Romi catering

Romi catering የጾም የፍስክ ምግቦች ለሰርግ፣ ለልደት እና ለተለያዩ ዝግጅቶች ለወንደላጤዎች ለቤተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በትእዛዝ እንሰራለን። በተጨማሪም ለክትፎ ፣ ለወጥ የሚሆን የተነጠረ ቅቤ ፣ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ካስፈለግዎ ይደውሉልን::

01/20/2023
በዋሽንግተን ዲሲ እና አከባቢው ለምትኖሩ ኢትዮ-ኤርትራውያን በሙሉ ቤተሰብ ጥየቃ ለመሄድ ፣ ሃዘን ለመድረስ እየፈለጉ በስራ ብዛት ሳይመችዎ ቀርተው ምን ይዤ መሄድ እችላለሁ ብለው ተጨንቀዋል?...
11/27/2022

በዋሽንግተን ዲሲ እና አከባቢው ለምትኖሩ ኢትዮ-ኤርትራውያን በሙሉ
ቤተሰብ ጥየቃ ለመሄድ ፣ ሃዘን ለመድረስ እየፈለጉ በስራ ብዛት ሳይመችዎ ቀርተው ምን ይዤ መሄድ እችላለሁ ብለው ተጨንቀዋል? እንግዲያውስ አይጨነቁ ሮሚ ኬተሪንግ በፈለጉት መጠንና አይነት የፆም/የፍስክ/ አገልግል ሰርተን ያሉበት ድረስ የምናቀርብ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

እርድ የሚሰጣቸው በርካታ የጤና በረከቶች******************************እርድ የዝንጅብል ዘር ሲሆን ብዙ ግዜ በቅመም መልክ ከምግብ ጋር ተዋህዶ ይዘጋጃል።የእርድ ቅመም ለመስራ...
11/15/2022

