነትና መብት የተነሳ ጉዳይ ነውና “እኔ ታዲያ እዚህ ተቀምጬ ምን እሠራለሁ?” ብዬ ከመቀመጫዬ ተነሳሁ።
ስለጉዳዩ እያሰብኩ ስለነበር ዘወር ስል ቦታዬ ተይዟል! መሀል ቆሜ “ምን ልበላቸው?” እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ። ሁሉም ዓይን ዓይኔን ሲመለከተኝ፦
“I am from a place where our airline is part of our identity.”
“የመጣሁት እንደ ዓይናችን ብሌን የምናየው አየር መንገዳችን የማንነታችን አካል ከሆነበት አገር ነው።” እንደማለት ነው።
ዙሪያዬን አየሁ።
የሚነሳ አጣሁ!
አንድም የጨዋታው ተሳታፊ ከመቀመጫው አልተነሳም። ግራ ገባኝ። እኔም እዚያው መሀል ቆሜ ቀረሁ። ምንም እንኳ የጨዋታው ሕግ መጠየቅን ባይፈቅድም፣ አለመነሳታቸው ቆረቆረኝ። የመጣው ይምጣ ብዬ፦
“ለምን አልተነሳችሁም?” አልኳቸው።
መልሳቸው የተለያየ ነበር። ለአንዳንዶቹ አየር መንገድ በዋናነት የመጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው። አንዳንዶቹማ “የእኛ” የሚሉት ተወዳዳሪ ብሔራዊ አየር መንገድ እንኳ የላቸውም። ለሌሎቹ ደግሞ የሀገራቸው መለያ ቢሆንም፣ እስከ “የማንነቴ አካል ነው” የሚያስብል ግንኙነት ከአየር መንገዳቸው ጋር አልነበራቸውም።
ምናልባት “የመጣሁት ሽማግሌዎች ከሚከበሩበት ቦታ ነው” ብዬ ቢሆን ኖሮ ከወንበራቸው የሚነሱ ይኖሩ ነበር። “የመጣሁት ቤተሰብ ትልቅ ቦታ ከሚሰጠው ማኅበረሰብ ነው” ብል፣ ወይም “የመጣሁት እንግዳ በክብር ከሚቀበልበት ቦታ ነው” ብል፣ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሰዎች ሐሳቡን ሊጋሩኝ ይችሉ ነበር። እነዚህ በብዙ ማኅበረሰቦች የሚጋሩ እሴቶች ናቸውና።
አየር መንገድን ከማንነት ጋር ሳገናኝ ግን ሐሳቡን የሚጋራኝ አጣሁ።
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ውስጤ ቀረ።
እንዴት ነው አንድ የንግድና የመጓጓዣ ተቋም ከተራ ተቋምነት አልፎ የሕዝብ የጋራ ማንነትና ኩራት አካል የሚሆነው?....መልሱ “የሀገራችንን ባንዲራ ይዞ ስለሚበር” ብቻ አይደለም። እንዲያውም ይህ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ የተሰጠ ልዩ ነገር አይደለም። በዓለም ላይ ብዙ flag carriers የሀገራቸውን ባንዲራ፣ ብሔራዊ ቀለማት ወይም ሌሎች የሀገር ምልክቶች በአውሮፕላኖቻቸው ላይ ይዘው ይበራሉ።
ታዲያ የእኛን ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?....
ለእኔ ልዩነቱ ባንዲራውን መሸከሙብቻ አይደለም። ያንን ባንዲራና “Ethiopian” የሚለውን ስም ከተቋማዊ ቀጣይነት፣ ከውድድርና ከስኬት ጋር ማያያዝ መቻሉ ነው። የኢትዮጵያን ስም ይዞ ለዓመታት ተወዳድሯል። በውድድሩ ውስጥ ብቻ አልቆየም፤ አድጓል፣ መዳረሻዎቹን አስፍቷል፣ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ገበያ ውስጥም ተወዳዳሪ ተቋም ሆኗል። በሀገራችን የተለያዩ ዘመናት፣ መንግሥታትና ፈተናዎች ሲፈራረቁ፣ እሱ ግን ትውልድ ተሻግሮ “Ethiopian” የሚለውን ስም ይዞ ቀጥሏል። ምናልባት የማንነት ጉዳዩ የሚጀምረውም እዚህ ላይ ነው። ማንነት በስም፣ በባንዲራና በቀለም ብቻ አይገነባም፤ በታሪክ፣ በቀጣይነት፣ በስኬትና በጋራ ትውስታም ይገነባል።
ስለዚህ በሌላ ሀገር አየር ማረፊያ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዩን ጭራ ከሩቅ ስናይ፣ የምናየው ቀለም ብቻ አይደለም። ከዚያ ቀለም ጀርባ ያለውን ስም፣ ታሪክ፣ ቀጣይነትና ስኬትም ነው። በዚህም አየር መንገዳችን ከተራ የመጓጓዣ ተቋምነት አልፎ የጋራ ትውስታችንና ኩራታችን አካል ሆኗል። በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያገኘው ቦታም ከዚህ የመጣ ነው።
ከጨዋታው በኋላም ለሥልጠናው ከተለያዩ ሀገራት ለመጡት የትያትር ባለሙያዎች ደረቴን ነፍቼ ነገርኳቸው፤ አየር መንገዳችን ከA ወደ B የሚያደርሰን የመጓጓዣ ተቋም ብቻ አይደለም። “Ethiopian” የሚለውን የሀገሬን ስም ይዞ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ መልክ በሰማይ ላይ የሚዞር፣ ታሪካችንን ሰማይ ላይ ያተመ ስማችን ነው፡፡ መቸስ ከዚህ በኋላ የኢትዮዽያን አየር መንገድ ሲያዩ እንደ ቀላላ አየር መንገድ እንደማይወስዱት ተስፋ አለኝ፡፡
አዎ፣ እኔ ሁሌም እንዲህ እላለሁ፦
“I am from a place where our airline is part of our identity.”
የመጣሁት አየር መንገዳችን የማንነታችን አካል ከሆነበት አገር ነው።
ደህና አምሹ!

