17/07/2026
"የደብረ ብርሃን ከተማ ምክር ቤት4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 50ኛ መደበኛ ጉባኤ" በቀረበው ሪፓርት በኢኮኖሚ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን የደብረ ብርሃን ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት ካቀረቡት ሪፓርት የተወሰደ
በ2018 በጀት ዓመት አስደናቂና ካቀደችው በላይ የሆኑ የኢኮኖሚ ውጤቶችን አስመዝግባለች። የከተማችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና የልማት ጉዞ የሚያሳዩ ዋና ዋና ስኬቶችን
🏭 ኢንደስትሪ፣ ኢንቨስትመንትና የውጭ ምንዛሬ
ከተማችን አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብና ነባሮችን በማጠናከር ረገድ ፡
👉አዳዲስ ባለሀብቶችና ፈቃድ: 142 አዳዲስ ባለሀብቶች የተመለመሉ ሲሆን 228 ባለሀብቶች ደግሞ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል (ከዕቅድ በላይ)።
👉የተመዘገበ ካፒታል: በአጠቃላይ 29.62 ቢሊዮን ብር ካፒታል ተመዝግቧል።
👉የገበያ ፍላጎት መተካት: 43 አምራች ኢንዱስትሪዎች 589.33 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሀገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ችለዋል።
👉የውጭ ምንዛሬ ግኝት: 12 አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ በመላክ 137.54 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝተዋል።
👉የመሠረተ ልማት ድጋፍ: ለፕሮጀክቶች የሚሆን 6.67 ቢሊዮን ብር የሊዝና የፋይናንስ ብድር የተመቻቸ ሲሆን፣ 155 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት 33.3 ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመር ተዘርግቷል።
💼 የስራ ዕድል ፈጠራ
በከተማዋ በአጠቃላይ 17,703 የስራ ዕድሎች የተፈጠሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 11,278 ቋሚ እና 6,425 ጊዜያዊ ናቸው።
ወደ ስራ በገቡ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ብቻ 5,651 ቋሚ የስራ ዕድሎች (3,215 ወንዶች እና 2,436 ሴቶች) ተፈጥረዋል።
🏗️ መሠረተ ልማት፣ ቤቶችና የኮሪደር ልማት
👉የቤት ግንባታ: በተለያዩ አማራጮች 3,210 መኖሪያ ቤቶች ተገንብተዋል (ዕቅዱ 2,137 ነበር)።
👉መንገዶች: 2.99 ኪ.ሜ የኮብልስቶን መንገድ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የ5 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ ግንባታ በሂደት ላይ ይገኛል።
👉የኮሪደር ልማት: ከበሬሳ እስከ መሃል ከተማ የሚዘልቀው 3 ኪ.ሜ የኮሪደር ልማት ስራ 90% ደርሷል።
👉የህዝብ ተሳትፎ: ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ 264.2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል።
🗺️ የመሬትና ማዕድን አስተዳደር
👉የካሳ ክፍያ: ለካሳና መልሶ ማቋቋም ስራ 410 ሄክታር መሬት የተለቀቀ ሲሆን 1.63 ቢሊዮን ብር ካሳ ተከፍሏል።
👉የይዞታ ማረጋገጫ: 5,557 ይዞታዎች በወረቀትና በሲስተም ተመዝግበው 5,342 የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶች ተሰራጭተዋል።
👉የማዕድን ገቢ: ከሮያሊቲ፣ ከቁርጥ ዋጋና ከተዛማጅ አገልግሎቶች ከፍተኛ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን፣ 19 የባህላዊና አነስተኛ ማዕድን ማምረት ፈቃዶች ተሰጥተዋል።
🌾 ግብርና፣ እንስሳትና ህብረት ስራ ማህበራት የሰብል ምርት: 22,698 ሄክታር መሬት በመልማቱ 819,725.85 ኩንታል ምርት ተገኝቷል።
👉የእንስሳት ሃብት: 52,106 ቶን የስጋ ምርት የቀረበ ሲሆን፣ 698,600 የአንድ ቀን ጫጩቶች ለአርቢዎች ተሰራጭተዋል።
👉የወተት ግብይት: 4.4 ሚሊዮን ሊትር ወተት ለገበያ ቀርቧል።
የህብረት ስራ ማህበራት: 3,036 አዳዲስ አባላትን በመቀበል ጠቅላላ ካፒታላቸውን ወደ 146 ሚሊዮን ብር አሳድገዋል (ከዕቅዱ 14 ሚሊዮን ብር እጅግ የላቀ)።
🎯 በአጠቃላይ፤ ደብረ ብርሃን የኢንቨስትመንት፣ የስራ ዕድል እና የልማት ተምሳሌትነቷን በተግባር እያስመሰከረች ትቀጥላለች!
#ደብረብርሃን #ኢንቨስትመንት #ልማት #ብልጽግና