እርድ የሚሰጣቸው በርካታ የጤና በረከቶች
******************************
እርድ የዝንጅብል ዘር ሲሆን ብዙ ግዜ በቅመም መልክ ከምግብ ጋር ተዋህዶ ይዘጋጃል።
የእርድ ቅመም ለመስራት የእርድ ተክል ስር ከ30-45 ደቂቃ ይቀቀላል። ከዛም ምድጃ ውስጥ ገብቶ እንዲደርቅ ይደረግና ቅመም ይዘት እስኪኖረው ይፈጫል። እርድ ከእኛ ሃገር አልፎ በህንድ እና ፓኪስታን ከፍተኛ ተጠቃሚነት ያገኘ ምግብ ነው።
እንደ ዩኤስዲኤ ኒውትሪየንት ዳታቤዝ አንድ ሻይ ማንኪያ እርድ 29 ካሎሪ፣ 0.9 ግራም ፕሮቲን፣ 0.3ግራም ፋት እና 6.3ግራም ካርቦሃይድሬት ይይዛል። የአይረን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ፖታሲየም እና ማንጋኒስ ይዘትም አለው።
እርድ መብላት ለጤና የሚሰጠው ጥቅም
የእርድ በርካታ ጤና ጥቅሞች ውስጡ የሚገኙ ከርኪውሚን ተብለው የሚጠሩ ንጥረነገሮች ውጤት ነው። ለእርድ ጣእም የሚሰጡት እነዚህ ከርኪውሚን የተባሉ ንጥረነገሮች ናቸው።
ለሆድ መፍጨት
ከርኪውሚን የሃሞት ቀረጢት ሃሞት እንዲያመነጭ በማድረግ ምግብ መፍጨትን ይረዳል ተብሎ ይታመናል። እርድ በሆድ መፍጨት ችግር መነፋት እና ፈስ የሚያስቸግራቸውን ሰዎች እንደሚረዳ አንድ ጥናት ይናገራል።
የቃጠሎ ስሜት ያስታግሳል
ከርኪውሚን የተለያዩ ህመሞች የሚያመጡትን የቃጠሎ ስሜት የሁለት ኢንዛይሞችን መጠን በመቀነስ ያስታግሳል።
የሚከተሉት በሽታዎች በሰውነታችን የቃጠሎ ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፦
• የልብ በሽታ
• ስኳር
• ስትሮክ
• አርትራይተስ(የአጥንት መገጣጠሚያ በሽታ)
• አይቢኤስ
• ካንሰር
• አልዛይመር
ከርኪውሚን እንደ ተፈጥሮአዊ ጸረ-ቃጠሎ ህክምና ሊያገለግል ይችላል።
የልብ ህመም
እርድ ሰውነት ውስጥ የሚፈጠርን የደም መርጋት ይከላከላል። ቅድመ-ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በደም ቧንቧ የሚፈጠርን የፕላክ(ቆሻሻ) ክምችት ሳይቀንስ አይቀርም። እንስሶች ላይ በተደረገ ሙከራ እርድ የኮሌስትሮል መጠን እንደሚቀንስ ማየት ተችሏል። ነገር ግን ሰዎች ላይ በተደረገ ሙከራ የተጠበቀውን ያህል ለውጥ አላሳየም።
የእርድ ጸረ-ቃጠሎ ባህሪ ለልብ ጤና ይጠቅማል። እንስሶች ላይ በተደረገ ሙከራ የእርድ ጸረ-ቃጠሎ እና ጸረ-ኦክሲዳንት ባህሪ የሚከተሉትን የጤና ጥቅሞች አስከትሏል፦
•የሰውነት ክብደት መቀነስ
•ሜታቦሊክ ሬት መጨመር
•ኢንሱሊን ሴንሲቲቪቲ መጨመር
እነዚህ የጤና ለውጦች የልብ ህመም ተጋላጭነታችንን ይቀንሳሉ። ነገር ግን በእርግጠኝነት ለመናገር የጥናቱ ውጤቶች በሰው ላይ መደገም ይኖርባቸዋል።
ካንሰር
ቅድመ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የእርድ ጸረ-ቃጠሎ እና ጸረ-ኦክሲዳንት ባህሪዎች ካንሰር ከመፈጠሩ በፊት ለመከላከል እንደሚረዳ ይናገራሉ። ነገር ግን የበለጠ ጥናት የሚያስፈልገው ነገር ነው።
የአእምሮ ጤና
እርድ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች የአእምሮ ብቃት ከሚያዳክሙ በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል። ዲሜንሺያ በሽታ በታየባቸው 1000 አዛውንቶች ላይ በተሰራ ጥናት በህይወታቸው እርድ ይመገቡ የነበሩት አዛውንቶች የአእምሮ ጤንነታቸው ከሌሎቹ ታካሚዎች የተሻለ ሁኖ ተገኝቷል።
የስኳር በሽታ
ኦክሲዴቲቭ ጭንቀት እና የቃጠሎ ስሜት የስኳር በሽታ እንዲጀምር ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። እርድ ውስጥ የሚገኘው ከርኪውሚን ጣፊያ ኢንሱሊን እንዲያመርት በማድረግ የስኳር በሽታ ህመምን ያስታግሳል።
240 የቅድመ-ስኳር ህመም የጀመራቸው ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት ከርኪውሚን የተመገቡት ታካሚዎች በንጽጽር ለሙሉ ስኳር በሽታ ተጋላጭነታቸው ቀንሶ ታይቷል።
እርድን እንዴት አዘውትረን መመገብ እንችላለን?
• ከጨው እና ቁንዶ በርበሬ ጋር አብሮ እርድን እንደ ቅመም መጠቀም
• ሰላጣ ስንሰራ ከአቸቶ እና ዘይት ጋር አብረን መነስነስ
እርድን መመገብ ሊያመጣ የሚችለው የጤና ችግር
እርድን በአግባቡ መጠቀም የጤና ችግር አያመጣም። ነገር ግን በከፍተኛ መጠን መመገብ ሆድን ሊያስቆጣ ይችላል። በጣም ከከፋ የሆድ አልሰር ሊያመጣ ይችላል። እርድ ደምን ስለሚያቀጥን ቀዶ ጥገና በሚደረግበት ሁለት ሳምንት ውስጥ መወሰድ የለበትም። እርጉዝ እና የሚያጠቡ ሴቶች ባይመገቡት ይመከራል።

11/15/2022

የተለመዱ ግን የተሳሳቱ አመለካከቶች

የተሳሳተ አመለካከት፦ አንድን ምግብ ስናየው፣ ስናሸተው ወይም ስንቀምሰው ደህና ከሆነ ልንመገበው እንችላለን።

እውነታው፦ አንድ ሊትር ውኃ ተበክሎ ጉም የሚመስልበት ደረጃ ላይ የሚደርሰው በውስጡ ከ10 ቢሊዮን በላይ ባክቴሪያዎች ሲኖሩ ነው፤ ሆኖም ይህን ያህል መጠን ባለው ውኃ ውስጥ ከ15 እስከ 20 አደገኛ ባክቴሪያዎች ቢኖሩ እንኳ ልንታመም እንችላለን። የምትበላውና የምትጠጣው ነገር ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ምግቡን ስታዘጋጅ፣ ስታቀርብም ሆነ ስታስቀምጥ ተገቢ የሙቀት መጠንን በተመለከተ የተሰጡ መመሪያዎችን ተከተል።