ናይጄሪያውያን 2ኛ ደረጃን ከኢትዮጵያዊቷ ሩት ይርጋለም ተረባርበው ነጠቁ!በዓለም አቀፉ የሚስ ወርልድ (Miss World) የቁንጅና ውድድር በአፍሪካ አህጉር Round 1 የሕዝብ ድምፅ አሰጣጥ...
29/08/2026

ናይጄሪያውያን 2ኛ ደረጃን ከኢትዮጵያዊቷ ሩት ይርጋለም ተረባርበው ነጠቁ!

በዓለም አቀፉ የሚስ ወርልድ (Miss World) የቁንጅና ውድድር በአፍሪካ አህጉር Round 1 የሕዝብ ድምፅ አሰጣጥ ላይ አገራችንን ወክላ የምትወዳደረው ሞዴል ሩት ይርጋለም በ2.29 ሚሊዮን በላይ ድምፅ በ3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በሕዝብ ብዛታቸው ከአፍሪካ አንደኛ የሆኑት ናይጄሪያውያን ባደረጉት የተቀናጀ የድምፅ አሰጣጥ፣ ተወዳዳሪያቸው ሶዬ ካሪቢ-ጆርጅ 2.76 ሚሊዮን በላይ ድምፅ በማግኘት 2ኛ ደረጃን ተቆጣጥራለች።

ይህ የመጀመሪያ ዙር የህዝብ ድምፅ አሰጣጥ ሊጠናቀቅ የቀረው 6 ቀን ብቻ በመሆኑ አሁን እያንዳንዱ ሰከንድ እና ድምፅ ወሳኝ ነው!
የወቅቱ የአፍሪካ አህጉር Round 1 የድምፅ ደረጃ (Current Standings)