የተሳሳተ አመለካከት፦ ዝንቦች ምግብ አይበክሉም።

እውነታው፦ ዝንቦች የሚመገቡትም ሆነ የሚራቡት እንደ እዳሪ ባሉ ቆሻሻዎች ላይ ነው፤ በመሆኑም ብዙውን ጊዜ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በሽታ አምጪ ጀርሞችን በእግራቸው ይሸከማሉ። የበሰለ ምግብ በዝንቦች እንዳይበከል ሙሉ በሙሉ መሸፈን ይኖርበታል።

የተሳሳተ አመለካከት፦ “ለረጅም ጊዜ ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት አልነበረኝም፤ አሁን ለውጥ ባደርግም ያን ያህል አይጠቅመኝም።”

እውነታው፦ ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት ከሆነ አመጋገብህን ለማስተካከል አሁኑኑ እርምጃ መውሰድህ ያለዕድሜ የመሞት አጋጣሚህ እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ጤናማ አመጋገብ ይዘህ በቀጠልክ መጠን ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞች ታገኛለህ።

10/30/2022

ለምግብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ አራት ነገሮች

1. ምግብህን በጥንቃቄ አዘጋጅ።

ለምን? በተበከለ ምግብና ውኃ ውስጥ ያሉ አደገኛ ጀርሞች ወደ ሰውነትህ ሊገቡና ሊያሳምሙህ ይችላሉ።

የጤና ባለሙያዎች ምን ይመክራሉ?

ምግብ ማዘጋጀት ከመጀመርህ በፊት እጅህን በሳሙናና በውኃ ታጠብ። እጆችህን ቢያንስ ለ20 ሰከንድ በደንብ እሻቸው። የእጆችህን ጀርባ (አይበሉባ)፣ በጣቶችህ መሃል ያሉትን ቦታዎች እንዲሁም ከጥፍሮችህ ሥር ያሉትን ቦታዎች በደንብ እሻቸው። ከዚያም እጆችህን በውኃ አልቅልቀህ በደንብ አድርቃቸው።

መክተፊያዎችን፣ ድስቶችንም ሆነ ምግብ የሚቀመጥበትን ማንኛውንም ዕቃ በሳሙናና በውኃ እጠብ። በተጨማሪም የሚበስሉና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን በአንድ መክተፊያ አትክተፍ።

ማንኛውንም ፍራፍሬና አትክልት ሳታጥብ አትመገብ፤ በአካባቢህ ሰዎች እርሻ ለማልማት እዳሪ የሚገባበትን ውኃ እንደ መስኖ አድርገው የሚጠቀሙ ከሆነ የምትገዛቸውን ፍራፍሬዎችና አትክልት በጀርም ማጽጃ ኬሚካሎች አጽዳ።

2. የበሰሉና ያልበሰሉ ምግቦችን ለያይተህ አስቀምጥ።

ለምን? ያልበሰሉ ምግቦች ውስጥ ያሉ ጀርሞች (ለምሳሌ በጥሬ ሥጋና ከውስጡ በሚወጣው ፈሳሽ ውስጥ ያሉ ጀርሞች) ሌሎች ምግቦችን ሊበክሉ ይችላሉ።

የጤና ባለሙያዎች ምን ይመክራሉ?

ከገበያ የገዛሃቸውን ነገሮች ወደ ቤት ስትወስድም ሆነ ቤት ውስጥ ስታስቀምጥ ያልበሰሉ ምግቦችን (በተለይ ሥጋን) ከበሰሉ ምግቦች ለይተህ አስቀምጥ።

ሥጋ ከከተፍክ በኋላ ሌላ ነገር ከመክተፍህ በፊት እጅህን በሚገባ ታጠብ፤ የተጠቀምክበትን ቢላና መክተፊያም በደንብ እጠብ።

3. በእሳት መብሰል ያለባቸውን ምግቦች በሚገባ አብስል።

ለምን? ጎጂ ጀርሞችን መግደል የሚቻለው በከፍተኛ ሙቀት ብቻ ነው።

የጤና ባለሙያዎች ምን ይመክራሉ?