ደረጃ ሀገር ተወዳዳሪ ያገኘችው ድምፅ ከኢትዮጵያ (ሩት) ያለው የድምፅ ልዩነት

1ኛ ኤርትራ ስኒት ሀብተአብ 5,266,497 2,973,332 ድምፅ ይበልጣል

2ኛ ናይጄሪያ ሶዬ ካሪቢ-ጆርጅ 2,763,769 470,604 ድምፅ ይበልጣል

3ኛ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም 2,293,165

የህዝብ ድምፅ አሸናፊ (People's Choice Winner): በቀጥታ ወደ Top 6 ተቀላቅላ ለዋናው አክሊል ትወዳደራለች።

የአህጉራት አሸናፊዎች (Continental Winners): በቀጥታ ወደ Top 40 ያልፋሉ።

የድምፅ መደመር: በRound 1 የሚሰበሰቡ ድምፆች በሙሉ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚሸጋገሩ (Carry over) በመሆናቸው እያንዳንዱ ድምፅ ዋጋ አለው!

ሩት ይርጋለም 2ኛ ደረጃ ላይ ከምትገኘው ናይጄሪያዊት ጋር ያላትን 470,604 የድምፅ ልዩነት በማጣበብ በቀላሉ ወደ 2ኛ ደረጃ፣ እንዲሁም ከኤርትራዋ ተወዳዳሪ ጋር ያለውን የ2,973,332 ድምፅ ልዩነት በመቀነስ ወደ 1ኛ ደረጃ ማለፍ ትችላለች!

ቀሪው 6 ቀን ሳይጠናቀቅ በውጭ ሀገር የምትኖሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት (Diaspora Community) እና በሀገር ውስጥ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፦ እባካችሁ ይህንን መረጃ በስፋት Share በማድረግ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ በማስተላለፍ እና ድምፅ በመስጠት የሀገራችንን ተወካይ ከጎኗ በመቆም እንቀላቀል!

2ኛ ደረጃ ላይ ሆኖ መጨረስ ራሱ ከባድ ትልቅ እድል ነው እባካችሁ ወደ ቦታዋ ወደ ነበረችበት እንኳን እንመልሳት አረ እባካችሁ ሼር

PLEASE 🙏

ጉርሻ page

የምሽቱ ትልቁ ፍልሚያ፡ ጆኒ አዲሱ የ ETFC 2 ቻምፒዮን ሆኗል! በknock out what a game 😮በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው የኢቲኤፍሲ 2 (ETF...
28/08/2026

የምሽቱ ትልቁ ፍልሚያ፡ ጆኒ አዲሱ የ ETFC 2 ቻምፒዮን ሆኗል!

በknock out what a game 😮

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው የኢቲኤፍሲ 2 (ETFC 2) ኮከቦች ምሽት በጉጉት በተጠበቀውና በዋናው የዋንጫ ፍልሚያ (Main Event) በይፋ ፍጻሜ አግኝቷል!

በሚድል ዌይት (Middleweight MMA Bout) ዘርፍ በጆኒ እና በሴዶ መካከል የተደረገው ይህ አስደናቂና አቃጣጣኝ ፍልሚያ የመላው ተመልካች ቀልብ የሳበ ነበር።

በከፍተኛ የኤምኤምኤ (MMA) ቴክኒክ፣ የላቀ ብቃትና ፍጹም የድል ወኔ ተጋጣሚውን ሴዶን ያሸነፈው ጆኒ፡ የምሽቱን ትልቅ ድል በመቀዳጀት አዲሱ የ ETFC 2 ቻምፒዮን (Champion) በመሆን ዘውዱን ደፍቷል!

እንኳን ደስ አለህ ጆኒ!

ላሳየኸው አስደናቂ የኤምኤምኤ (MMA) ብቃትና ላስመዘገብከው ታሪካዊ የቻምፒዮንነት ድል እንኳን አበቃህ!

ለተሳተፉት ተዋጊዎቻችን በሙሉ እና ሙሉ ውድድሩን በስኬት ላጠናቀቁት አዘጋጆች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!

እንዴት አያችሁት ጭዋታውን ሀሳባችሁ አካፉሉን..

Address

London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Drama posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share