ምግብ ስታበስል በደንብ ከመብሰሉ በፊት አታውጣው። የምታበስለው ምግብ (የሥጋን ውስጠኛ ክፍል ጨምሮ) 70 ዲግሪ ሴልሸስ የሙቀት መጠን ላይ ከደረሰ በኋላ ቢያንስ ለ30 ሰከንድ እሳት ላይ ሊቆይ ይገባል።

ሾርባ ወይም ወጥ ስትሠራ በደንብ እንዲንተከተክ አድርግ።

ቀድሞ የበሰለን ምግብ ከመመገብህ በፊት ትኩስ እስኪሆንና እንፋሎት እስኪያወጣ ድረስ አሙቀው።

4. ምግብህን በተገቢው የሙቀት መጠን ላይ አስቀምጥ።

ለምን? ከ5 እስከ 60 ዲግሪ ሴልሸስ ባለ የሙቀት መጠን ላይ የተቀመጠ ምግብ በ20 ደቂቃ ብቻ በውስጡ ያሉት ባክቴሪያዎች በእጥፍ ሊጨምሩ ይችላሉ። በተጨማሪም ጥሬ ሥጋ በተገቢው የሙቀት መጠን ላይ ካልተቀመጠ በውስጡ ያሉት አንዳንድ ባክቴሪያዎች የሚያመነጯቸው መርዞች ሥጋው በእሳት ከበሰለ በኋላም እንኳ ላይጠፉ ይችላሉ።

የጤና ባለሙያዎች ምን ይመክራሉ?

ምግብ፣ ወይ ቀዝቃዛ ወይ ትኩስ ሆኖ መቀመጥ አለበት እንጂ ለብ ብሎ መቀመጥ የለበትም፤ ይህም በምግቡ ውስጥ ያሉት ጀርሞች የሚባዙበትን ፍጥነት ለመግታት ወይም ጨርሶ እንዳይባዙ ለማድረግ ይረዳል።

ምግብህን ማቀዝቀዣ ውስጥ ሳታስገባ ከሁለት ሰዓት በላይ ማቆየት አይኖርብህም፤ የክፍሉ ሙቀት ከ32 ዲግሪ ሴልሸስ በላይ ከሆነ ደግሞ ምግቡ ከአንድ ሰዓት በላይ ውጭ መቆየት የለበትም።

ምግብ ካበሰልክ በኋላ እስክታቀርበው ድረስ ትኩስ ሆኖ እንዲቆይ አድርግ።

የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞችአብሽ ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉን? ለልብ ድካም፣ ለደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጉውራ እና በሱካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው:: ገ...
10/24/2022

የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞች

አብሽ ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉን? ለልብ ድካም፣ ለደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጉውራ እና በሱካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው:: ገና ለወለዱ እናቶችም የጡታቸውን መጠን በተወሰነ መልኩ በመጨመር ጠቀሜታ አለው::

በዝርዝር ቀጥሎ ይቀርባል

✅ የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል - አብሽ ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ኢንሱሊን መቋቋምን ይቀንሳል።

✅ የልብ በሽታን Heart Attacks) ያስወግዳል - የልብ ጉዳትን ለመከላከል እና ኦክሲዳቲቭ ውጥረት (oxidative stress) ለማስወገድ ይረዳል።

✅ የወር አበባ ቁርጥማትን (Cramps) ያስታግሳል - አብሽ ከቁርጥማት በተጨማሪ፣ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ እና ድካምን ለመቀነስ ይረዳል።

✅ የጡት ወተት ምርትን ያሻሽላል -አብሽ ፓይቶኤስትሮጅን (phytoestrogen) የተባለ የወተት ምርትን የሚጨምር ውህድ ስላለው፤ ለሚያጠቡ እናቶች ይረዳል።

✅ የአርትራይተስ (Arthritis) ህመም ለመቀነስ ይረዳል:- አብሽ አንቲ-ኦክሲደንት እና አንቲ-ኢንፍላማቶሪ ባህርያት ስላለው፤ በአርትራይተስ የሚመጣን ህመም ለመቀነስ ይረዳል።

✅ የምግብ መፍጨት ችግርን ይረዳል:- የሆድ ድርቀትን እና ከጨጓራ መቆጣት የተነሳ ለሚከሰት የምግብ መፍጨት ችግር ን ለመከላከል ይረዳል።

✅ ፀረ- እርጅና ጥቅም አለው:- ለቆዳችን አስደናቂ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን የእርጅና ምልክትን እንደ የቆዳ መጨማደድ እና ቀጫጭን መስመሮችን ያስወግድልናል።

✅ ብጉርን ለመፈወስ:- አብሽ አንቲ-ኢንፍላማቶሪ እና ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪያት ስላሉት፤ ብጉርን ለመከላከል ይረዳል።

✅ ቆዳን ለማርጠብ (moisturize):- የአብሽ የሚሙለጨለጨው በሃሪ የደረቁ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳችን እንዲረጥብ ይረዳናል።

ጥቁር-አዝሙድ ለጤና...1ኛ. ለእርጋታ -አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝ...
10/20/2022

ጥቁር-አዝሙድ ለጤና...
1ኛ. ለእርጋታ -
አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡
አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡ የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡

2ኛ. ለሳልና ለአስም -
በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡

3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ -
አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡

4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት -
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡

5ኛ. ለኩላሊት ጠጠር -
ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡ (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው)

6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት -
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ ልዩነቱን በጉልህ ያገኙታል፡፡

7ኛ. ከበሽታ ሁሉ ለመጠበቅ -
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር አዋሕዶ ያለማቋረጥ ጧት ጧት መውሰድ በሕይወት ዘመንዎ ሙሉ ጤነኛና የሐኪም እርዳታ የማያሻው ሰው ይወጣዎታል፡፡

8ኛ. በጭንና ጭን መካከል የቆዳ መቆጣት ሲያጋጥም -
በቅድሚያ አካባቢውን በውኃና በሳሙና በሚገባ ማጠብ፣ ቀጥሎ በሚገባ ማድረቅና በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማታ ቀብቶ ማደርና ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይህንኑ መፈጸም፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ውጤቱን ያዩታል፡፡

9ኛ. ለልብና ለደም ሥሮች ሕመም -
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት ይረዳል፡፡

10ኛ. ለለምጽና ለመሳሰሉት -
ተጠቂውን የሰውነት ክፍል በቱፋሕ (ፖም) ወይም አፕል ኮምጣጤ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለ15 ቀናት መቀባት፡፡

11ኛ. ለቁርጥማት ሮማቲዝምና የጀርባ ሕመም -
የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት፡፡

12ኛ. ለራስ ምታት -
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

13ኛ. ለጨጓራና ለአሲድ -
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ በሽታው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡

14ኛ. ለራስ ማዞርና ለጆሮ ሕመም -
አንድ ጠብታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጆሮ ውስጥ መጨመር በሻይ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት፡፡

15ኛ. ለቆዳ መቀረፍ -
በዚህ አይነቱ ሕመም የተጠቃው የአካል ክፍል በጥቁር አዝሙድ ዘይት መቀባት ሕመሙ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መቀጠል፡፡

16ኛ. ለቡግር -
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት የሰሊጥ ዘይትና አንድ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት ጨምሮ በአንድነት መለወስ ማታ ማታ ተቀብቶ ማደርና ጠዋት ለብ ባለ ውኃና በሳሙና መታጠብ፡፡

17ኛ. ለስብራት አፋጣኝ ጥገና -
የምስርና የሽንኩርት ሾርባ፣ ቅቅል እንቁላል፣ አንድ ትልቅ ማንኪያ የደቀቀ ጥቁር አዝሙድ በአንድነት ቀላቅሎ ቢያንስ አንድ ቀን ወስዶ በቀጣዩ ቀን አርፎ እንደገና በሁለተኛው ቀን መውሰድ፤ ስብራቱ የዘመናዊ ሕክምና በጀሶ ከታሰረ በኋላ በአቅራቢያ ያለውን አካል በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማሸት፤ እስሩ ከተፈታ በኋላ ደግሞ ለብ ባለ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በየቀኑ ማሸት ነው፡፡

18ኛ. ለጠባሳና ለመሳሰሉት -
አንድ እፍኝ ጥቁር አዝሙድ በሚገባ ማፍላት የተጎዳውን አካል ማጠብና ለሩብ ሰዓት በተዘጋጀው ፍል ጥቁር አዝሙድ ውስጥ መንከር፡፡ አካሉን ማንቀሳቀስ፡፡ ሳይሸፈን አድካሚ እንቅስቃሴ ሳያደርጉ መቆየት፡፡ ከመኝታ በፊት በየቀኑ ይህን መደጋገም፡፡

19ኛ. ለደም ብዛት -
ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ቢወስዱ ምንኛ ጥሩ ነበር፡፡

20ኛ. ለኩላሊት ኢንፌክሽን -
የጥቁር አዝሙድ ዱቄት በወይራ ዘይት ለውሶ ሕመም በሚሰማበት ቦታ መለጠፍ፤ በተጨማሪም አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፣ ከዚያ በኋላ ኢንፌክሽኑ ይወገዳል፡፡

21ኛ. ለሐሞት ከረጢት -
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ ሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት፡፡ ፊትዎ ቅላት እስኪያሳይና ችግሩ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መፈጸም፡፡ በየዕለቱ በባዶ ሆድ አንድ ሲኒ የወይራ ዘይት መጠጣት አይርሱ፡፡

22ኛ. ለልብና ለደም ዝውውር ችግር -
የልብ ሕመምተኛ ሰው በማናቸውም ወቅት እንደ ምግብም፣ እንደመጠጥም እንደአስፈላጊነቱ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

23ኛ. ለትውከት -
ጥቁር አዝሙድ ከቅርንፉድ ጋር በደንብ ማፍላት ማጣፈጫዎች ሳይጨምሩ በቀን ሦስት ጊዜ መጠጣት፡፡ ሁለተኛ ዙር መጠጣት አያስፈልግም፡፡

24ኛ. ለቃርና ለመሳሰሉት -
የተወሰኑ የጥቁር አዝሙድ ቅባት ጠብታዎች በአንድ ኩባያ ትኩስ ወተት ውስጥ ጨምሮ በማር አጣፍጦ መጠጣት፡፡ የቃር ስሜትዎ እንዳልነበር ሆኖ ይጠፋል፡፡ በእንግሊዘኛ (Lettuce) የተሰኘውን ተክል በብዛት መብላትንም አይዘንጉ፡፡

25ኛ. ለዓይን በሽታ -
በጥቁር አዝሙድ ዘይት በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የሰውነት አካል ከመኝታ በፊት ማሸት በማናቸውም ትኩስ መጠጥ ውስጥ አልያም የሥራ ሥር ጭማቂ እንደ ካሮት የመሳሰሉት ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡

26ኛ. የምግብ ፍላጎትን ለማሳደግ -
ከምግብ በፊት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ቅመሙን በጥርሶችዎ ማድቀቅ፣ ከዚያም ጥቂት ኮምጣጤ ጠብታዎች የተቀላቀለበት አንድ ስኒ ቀዝቃዛ ውኃ ያወራርዱት፡፡

27ኛ. ለቅማልና ለቅጫም -
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት በኮምጣጤ ለውሶ ለመታሻ በሚያገለግል መልኩ ማዘጋጀት ፀጉርን ተላጭቶ መቀባት አሊያም ቆዳው ድረስ ዘልቆ እንዲገባ ማድረግና ለሩብ ሰዓት ለፀሐይ ማጋለጥ፡፡ ከአምስት ሰዓታት በኋላ መታጠብ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንኑ ደጋግሞ መፈጸም፡፡

28ኛ. ለጥርስ፣ ለቶንሲልና ለጉሮሮ ሕመም -
የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና ለጉሮሮ ችግር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት፡፡

29ኛ. ከደም ላይ ኮሊስትሮን (ስብን) ለማስወገድ -
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት አንድ ማንኪያ የእኸሊ ቅጠል ከአንድ ስኒ ንጹሕ ማር ጋር ለውሶ በባዶ ሆድ መብላት፡፡

30ኛ. ለሽንት መታቀብ ችግር -
ከእምብርት በታች ያለውን የሰውነት አካል በጥቁር አዝሙድ ቅባት ከመኝታ በፊት ማሸት፡፡ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በአንድ ኩባያ ውኃ አፍልቶ በማር አጣፍጦ ከመኝታ በፊት በእለቱ መጠጣት፡፡

31ኛ. ፊት ላይ እንደ ቡጉር ክብ ሆኖ ለሚወጣ አተርን ያክል ጠጣር ነገር
በሽታ በሽታው የሰፈረበትን አካባቢ በረጅላ (Purslane) ተክል በሚገባ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት 15 ቀናት መቀባት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት መጠጣት፡፡

32ኛ. ለሚያስነጥስ -
ከባሕር ዛፍ የተጨመቀ ዘይት 40% ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር ደባልቆ በሁለቱም አፍንጫ በቀን ሦስት አራት ጊዜ ጠብታ ማድረግ ነው፡፡
ምንጭ:- ዶ/ር ኢያሱ ኃ/ሥላሴ

Address

Silver Spring, MD
20902

Telephone

(301)3004597

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Romi catering posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Romi catering:

Share

Category